በ2007 የተገነቡ የቡልቡላ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱ ነው ፤ አዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ገንቢዎቹን እንደሚጠይቅና የመፍትሄ ርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

Date:

አዲስ ሪፖርተር | አዲስ አበባ | የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ስር ከተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በግንባታ ጥራት ምክንያት እይፈረሱ ያሉ ተለይተው ነዋሪዎች እንዲለቁ እየተደረገ መሆኑ ተሰምቷል። የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ህንጻዎቹ እየፈራረሱና አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ዘርዝሮ በደብዳቤ በማሳወቁን ተከትሎ እርምጃው እንደተወሰደ መረጃውን ለአዲስ ሪፖርተር የሰጡ ገልጸዋል። ኮርፖሬሽኑ በበኩሉ ችግሩ መኖሩን አምኖ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አስታውቋል። አንዳንድ ነዋሪዎች ግንባታውን በወቅቱ ካከናወኑት መካከል ማንነታቸው ሁሉ የማይታወቅ ወይም እንዲጠፋ የተደረገ መኖሩንም ጥቆማ ሰጥተዋል።

አዲስ ሪፖርተር በአካል ተገኝቶ እንዳየው በቡልቡላ ኮንዶሚኒየም በተለይ ሰባት ብሎኮች ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ነዋሪዎችን ወደ ሌላ አካባቢዎች የማንሳት ስራ እንደሚጀመር ማረጋገጥ ችሏል። አንዳንድ ነዋሪዎች እንደሚሉት። ኮርፖሬሽኑም አጥንቶ ዶክመንት ማዘጋጀቱን ገልጾ፣ ከነዋሪዎቹም ጋር መግባባት ተደርሶ አስፈላጊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ግልጿል። በተመረጡት ብሎኮች ነዋሪዎችን ለማዘዋወርና ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ ዝግጅቱ መጠናቀቁን አስረድቷል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ከጥራት ችግር ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄ ሲመልስ የጥራት ችግር ያለባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ያሉት መሆናቸውን ይገልጻል። ጥቆማ አይሰጥ እንጂ በርካታ የጋራ መኖሮሪያ ቤቶች የግንባታ ጥራት ችግር እንዳለባቸው በገሃድ የሚታይ ሲሆን፣ በርካታ ነዋሪዎች ግንባታዎችን ተመለክተው ክፍያ በሚያጸድቁ ባለሙያዎች ላይ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባም ሆኑ መንግስት ሊጠይቃቸው የማይችልበት ምክንያት አይገባቸውም።

በአብዛኛ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጎልቶ የሚታይ ቢሆንም፣ ቀደም ሲል የተገነቡት የመኖሪያ ቤቶች ጥራት “ተቆጣጣሪ የለም ወይ” በሚያስብል ደረጃ አስገራሚ ነው። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኤጀንሲ ለአዲስ ሪፖርተር በድምጽ በላከው ምላሽ፣ ችግሮች ያለባቸውን የመኖሪያ ህንጻዎች ተለይተው፣ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ጋር ጥናት ተጠንቶ ወደ ትግበራ እየተገባ መሆኑን አመልክቷል።

“በጥናቱ መሰረት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተለይተዋል” ያለው ኮርፖሬሽኑ፣ የተጠቀሰው የቡልቡላ ሳይት ቅድሚ ከሚሰጣቸው ሳይቶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው መሆኑን አስረድቷል። የጥገና ስራው ለኮንትራክተር ተሰጥቶ ወደ ስራ እየተገባ መሆኑን አመልክቷል።

ጠፋ የተባለው መረጃ አስመልክቶ ኮርፖሬሽኑ ሲመልስ፣ መረጃዎቹ በቢሮ እንደሚገኙና፣ ምንም የጠፋ መረጃ እንደሌለ አስታውቋል።”ከተጠያቂነት ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄ በህጉና በህጉና መሰረት ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ ነው” በማለት ምላሽ ሰጥቷል።

ኮርፖሬሽኑ ይህን ቢልም ከ2007 ጀምሮም ሆነ በቅርቡ በተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ላይ የሚታየው የጥራት ጉድለት አነጋጋሪ ነው። በርካታ ዜጎችም ሆኑ የአዲስ ሪፖርተር ዘጋቢ እንዳየው ፐሮጀክቶቹን ገምግመው ያጸደቁና እንዳለቁ አድርገው የተቀበሉ እሰከ ዛሬ ድረስ ሳይጠየቁ መቆየታቸው አሳዛኝ ነው። አስር ዓመት ሙሉ ህንጻዎች እየፈራረሱና እያዘመሙ ቢታዩም በተጠያቂነት ከኮርፖሬሽኑም ሆነ፣ ግንባታውን ያከናወኑት ተቋማት አለመጠየቃቸው በሚመከታቸው ተቆጣጣሪ ሊመርመር እንደሚገባ በረካታ ዜጎች እየጠየቁ ነው።

ዝግጅት ክፍላችን በዚህ ዘርፍ እና በመንገድ ዘርፍ የአዲስ አበባ ኮሪዶር መንገዶችን በማካተት ተከታታይ መረጃዎችን እንደሚያቀርብ ያስታውቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ መረጃ ያላቹህ ለዝግጅት ክፍላችን ትልኩልን ዘንዳ ትብብር እንጠይቃለን።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related