“የመንግስት ሚድያዎች በተፎካካሪዎችና በገዥው ፓርቲ መካከል ያለው የመወዳደርያ መድረክ ኢፍትሐዊ አድርገውታል” ኢዜማ

Date:

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ለፓለቲካ ምህዳር መጎልበት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል

የኢትዮጵያ ዜጎች ማሕበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( ኢዜማ ) ፣ የመገናኛ ብዙዎች ለተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሰጠው የመወዳደሪያ መድረክ የፓለቲካ ምሕዳሩ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንሚኖረው አስታወቀ። በዚሁ ሳቢያ ፓርቲው በቀጣይ የሚደረገውን አገራቀፍ ምርጫ ላይ ከሚዲያዎች ፍትሃዊ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ስጋት እንዳለበት አመልከተ።

ፓርቲው እንደምክንያት ያነሳው የፓለቲካ ሐሳብ በዋናነት የሚስተናገዱባቸው መገናኛ ብዙሐን በበርካታ ሰንካ ስር መኾናቸውን ጠቅሶ በተለይም ሕዝብ በሚከፍለው ታክስ የሚተዳደሩ እንደመኾናቸው መጠን ሕዝብ እኩል የሚስተናገድባቸው ሊሆኑ እንደሚገባ ጠቁሟል።

ፓርቲው፣ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሚል የጠቀሳቸው ሚድያዎች እነማን እንደሆኑ በስም ባይዘረዝርም በደፈናው በመንግሥት በጀት የሚተዳደሩ መገናኛዎችን መኾናቸውን ባቀረበው ወቅሳ አመላክቷል። እንደ ኢዜማ ገለፃ ከኾነ አጠቃላይ የፓለቲካ ሐሳብ ገበያውን እና አጠቃላይ የሚድያ ምሕዳሩ በገዥው ፓርቲ ስር ወድቋል፡፡

መንግስት ስር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙሃን ተቋማት እና ባለሞያዎች በተለይም ጋዜጠኞች ላይ እየደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅእኖ እየከፋ መምጣቱንና በመንግሥት እና በፓርቲ መካከል ያለውን አረዳድ ላይ ተፅእኖ እያሳዳረ እንደሚገኝ አደረኩት ባለው ጥናት መረዳቱን ኢዜማ አስታውቋል። ኢዜማ ” ጉዳት ደረሰባቸው” በማለት የ”ጋዜጠኝነት” ስም የሰጣቸውን አላብራራም።

” የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ለገዥው ፓርቲ አመራሮች የሚሰጠው የአየር ሰአት የተጋነነ ነው” ያለ ሲኾን በዝያን ልክ ለተወዳዳሪ ፓለቲካ ፓርቲዎች እየተሰጠ ያለውን የመገናኛ ምህዳር ጠባብ መኾኑን ገልፆ በሌላ በኩል መንግስትን የሚተቹ ፕሮግራሞች ችግርና የምርመራ ዘገባዎች የሚሰሩ የጋዜጠኞች ቡድን አለመኖር አጠቃላይ ምሕዳሩ ያለበት አስቸጋሪ ሁኔታ መመልከት በቂ ነው ብሎ እንደሚያምን አመልክቷ፤።

በተለምዶ የንግድ መገናኛ ብዙሐን የሚባሉት የግል ሚድያዎች የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ድምፅ ለመኾንና አካታች እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ገልፆ የመንግስት የሚባሉት መገናኛ ብዙሐን ሁልጊዜ በሚባል ደረጃ መንግስትን የሚነቅፉ አጀንዳዎች እስካልሆኑ በስተቀር ዜናና ፕሮግራሞች ለመስራት ተነሳሽነት የላቸውም ሲል ኢዜማ ወቅሷል።

ሁኔታዎች በዚህ የቀጠሉ እንደኾነ የአገሪቱ ፓለቲካ ምሕዳር በታለመለት መልኩ ይሳካል የሚል እምነት እንደሌለው ኢዜማ ጠቅሶ በተለይም በቀጣይ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ ምርጫ የመገናኛ ብዙሃን በአካታችነት እና የፓለቲካ ብዙሀነት ሊያስተናግዱ ይገባል ሲል አሁን ላይ ያለውን የሚድያው ምሕዳር ያለውን አቋም አንፀባርቋል።

መንግስት በተለይ የንግድ ብሮድካስት መገናኛ ብዙሃን ከሚያደርሳቸው ተፅዕኖዎች አንዱ የመንግስት አካላትን በዘገባዎቻቸው ተጠያቂ ለማድረግ በሚሞኮሩበት ጊዜ ማስፈራርያ፣ ሕገወጥ እስሮች፣ ያለ ፍርድቤት ትእዛዝ በሕግ ቁጥጥር እንዱውሉ በማድረግ እና በዘፈቀደ እስር እየደረሰባቸው እንደሚገኝ በቀጣዮ ምርጫ ላይ ተፅእኖ ማሳደሩ እንደማይቀር ፓርቲው ተናግሯል። ፓርቲው ይህን ትችቱን ስምና ሚዲያ ጠቅሶ አላቀረበም።

“አንዳንዴም ስጋቶች እንዲፈጠሩ በማድረግ ጋዜጠኞች ዘገባዎቻቸው በትክክል እንዳይሰሩ እየተደረገ ይገኛል” ሲል የወቀሰ ሲኾን የመገናኛ ብዙሐን ባለቤቶች በአንድም በሌላ መንገድ ጫና ስር እንዲወድቁ እየተደረገ መኾኑን “ካለኝ ትዝብት” መረዳት ችያለሁ ብሏል።

የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ከራሳቸው ድክመቶች የሚመነጩ ዓይነተኛ ተግዳሮት እየገጠማቸው መኾኑን የገለፀው የኢትዮጵያ ዜጎች ማሕበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( ኢዜማ ) ተቋማቱ በሚመሯቸው አካላት ፍላጎት ምክንያት ገለልተኝነታቸውን ማጣት፣ ሚዛናዊ መረጃ ማድረስ ሳይችሉ መቅረትና አንዳንዴ ሞያዊ ብቃት ማነሶች እየተስተዋለ መኾኑንና ይህ ሁኔታ በአገእ አቀፉ ፓለቲካዊ ውድድር አሉታዊ ተፅእኖ እንዳይፈጥር ስጋት እንዳለው ፓርቲው ተናግሯል ።

ፓርቲው ለዚህ ሁሉ ችግር እንደምክንያት የሚያነሳው ቀደም ባሉ ጊዜያቶች አገራዊ ተቋማትን በመፍጠርና ገለልተኛ ብሔራዊና የጋራ ተቋማት በማቋቋም መጀመር የነበረበት በሚድያው ዙሪያ መሆን አለበት የሚል እምነት እንዳለውና ይህም አለመሆኑ እንደአገር ተቋማት ግንባታ ላይ ያለውን ክፍተት ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ሲል ተችቷል።

መገናኛ ብዙሃን ለሐሳብ ብዙሃነት በማስተናገድ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መኾኑን የሚታቅ ቢኾንም በዚህ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ክፍተት እየተስተዋለ መኾኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ማሕበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( ኢዜማ ) ስሞታ አቅርቧል። የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ለፓለቲካ ምህዳር መጎልበት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ፓርቲው ጠይቋል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...