የሽግግር መንግስት ቀመኞች ከአሜሪካ ወደ አምስተርዳም ፤ በባንዳነትና ማሕጸን ውስጥ ድሮ የተወለደው “አዲሱ ፍኖተ ካርታ”

በአለባቸው ጉብሳ ባልንጀራየ ሰሞኑን አምስተርዳም ውስጥ በተካሄደ የዲያስፓራ የኢትዮጵያ የፓለቲካ “ሊህቃን’ ስብሰባ ሰነድ እንደሆነ ገልፆ እንዳነበው በመልዕክት ሳጥን ላከልኝ። የሰዎቹን ከንቱነት ስለማውቅ አንብቤ አስተያየት...

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ለንግድ ባንኮች ጥብቅ መመርያ አስተላለፈ

Date:

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ አጠቃቀምን ጋር በተያያዘ የተለያዩ ሕገወጥ ነክ ግብይቶችና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች እየፈፀሙ እንደሚገኙ ማረጋገጡን አስታውቋል።

ባንኩ፣ በዋናነት የንግድ ድርጅቶችና ግለሰብ ነጋዴዎች ለንግድ ሥራቸው በሚል የተከፈቱ የባንክ ሒሳቦች ውጭ የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ ተጠቅመው የተለያዩ የንግድ ግብይቶች እየተፀሙ መሆናቸውን አደረኩት ባለው ምርመራ ማረጋገጡንና በአገሪቱ ያሉ ለሁሉም ንግድ ባንኮች ማሳሰብያ ደብዳቤ መላኩን ገልጿል።

ባንኩ ለሁሉም ንግድ ባንኮች በላከው መልእክት
ሕገ-ወጥ ድርጊት የሚጠቀሙ ደንበኞች መረጃ እንዲልኩ ባወጣው መመሪያ የገለፀ ሲኾን ድርጊቱ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣናት ቁጥጥርና ክትትል ለመሸሽ የሚደረግ ተግባር በመሆኑ ድርጊቱን የማሳወቅ ግዴታ እንዳለባቸው አስገንዝቧል።

ባንኩ ለሁሉም ንግድ ባንኮች በዚህ አግባብ የሚፈፀሙ የፋይናንስ ግብይቶች እና የገንዘብ እንቅስቃሴዎች የወንጀል ፍሬ ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ጋር የተያያዙ ወይም የተገናኙ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያለውን ጥርጣሬ በመግለፅ ንግድ ባንኮች ድርጊቱ እንዲያጋልጡ ጠይቋል።

እነዚህን መሰል ተግባራትን ለመግታት አስፈላጊው የተቀናጀ እርምጃ እንዲወሰድ መወሰኑን ጠቅሶ የፋይናንስ ሥርዓቱን ጤናማነትና ታማኝነት ለመጠበቅ እንዲሁም በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ደህንነት መጠበቅ እንዲቻል ባንኮች የተጣለባቸውን ሐላፊነት እንዲወጡ ጥብቅ መመሪያ አሳስቧል ።

ባንኩ በቅርቡ ከአለማቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር በነበረው ስብሰባ ሸብርተኝነት ጋር በተያያዘ ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውሮች የኢትዮጵያ መንግስት ቁጥጥር እንዲያደርግ አደራ እንደተጣለበት የባንኩ ዋና ገዥ ኢዮብ ተካልኝ ገልፀው የነበረ ሲኾን ባንኩ ይህንን ቁጥጥር ለማጥበቅ ሲባል ሁሉም ንግድ ባንኮች መረጃ እንዲልኩ አሳስቧል።

የፋይናንስ ደህነነት መስርያ ቤት እንዲህ ካለው ተግባር ጋር በተገናኘ የተለያዩ ምርመራዎች ሲያደርግ እንደነበር የሚታወቅ መኾኑንና ይህን መረጃ ለብሔራዊ ባንክ በመላክ የመረጃ ማጣራትና እርምጃዎችን እንዲወስድ አሳስቦ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ይሁንና ባንኩ አጠቃላይ የባንኩን ዘርፍ እና የፋይናንስ ዘርፍ ጤናን ለመጠበቅ ከባንክ ፕሬዚዳንቶች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደነበር በተደረገው ውይይትም የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ ያሉ አጠራጣሪ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ ስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር ተገልጿል።

በተለይም ባንኩ አለኝ ባለው መረጃና ጥርጣሬ መሰረት የንግድ ድርጅቶችን ተብሎ ከተከፈተው የባንክ ሒሳቦች ውጭ የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ ተጠቅመው የሚያንቀሳቅሱት ግለሰቦች መኖራቸውን ደርሼበታሁ ብሏል።

ይህንን የመከታተል ብሔራዊ ባንክ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መኖሩን አስታውሶ የሶስተኛ ወገን የባንክ ሒሳብ ተጠቃሚዎች ላይ ከባድ እርምጃዎችን እንደሚወስድ እወቁት ብሏል።

በተያያዘ መረጃ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ አገራት የሚገኙ ሐዋላ አስተላላፊ ድርጅቶች ከንግድ ባንኮች ጋር በመመሳጠር በሕገ- ወጥ እንቅስቃሴ ላይ ያሉ አካላት ከተግባራቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቆ ነበር።

ሕገ- ወጥ የሐዋላ ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ላይ በጥናት እና በመናበብ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ እና አንዳንድ አስመጪ እና ላኪ ድርጅቶችም አሁን ላይ የሚወሰደውን ርምጃ አውቀው ሊጠነቀቁ ሲሉ ገዢው ማሳሰብያ መስጠቱን መወገባች ይታወሳል።

በዚኹ መሰረት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም ባንኮች የግል ባንክ ሂሳቦችን ለንግድ እና ለሕገ-ወጥ ድርጊት የሚጠቀሙ ደንበኞችን አስመልክቶ አስፈላጊ መረጃዎችን በማደራጀት እንዲልኩ መመሪያ ማስተላለፍን ሰምተናል፡፡

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ለኢትዮጵያ የተበጀላት የሽግግር መንግስት ከአሜሪካ ወደ አምስተርዳም የተጓጓዘው አሜሪካ ባለመቀበሏ ነው

አምስተርዳም ይካሄዳል ተብሎ ብውጭ አገር በሚኖሩ በተለያዩ የተቃዋሚ ርቲ...

የሽግግር መንግስት ቀመኞች ከአሜሪካ ወደ አምስተርዳም ፤ በባንዳነትና ማሕጸን ውስጥ ድሮ የተወለደው “አዲሱ ፍኖተ ካርታ”

በአለባቸው ጉብሳ ባልንጀራየ ሰሞኑን አምስተርዳም ውስጥ በተካሄደ የዲያስፓራ የኢትዮጵያ...

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...