የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን “ጋዜጠኞችን” ከሰሰ፤ ቡድን ሳይኖር ምን ይጠበቃል?

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ እና የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን በሚያደርግበት ወቅት በተቃራኒ ብሔራዊ ቡድን ጎሎች ሲቆጥርበት የሚደሰት ኢትዮጵያዊ የስፖርት ጋዜጠኛ ተፈጥሯል ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማስታወቁን አሃዱ ዘግቧል። ዜናውን የሰሙ ሚዲያዎች በሚፈለገው ደረጃ ፌዴሬሽኑንና አሰራሩን እንደማይፈትሹ ገልጸው ቢናገሩ ይሻል እንደነበር አመልክተዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ በሜዳው እና ከሜዳ ውጭ ጨዋታዎችን በሚያድርግበት ጊዜ ጎሎች ሲቆጠሩበት የሚደስት የስፖርት ጋዜጠኛ ማየት እየተለመደ መምጣቱን የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ ተናግረዋል።

“ቡድኑ የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግብ የሚደሰት እና አሳዛኝ ውጤቶች ሲመዘገቡ የሚቆጭ የብሔራዊ ቡድኑ ደጋፊ እንዳለ ሁሉ፤ በተቃራኒ በብሔራዊ ቡድኑ ሽንፈት የሚደሰትና የሚጨፍር የሚዲያ ባለሙያ አለ” ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን የገለጹት፤ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ስታድየም የሊግ ጨዋታዎችን ለማስጀመር ከክለቦችና የፌዴሬሽን አመራሮች ጋር በቅድመ ዝግጅቱ ዙሪያ እያደረገ ባለው የምክክር መድረክ ላይ ነው፡፡

በምክክሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ፣የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር ፕሬዝዳንት ፈቃደ ማሞ እንዲሁም የሁሉም ክለቦች አመራሮች ተገኝተዋል። እንዲሁም፤ የመገናኛ ብዙሃን እና የዘርፉ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ብሔራዊ ቡድኑ ለዓለም ዋንጫ የምድብ የማጣሪያ በሁለት ጨዋታ 2-0 በሆነ ውጤት መሸነፉ ይታወሳል።

በግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ወቅት ላይ የተፈጠሩ ሁለት ክስተቶች በተመለከተ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ክስ ማቅረቡን የተገለጸ ሲሆን፤ በተለይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር የተሰማው አስነዋሪ ተግባርን ለፊፋ በወቅቱ ማሳወቅ መቻሉ ይታወሳል። ነገር  ግን የጨዋታ ነጥብ የሚያስቀይር እንዳልሆነና ሌላ የዲሲፕሊንን እርምጃ ግን እንደሚወሰድ ከፊፋ ዲስፕሊነሪ ኮሚቴ በኩል መገለጹም መነሳቱ አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ትንሳኤ እንደሚያሰፈልገው በተጨማሪነት የተገለጸ ሲሆን፤ በእግር ኳስ ያጋጠመውን ውጤት ማጣት ለመፍታት በሂደት ሥራዎች እንደሚሰሩ እና የሥራ አሰፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ እንደሚደረግ እንዲሁም፤ ትውልድ ኢትዮጵያዊያን የመጫወት ሕጋዊ ፍቃድ መስጠት እና Road to 2029 በሚል የተጀመሩ ሥራዎች እንደማሳያ መነሳታቸው ይታወሳል።

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በበኩላቸው፤ ተጫዋቾቹ በሜዳ ላይ የሚችሉትን ሁሉ ማድረጋቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ለወጣቶች ዕድል መስጠት እንደሚያስፈልግ እንዲሁም ቡድን ግንባታ ጊዜ እንደሚፈልግ ተናግረዋል። በተጨማሪም ለተመዘገበው አሁናዊ የውጤት መጥፋት ብዙ አካላት የራሳቸውን ድርሻ ቢወስዱም፤ በዋነኝነት ለተመዘገበዉ ውጤት ማጣት ሃላፊነቱን እንደሚወስዱ ማብራራታቸው አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ከስር መሰረቱ መቀየር፣ ክለቦችም ለተጨዋች ግዢ እያሉ የመንግስትና የማህበረሰብ ሃብት ዘርፈው ከሚያዘርፉ፣ በሚፈሰው ሃብት ሰፊ የታዳጊ ወጣቶች መርሃ ግብር በመላው አገሪቱ መዘርጋት እንደሚሻል በርካቶች ይናገራሉ። ሰሚ ጠፍቶ እንጂ አሁን በተያዘው የኢትዮጵያ እግር ኳስ አካሄድ እስከመቼውም ውጤት ሊመጣ ስለማይችል መንግስት ያለአግባብ የሚዘረፈው ሃብት ላይ ጠንካራ መመሪያ ሊያወጣ እንደሚገባ የሚከሩ ጥቂት አይደሉም። ኮሚቴዎችና የመንግስት ተቋማት፣ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሮች ተቧድነው በዘረፋ የራሳቸውን ጥቅም በደላላና በኮሚሽን ከማሳደድ ውጪ ለእገር ኳሱ እድገት ምንም ደንታ እንደሌላቸው የሚናገሩ መንግስት መላ እንዲላቸው በተደጋጋሚ ይወተውታሉ።

በወልደሐዋርያት ዘነበ

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...