የቅንጅት ዘመን “መቀናጆን” ያስታወሰው አብሮነት፤ ሱናሚ Vs የሰማይ ላይ ትዕይንት

Date:

” አብሮነት” የተባለውን አዲስ ስብስብ ከ1997 ቅንጅት ጋር የሚያመሳስሉ ወገኖች “ነገሩ ግትምጥም ነው” ይላሉ። አብሮነትና ቅንጅት የተመሳሰሉባቸው ሳይጣመዱ “ተጣመድን” ማለታቸው ሲሆን ግጥምጥሙ ደግሞ አቶ ልደቱ ዋና ተዋንያን ሆነው ከፊት መምጣታቸው እነደሆነ እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ።

“የሰማይ ላይ ትዕይንት” በሚል የሳይበር ዓለም ዓቀፋዊ ስብሰባ የተጀመረው የአብሮነት ዘመቻ ሲታወጅ ከ1997 የምርጫ ዋዜማ “ሱናሚ” የተሰኘ የሕዝብ ጎርፍ ከታየበት ሰልፍ ጋር ለማመሳሰል መሞከሩን እነዚሁ ወገኖች ያብራራሉ።

“የምድሩን ጨርሰው የሰማይ ላይ ሰልፍ ጠሩ” በሚል ያላገጡት ሳይሆኑ፣ በማስታወቂያው ተስበው በአዲሱ የአቶ ልደቱና ከጀርባቸው ሆነው አጀንዳ ይሰጧቸዋል በሚባሉት አካላት ቅስቀሳ ወደ “ጥምዶው” የተንሸራተቱ በርክተዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ቦርድ የሰየመው አብሮነት፣ ባለፈው ቅዳሜ ሰባት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ለመስየም ቀጠሮ ይዞ ተሰብስቦ ነበር፡፡

ከሃያ አንዱ የቦርድ አባላት መካከል የሆኑና የቨርቱዋል ስብሰባውን የተካፈሉ ለአዲስ ሪፖርተር ሲናገሩ ” በስብሰባው የተገኘነው አስራ አምስት ነበርን” በማለት ነው የሚጀምሩት።

ገና ከጅምሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጃዋርን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን ከአብሮነት ሲያገሉ በአሁኑ ሰዓት ጥምረቱ ውስጥ ያሉት ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል ብቻ እንደሆኑ ከተሰበሳቢዎቹ ለማወቅ ተችሏል።

ሲቋቋም ኢትዮጵያ ካለችበት ውጥንቅጥና ጦርነት እንድትወጣ ሰላማዊ ትግል ለማድረግ የጸና አቋም ይዞ መነሳቱን፣ በመግለጫ፣ በቃለ ምልልስ፣ በውይይትና በሳይበር በተጠራ ሰላማዊ ሰልፍና መድረክ ያስታወቀው አብሮነት ገና ሳይጣመድ ከወዲሁ መልፈስፈስ እንደገጠመው አብረው ስብሰባዎቹን የሚያከናውኑት ይናገራሉ።

ባለፈው ሳምንት በተጠራው ስብሰባ ዋና አጀንዳው ለሕዝብ ግልጽ የማይሆኑ ሰባት የስራ አስፈጻሚ አባላትን መሰየም ሆኖ ሳለ ያልተጠበቀ ክርክር ተነስቶ ስብሰባው ያለ ውጤትና ያለ ቀጠሮ መበተኑ ታውቋል። ቀታዩ ስብሰባ መቼ እንደሚሆንም አልታወቀም።

የትጥቅና የሰላማዊ ትግል አቀናጅተን እንቀጥል

ስብሰባው እንድተጀመረ አብሮነት የጠመንጃ ትግል እያደረጉ ያሉትን ኃይሎች ማለትም የኦሮሞ ነጻ አውጪ ጦርን፣ የፋኖ ኃይሎችን፣ የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባርንና የትህነግ ተዋጊዎችን መደገፍ እንደሚገባ ገልጸው አሳብ የሰነዘሩ ተሰሙ።

እነዚህ ወገኖች የትጥቅ ትግልን መደገፍ የአብሮነት አልፋና ኦሜጋ የሆነ መርህ መሆን እንዳለበት ሲሞግቱ አቶ ታምራት ላይኔና አቶ ልደቱ ተጋግዘው መሆን እንደማይገባው በመግለጽ ሰፊ ክርክር አድርገዋል። በስተመጨረሻ አቶ ታምራት አቋማቸውን ቀይረው የትጥቅ ትግል ለመደገፍ ተስማሙ። በዚሁ ከአስራ አምስት ተሰብሳቢዎች ውስጥ የርዕዮቱን ቴዎድሮስ ጸጋዬን ጨምሮ በአብዛኞቹ አንድ አቋም በመያዛቸው ስምምነት ላይ ሳይደረስ ስብሰባው ማለቁን ተሰብሳቢዎቹ ለአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግተን ተባባሪ ነግረዋል።

ለፌደራሊስ እሳቤ የተመለመሉት ፌይሰል ሮብሌ

በዕለቱ ናይሮቢ ሆነው ስብሰባውን የተከታተሉት ፌይሰል ሮብሌ ከጋምቤላ፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከአፋር ወዘተ የሕዝብ ወኪል ተብለው እንደተመለመሉት እሳቸውም የሶማሌ ተውካይ ተብለው ነበር። የአብሮነት ቦርድ አባል ከሆኑት መካከል መረጃ ያካፈሉ በማስረጃ አስደግፈው እንደተናገሩት አቶ ፌይሰል ጅግጅጋ የተወለዱ የሶማሌ ዜግነት ያላቸው ናቸው።

እኚሁ ሰው ለሶማሌ ፓርላማ ተወካይ ሆነው በሞቃዲሾ መሃላ ሲፈጽሙ የሚያሳይ የቪዲዮ ማስረጃ በመላክ መረጃውን የላኩልን “አብሮነት በዚህ መልኩ ነው አብሮ የሆነው” ሲሉ የዘመነ ቅንጅትን መቀናጆ ያስታውሳሉ።

ሃሳቡን እንደሚደግፉ ያመለከቱት የመረጃው ምንጮች ሙሉ በሙሉ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ያፈገፈጉበት “አብሮነት ምኑን አብሮነት ሆነ” በሚል ወደፊት ሊገፋ እንደማይችል ከወዲሁ መደምደማቸውን አስታውቀዋል።

የኦሮሞ ፖለቲከኞች አብሮነትን ለምን ተለዩት

የኦነግ ከፍተኛ አመራር ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት “አብሮነት ውስጥ ከሚታዩት ተዋንያኖች መካከል ኦሮሞን እንደ ሕዝብ ለማጥቃት በአደባባይ የሚማማሉ አሉበት፤ ለዚህም ዓላማቸው ሎጅስቲክ በማሰባሰብ የተጠመዱና ይህንኑ ለማሳካት ሩቅ መንገድ የሄዱ እንዳሉ ምንም ድብቅ የለውም። ስለዚህ በኦሮሞ ስም እዚህ ሕብረት ውስጥ መሳተፍ ክህደት ነው” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። አክለውም የምናውቃቸውን መክረናል ዘክረናል። ሰምተዋል” ብለዋል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥሩነህ ገምታ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር በሌሎች ጉዳዮች ባደረጉት ቃለ ምልልስ ” ሰዎቻችንን እናርቃለን” በማለት አስተያየት ሰጥተዋል። ኦሮሞን ከአገሪቱ የፖለቲካ ማዕከል ለመግፋት የሚደረግ ትግል ውጤት እንደማያመጣ ለመናገር ነብይ መሆን እንደማያስፈልግ አስታውቀው “በየትኛውም ወቅት በኦሮሞ ሕዝብና ጥቅም ላይ ከሚያብሩ ጋር የሚያብሩ አባሎቻችን አይኖሩም፣ እንዳንድ ወለምታዎች ቢታዩም አርቀናቸዋል ይስተካከላሉ” በማለት ትዝብታቸውን አጋርተዋል።

አቶ ጥሩነህ ይህን ካሉ በሁዋላ ፓርቲያቸው አብሮ በመስራት፣ በመከባበር ላይ የተመሰረት ቅንጅት በመፍጠር የሚታወቅና በዚሁ መርሁ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ እንደነበረው ወደፊትም እንደሚገፋበት አስታውቀዋል። ይህ የፓርቲያቸው አቋም በአቻ ፓርቲዎችና መላው ሕዝብ ዘንድ የሚታውቅ መሆኑንም ገልጸዋል።

በኦሮሚያ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጃዋርን ጨምሮ በርካታ በስም የሚታወቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሊነሱ እየፎከሩ ካሉ ኃይሎች ጋር ማበራቸውን እንደሚቃወሙ በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች በተደጋጋሚ ሲገልጹ ተስተውሏል።

አብሮነት ደግሞ ደጋሞ እንደሚለው የትጥቅ ትግል አይደግፍም። በኢትዮጵያ ያለውን መንግስት በአምባገነንነት በመፈረጅ ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጣ ጫና ለመፍተርና ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ችግር ለማላቀቅ ራሱን መፍትሄ አድርጎ ማቅረቡን ነው የሚገልጸው።

አብሮነት በዚህ ዓላማ ቢነሳም፣ በቦርዱ ውስጥ ከተካተቱት ውስጥ የትጥቅ ትግል መደገፍ እንደሚገባቸው የሚያምኑ መበራከታቸው፣ እንደ አቶ ነአምን ዓይነት ከኤርትራ መንግስት ጋር ኝኙነት እንዳለው በይፋ የሚያስታውቅ፣ እንድ ኢንጂነር ይልቃል ዓይነት ” ከግብጽም ጋር ቢሆን ብልጽግናን ለመጣል ከረዳን አብረን እሰራለን” የሚሉ ወገኖች አካቶ የተነሳው አብሮነት እያደር መንጠባጠብ እንደገጠመው ከተመረጡት የቦርድ አባላት መካከል የሆን አስታውቀዋል።

ሕገ ደንቡ አከራከረ

በስብሰባው ላይ ሌላ የተነሳው የአብሮነት መተዳደሪያ ደንብ ነበር። ደንቡ በህቡዕ ይመረጣሉ የተባሉት / ለምን ህቡዕ ይሆናሉ? የሚለውም አላስማማም/ ቢያንስ አምስት ዓመት በፖለቲካ ድርጅት መሪነት ያለው፣ የተማረና ብዙ ልምድ ያካበተ የሚል መስፈርት አስቀምጧል።

ከአውስትራሊያ የተሳተፉት የቦርድ አባል “ለምን ያልተነጋገርንበት ሕገ ደንብ እንዲጽድቅ ይደረጋል” ያሉት አሳብ በሌሎችም በመገዛቱ ሌላው የልዩነት ምክንያት እንደሆነ ተሰብሳቢዎቹ አስታውቀዋል። በዚህና ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች ስብሰባው በህቡዕ ይሰራሉ፣ ለሕዝብ ይፋ አይሆኑም ያላቸውን ሰባት ስራ አስፈጻሚዎች ሳይመርጥ ተበትኗል።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...