የባሌ ጎባው ስብሰባ ቀልብ ስቧል፤ መንግስት የቀድሞ ባለስልጣናትን አካቶ ባሌ ጎባ በጂኦስትራቴጂ ጉዳይ እየመከረ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂያዊ መነቃቃት የባሌ ጉባው ጉብኝትና የሚንስቴር መስሪያ ቤቶች ጆኦስተራቴጂክ ስልጣነና ቀልብ የሚስብ ሆኗል። በተለይም አሁን ላይ መንግስት በስፋት እየገለጸ ካለው ወደ ቀይ ባህር የመመለስ ዕቅድ አንጻር ጉዳዩ ትኩረት የሚሰጠው ሆኗል።

በፌደራል መንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ለሰራተኞቻቸው በኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂ ጉዳዮች ላይ ስልጠና እየሰጡ እንደሚገኙ ይፋ ሆኗል። ይህ ስልጠና የሀገሪቱን ዋና የትኩረት አቅጣጫ ግልጽ አድርጓል። የዚህ ስልጠና ዋነኛ ዓላማ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ስትራቴጂያዊ አቋም፣ በተለይም ደግሞ ከቀይ ባህር ጋር በተያያዘ ያላትን የረጅም ጊዜ ብሔራዊ ጥቅም በተመለከተ ሰፊ የመንግስት ግንዛቤ መፍጠር ነው።
ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣቷ በኢኮኖሚዋ ላይ የሚፈጥረውን ጫና እና የሀገሪቱን የህልውና ጥያቄ ከማህበረሰቡ እና ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር መሞከር የዚህ ስልጠና ዋናው ተልዕኮ ነው። ይህ እርምጃ የባህር በር ጥያቄ ከፖለቲካዊ አጀንዳነት ወደ ዘላቂ ብሔራዊ ስትራቴጂ ከፍ ማለቱን ያመላክታል።

በሌላ በኩል፣ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የቀድሞ የትግራይ ህዝቦች ነፃ አውጪ ግንባር (ህወሃት) እና የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦህዴድ) አመራሮችን ጨምሮ ለየት ያለ የፖለቲካ ልዑክን ይዘው ወደ ባሌ ጎባ አቅንተዋል።

የቅርብ ምንጮች ጉብኝቱ በባሌ ተራሮች እየተገነቡ ያሉትን የቱሪስት ሎጆችን ለመጎብኘት እንደሆነ ቢገለጽም፣ የልዑኩ ስብስብ ለየት ያለ መሆኑ ዓላማው ከቱሪዝም አልፎ ጂኦስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እንደሆነ መገመት አይከብድም ባይ ናቸው።

በተለይም እንደ አሰብ ያለ ወሳኝ የባህር በር ጥያቄን በብሔራዊ ደረጃ ለመምከር እና የጋራ አቋም ለመያዝ የሚደረግ ጥረት መሆኑን አመላካች ነው። የአሰብን ጉዳይ ጨምሮ የባህር በር ጥያቄ የፌደራል መንግስቱን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ክልሎች በተለይም ደግሞ የትግራይን ክልል በቀጥታ የሚመለከት የህልውና ጉዳይ ነው።

እነዚህ ሁለቱ ክንውኖች – የጂኦስትራቴጂ ስልጠናው እና የባሌ ጎባው ጉባኤ – ከኢትዮጵያና ኤርትራ ወቅታዊ ግንኙነት አንፃር ሲታዩ ተመሳሳይ ስልታዊ አንድምታዎችን ይሰጣሉ። ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን በውስጣዊ ብሔራዊ መግባባት ለማጠናከር መሞከሯ፣ ለኤርትራ መንግስት እና ለሌሎች የውጭ አካላት የኢትዮጵያ አቋም ጠንካራ ብሔራዊ መሠረት እንዳለው ማሳያ ነው። የባህር በር ጉዳይ በአንድ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን በብሔራዊ መግባባት የተደገፈ መሆኑ፣ በጉዳዩ ላይ የሚደረጉ ማናቸውም የዲፕሎማሲ ወይም ሌሎች እርምጃዎች ዘላቂነት እንደሚኖራቸው ያመለክታል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ የቀይ ባህርን አስፈላጊነት በስልጠና ማጉላት እና በአሰብ ዙሪያ የምትወስዳቸው ማንኛውም እርምጃዎች ለኤርትራ ከፍተኛ የሉዓላዊነትና የፀጥታ ስጋት መፍጠሩ አይቀርም። በመሆኑም የባሌ ጎባው ስብሰባ የአሰብን ጉዳይ ከብሔራዊ መግባባት አንፃር በመመልከት፣ ለኤርትራ የሚልከው መልዕክት የኢትዮጵያ ፍላጎት ሰላማዊ እና ህጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ ለመስራት መሆኑን ማመልከት አስፈላጊ ሆኗል።
በአጠቃላይ የፌደራል ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች የጂኦስትራቴጂ ስልጠና እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የባሌ ጎባ ጉብኝት ተራ መገጣጠም ሳይሆን ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ስልታዊ እርምጃ እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ይገልፃሉ። ይህም የኢትዮጵያ መንግስት የባህር በር ጥያቄን እንደ ዋና የብሔራዊ ህልውና ጉዳይ በመውሰድ፣ የውስጥ መግባባትን በመፍጠርና አቋሙን በማጠናከር ለቀጣይ የውጭ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች መዘጋጀቱን የሚያሳይ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ በቅርቡ ከኤርትራ ጋር በተፈጠረው ውጥረት ውስጥ የኢትዮጵያን አቋም ያጠናክራል።

3 COMMENTS

  1. የጎባና አካባቢው ከተሞች ላይ በተለይ በጎባ ከተማ ላይ የተደራጁ የከተማው ደላላና የመሬት አስተዳደር ሰራተኞች በቅንጅት እያደረጉ ያለውን የመሬት መቀራመትና ሙሰኝነት እንዲሁም መረጃ የላችሁም በማለት የባለቤትነት ይዞታ መረጃዎችን ደብዛ በማጥፋት ህዝብንና መንግስትን እያቃቃሩና መሬት ነጠቃ ላይ መሆናቸውን መከላከል ያልቻለ የክልሉ መንግስትና የከተሞቹ መስተዳድራን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲጎበኟቸው ምን ጥሩ ሪፖርት ይዘው ይቀርቡ ይሆን? ኧረ ጭራሽ የአካባቢ ፍርድ ቤቶች ጭምር በሙስና ይታማሉ:: ነው ወይስ ጠ/ሚኒስትሩ ጭራሽ አይጠይቋቸው ይሆን?? ጠቅላዩንና አስተዳደራቸውን እንዲሁም ህዝብን እርስ በእርስ እያቃቃሩና ሴራ እየሸረቡ መሆኑን የሚመለከተው አካል ይስማልን::
    ይህችን መረጃ ለሚዲያና ለሚመለከተው የመንግስት አካል አሳውቁልን::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...