ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፈጦ ይውጣ እንጂ በተያዩ የዕምነት ደጆች ስርቆት ዋናው ሐዋሪያዊ ተለዕኮ መስሏል። ሙሉ በሙሉ ማለት ባይቻልም “መልካም” የሚባሉትን ያጨለመውና እያጨለመው የመጣው የዕምነት ደጆች ውስጥ ያለ ውንብድና ” ፈጣሪ እንደ ስራቸው ይከፍላቸዋል” እየተባለ የሚታለፍበትን ገደብ ያለፈ ይመስለኛል። በሁሉም አቅጣጫና የዕምነት ደጆች “ገንዘብ ወይም ሞት” ያሉና ለራሳቸው የከበረ ስም አጎናጽፈው፣ ቡድን አደራጅተው ድራማ የሚሰሩትን ” ተገልጋዮች”፣ በማህበራዊ ሚዲያ ጭፍሮቻቸው ተዓምራትን በስፋት እያሰራጩ የሚቆምሩትን ሁሉንም በዚህ ጽሁፍ ማንሳት ባልችልም ያሳደገችኝን ቤተክርስቲያኔን እየበላ ያለውንና እኔ ” ጥቁሩ ሲኖዶስ” ስላልኩት ክፍል በተከታታይ አካፍላለ፡፡ ሌሎችም በተመሳሳይ ያለ ሃፍረት ለዕመት ቤታቸው ቅናት አድሮባቸው በጨዋነትና በጥንቃቄ በዚሁ ጉዳይ ላይ የበኩላቸውን እንዲሉ እጋብዛለሁ፤
ዛሬ በፖለቲካው መድረክና በዝርፊያ ሃብት የሰበሰቡ የሚቀልቡት ሚዲያ እንዳላቸው ይታወቃል። ሚዲያ ማደረጃት ለመልካም ተግባር ከሆነ የሚመሰገን ተግባር ስለመሆኑ ጥርጥር ባይኖረውም ዛሬ በአገራችን በብዛት ሚዲያዎች ዓላማቸውን ስተው ሲያስቱ እየታየ ነው። ታዋቂ የስፖርት ሰዎች ሳይቀር ሚዲያ እየቀለቡ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ራሳቸውን የሚዲያ ባለቤት አድርገው መረጃ በሚያቀብሏቸው አማካይነት የሚደራደሩ፣ በኮሚሽን የሚሰሩ ጥቂት አይደሉም። እነዚህ ዓይነቶቹ ሚዲያዎችም በተከታታይ በማቀርበው ጽሁፌ የሚዳሰሱ ይሆናሉ።
በለካስዋ ቦካሳ
ሃይማኖት የሰው ልጅ በምድር ላይ እንዳለበት ዘመን ሁሉን አቀፍ ክስተት ነው። ሃይማኖት ለግለሰቦችና ለኅብረተሰቦች የሚያከናውናቸው በርካታ ተግባራት ስላሉት ለሰው ልጅ ሕይወት አስፈላጊ ነው።ከተለያዩ የትምህርት ዘርፎች የተውጣጡ ምሁራን ስለ ሃይማኖት የራሳቸው ፍቺዎች እና አመለካከቶች አሏቸው፤ ስለዚህ ሃይማኖት ለሶሺዮሎጂስት አንድ ነገር ሲሆን ለሥነ ልቦና ባለሙያ፣ ለአንትሮፖሎጂስት፣ ለፍልስፍና ባለሙያ እና ለሥነ መለኮት ባለሙያ ደግሞ ሌላ ነገር ነው።ካርል ማርክስ “ሃይማኖት የብዙኃኑ መነፅር ነው” ብሏል።
ነገር ግን በሁሉም ምሁራን ዘንድ በማህበራዊ ባህሪ እና በሰው ልጅ መስተጋብር ላይ ጠንካራ ተጽዕኖ የሚያሳድር ኃይል እንደሆነ እንዲሁም የሕዝቡን ባህል ለማጠናከር ጠንካራ መሠረት እንደሚጥል ይስማማል፣ ይህ ደግሞ በአገሪቱ ውስጥ ባሉ የተለያዩ የጎሳ ቡድኖች መካከል ባሉ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ልማዶች ውስጥ ይንጸባረቃል።
የሐይማኖት ተቋማት ሃይማኖት በማኅበረሰቡ ውስጥ ለሚኖረው የማይተካ ሚና መዋቅራዊ ወይንም ተቋማዊ መገለጫዎች ናቸው ፡፡ አንዳን ጊዜ ግን ወፍጮ ቤት የገባ ዱቄት ሳይነካው አይወጣም እደሚባለው የሃይማኖት ተቋማት በማኅበረቡ ውስጥ ለሚታዩ ማኅበረሰባዊ ውልቃቶች ሰለባ ሆነው ይታያሉ፡፡
” Pope Francis and the Vatican Deep State” በሚል ሆሊ ሲ ተብሎ በሚታወቀውና በሊቀ ጳጳሱ በሚመራው የሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማዕከላዊ መንግስት የአሜሪካ አምባሳደር በሆነችው በሜሪ አን ግሌንደን የተጻፈውን አርቲክል ለዓይን መግለጫ ያህል እንመልከት ….. ጽሑፉ እዲህ ብሎ ይጀምራል ….
… በብዙ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ለሚያንቀሳቅሰው ለዚህ መስሪያ ቤት ቅድመ ኦዲት የሚባል ነገር ጨርሶ አይታወቅም፡፡ ድህረ ኦዲትም የሚሰራው ቀደም ሲል በነበረው ክፍል እንደተገለጸው ጨርሶ ስለ ሂሳብ ምርመራ የተለየ ሞያ በሌላቸው እና የሂሳብ ምርመራ ዓላማን ባልተረዱ የቤተክህነቱ አባላት …
“ካርዲናል ጆርጅ ቤርጎግሊዮ በመጋቢት 2013 ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ፣ እንደ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ “ከዳርቻው” ብለው ከሚጠሩት ነገር የመጡ መሆናቸው ተስፋ ሰጪ ይመስል ነበር። መመረጣቸው ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆኑት ካቶሊኮች በእስያ፣ በአፍሪካ እና በላቲን አሜሪካ በሚኖሩበት ዓለም ውስጥ የቤተክርስቲያኗን ሁለንተናዊነት የሚያሳይ ነበር።ይህም ትልቅ ተሃድሶ የሚያስፈልገውን ቢሮክራሲ ለመቆጣጠር ትክክለኛው ሰው ይመስሉ ነበር።
የተለያዩ የቅድስት መንበር ክፍሎች በጆን ጳውሎስ ዳግማዊ እና በቤኔዲክት 16ኛ የጵጵስና ዘመን ብዙም ቁጥጥር ሳይደረግባቸው ይሠሩ ነበር። የአስተዳደራቸው ዘዴ የቫቲካንን ውስጣዊ ጉዳዮች ሙሉ በሙሉ በታማኝ የበታች ሰዎች እጅ ውስጥ መተው ነበር። አንዳንድ ጊዜ በእነዚያ የበታች ሰዎች ላይ የተጣለው እምነት ጥሩ ነበር፣ ነገር ግን እንደ አሮጌው አባባል “ድመቷ ስትሄድ አይጦቹ ይጫወታሉ።” በዚህ ወቅት አንዳንድ የመምሪያ ክፍሎች ትናንሽ የሥልጣን መወሰኛ ቦታዎች ሆኑ ዋነኛው ደግሞ የፋይናንስ ዘርፍ ነበር፡፡
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በ2013 ስልጣን ሲይዙ፣ ወዲያውኑ በሃይማኖታዊ ስራዎች ተቋም (በተለምዶ ቫቲካን ባንክ በመባል የሚታወቀው) ውስጥ አዲስ ጉዳይ ገጠማቸው ፡፡ አዲሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወዲያውኑ ችግሩን የሚፈታተን ተቋምን ለመመርመር ኮሚሽን (እኔ ያገለገልኩበት) መሾማቸው አበረታች ነበር። ኮሚቴው ምንም እንኳን ሁሉንም መዝገቦች ለመመርመር እና ማንኛውንም ሰው ለመጠየቅ ሙሉ ስልጣን ቢኖረውም፣ በባንክ ባለስልጣናት በእያንዳንዱ ዙር በድንጋጤ ተገርፈን ነበር። ምን እየተከናወነ እንዳለ ለመረዳት፣ እኔ እና ሌላ ኮሚሽነር ከባንኩ 115 ሠራተኞች መካከል እያንዳንዱን ቃለ መጠይቅ አድርገናል፣ ነገር ግን ሊቀ ጳጳሱ ራሳቸው በግልጽ ለመናገር ያላቸውን ፍርሃት ማሸነፍ እንደማይችሉ ተገነዘብን።
በመሆኑም ከፍተኛ የገንዛብ መጠን ብክነት ከመታየቱም በላይ በአጋጣሚው ለመክበር ለተዘጋጁ ሁሉ ብቸኛው መንገድ ሆኖላቸዋል፡፡ እግዲህ የዚህ “የጨለማው ሲኖዶስ ” ዋነኛ ትኩረቶቹ የሰው ኃይል ምደባን እና የገንዘብ ፍሰትን አስመልክቶ በሚነሱ ዋነኛ ጉዳዮች ይሆናሉ ማለት ነው ፡፡
ከጥቂት ወራት በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ካርዲናል ጆርጅ ፔልን መላውን የፋይናንስ ሥርዓት ለማሻሻል ሲመጡ፣ የመጀመሪያ እርምጃዎቻቸው አንዱ የተከበረ የውጭ ኦዲተር መቅጠር ነበር። ኦዲተሩ ሊቤሮ ሚሎን (በወቅቱ የቫቲካንን ሀብት በብዛት የሚቆጣጠረውን) ኃያል የመንግሥት ሴክሬታሪያት ፋይናንስ መመርመር እንደጀመረ፣ ወዲያውኑ በካርዲናል ጆቫኒ ቤቺዩ ከሥራ ተባረሩ፤ከዚያ በኋላ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የውስጥ ተሃድሶ ሀሳቦችን በአብዛኛው ትተው ትኩረታቸውን ወደ ውጭ አዞሩ። “ ትለናለች፡፡
የሜሪ አለን ግሌንደንን ጽሑፍ በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ከእውነት በተቃራኒ የሚሰሩ አሰራሮች እዳሉ ይህም የቤተክርስትያኒቱ ውሳኔ ሰጪ አካል ትይዩ ይህን ውሳኔ የሚቀለብስ ከዚሁ ከቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር የተቆረሰ ቡድን እንዳለ የሚያሳይ ነው ፡፡
ደረጄ ተክሌ ወልደማርያም በተመሳሳይ የድርጊት አወቃቀር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚፈጸመውን የመዋቅር ስብራት “460 ቀናት በመንበረ ፓትርያርክ ” በሚል መጽሐፍ ውስጥ ሜሪ አለን ግሌንደን ” the Vatican Deep State” በሚል የገለጠችውን እረሱ “የጨለማው ሲኖዶስ ” በሚል አስቀምጦታል ፡፡ማንነታቸውንም ሲናገር
” አባላቱ በቅርብ ዝምድና የሚታወቁ፤ ታማኝነታቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች ያረጋገጡ እና አንዲት ብርቱ ሴት በአባልነት የሚገኙበት ቡድን ነው፡፡ በምሽት በዋናው እልፍኝ እየተገኘ ማንኛውም ወገን ቀድሞ የተወሰነን ጉዳይም ሆነ ሊወሰን የተቃረበን ጉዳይ በማስመልከት እንዲሁም ከተለያዩ ቦታዎች የተሰበሰቡ መረጃዎች ላይ ግምገማ ያካሂዳል፡፡ ውሳኔም ያሰጣል፡፡ የቡድኑ ዋና ዓላማ በቡድኑ እይታ ለጠቅላይ ቤተክህነቱ ይጠቅማሉ በሚላቸው ጉዳዮች ላይ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ደብሮችንም ጨምሮ/ የሰው ኃይል ምደባን እና የገንዘብ ፍሰትን አስመልክቶ በሚነሱ ዋነኛ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ማሰጠት እና ይህንኑም እስከ ታች አካላት ድረስ በሚገኘው ሰንሰለቱ አማካይነት የቅርብ ክትትል በማድረግ በተግባር ማስተርጎም ናቸው፡፡ ለዚህም ነው ቀን በብርሃን ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች ማምሻውን ተገልብጠው በነጋታው በአዲስ መልክ ብቅ የሚሉት፡፡ የዚህ ቡድን አባላት ከመደበኛ ደሞዝ ባሸገር የሌሎች ጥቅሞች ተጋሪዎች ናቸው ፡፡ “ በሚል አስቀምጦታል ፡፡
ከላይ ከተቀመጡት የቡድኑ ተግባራት መካከል “የገንዘብ ፍሰት ” በተመለከተ ያለው ሥራን ያለውን ስንመለከት እንደሚታወቀው የቤተክርስቲያኒቱ ገቢ ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ዋነኞቹ ግን የየአጥብያ ቤተክርስቲያናቱ ሰበካ ጉባዔ አባላት ወርሃዊ መዋጮ፤ ከቤተክህነት ቤቶች ኪራይ፤ ከቤተክርስቲያናቱ በደረሰኝ ከሚሰበሰብ የአገልግሎት ክፍያ፤ በየቤተክርስቲያናቱ እና አድባራቱ ንግስ በዓላት ወቅት ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገር የሚሰበሰብ የስዕለት ገንዘብ እና ከአንዳንድ በጎ አድራጊዎች የሚገኝ የእርዳታ ገንዘብ ሲሆን ከሁሉም በላይ ግን በስውርም ሆነ በግልጽ በሙዳየ ምጽዋት የሚሰበሰብ የሕዝበ ክርስቲያኑ የገንዘብ እና የከበሩ እቃዎች ስጦታ ይገኙበታል፡፡
ይህ በየአድባራቱ በሙዳየ ምጽዋት የሚሰበሰብ ገንዘብ የሚቆጠረው እና የሚመዘገበው በደብሩ ኃላፊዎች ከሀገረ ስብከት በተወከለ ተጠሪዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አባላት ባሉበት ሲሆን ተከፍቶ ከተቆጠረ እና ከተመዘገበ በኋላ ቤተክርስቲያናቱ ለደሞዝ እና መሰል አስተዳደራዊ ስራዎች የሚሆነውን አስቀርተው በመቶኛ በማስላት ለሚጠሩበት አህጉረ ስብከት የተመደበውን እንዲስው ሲደረግ አህጉረ ስብከቱም ከደረሳቸው ገንዘብ ላይ የየራሳቸውን ወጪ አስቀርተው ሌላ መቶኛ ካወጡለት በኋላ የጠቅላይ ቤተክህነቱን ድርሻ ወደላይ ያስተላልፋሉ፡፡ በመሆኑም ጠቅላይ ቤተክህነቱ በመቶኛ የተሰላ ድርሻውን ከየአህጉረ ስብከቱ እየተከታተለ በመቀበል ከሌሎች ገቢዎቹ ጋር ጨምሮ ደሞዝና ሌሎች ወጪዎቹን ይሽፍናል፡፡
… ከፍተኛ የገንዛብ መጠን ብክነት ከመታየቱም በላይ በአጋጣሚው ለመክበር ለተዘጋጁ ሁሉ ብቸኛው መንገድ ሆኖላቸዋል፡፡ እግዲህ የዚህ “የጨለማው ሲኖዶስ ” ዋነኛ ትኩረቶቹ የሰው ኃይል ምደባን እና የገንዘብ ፍሰትን አስመልክቶ በሚነሱ ዋነኛ ጉዳዮች ይሆናሉ ማለት ነው…
በብዙ ሚሊዮን ብር የሚቆጠር ገንዘብ ለሚያንቀሳቅሰው ለዚህ መስሪያ ቤት ቅድመ ኦዲት የሚባል ነገር ጨርሶ አይታወቅም፡፡ ድህረ ኦዲትም የሚሰራው ቀደም ሲል በነበረው ክፍል እንደተገለጸው ጨርሶ ስለ ሂሳብ ምርመራ የተለየ ሞያ በሌላቸው እና የሂሳብ ምርመራ ዓላማን ባልተረዱ የቤተክህነቱ አባላት ነው፡፡ በመሆኑም ከፍተኛ የገንዛብ መጠን ብክነት ከመታየቱም በላይ በአጋጣሚው ለመክበር ለተዘጋጁ ሁሉ ብቸኛው መንገድ ሆኖላቸዋል፡፡ እግዲህ የዚህ “የጨለማው ሲኖዶስ ” ዋነኛ ትኩረቶቹ የሰው ኃይል ምደባን እና የገንዘብ ፍሰትን አስመልክቶ በሚነሱ ዋነኛ ጉዳዮች ይሆናሉ ማለት ነው ፡፡
ይህም በገንዘብ የከበሩ ከቤተክርስቲያኗ አቅም በላይ የሆኑ ግለሰቦች እየበረከቱ ይመጣሉ .. ለዚህም አንዱ ማሳያ የቁልቢ ደብረኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ጉዳይ ነው፡፡ ነገሩ የተፈጸመው የዛሬ አራት ዓመት በ2013 ዓ.ም ሲሆን ከመንበረ ፓትሪያሪክ ጽ/ቤት በደብዳቤ ቁጥር 1/115520/2013 የመጣው ደብዳቤ ይዘት የሚያሳየው በወቅቱ የገዳሙ አስተዳዳሪ የነበሩት በገዳሙ ለተፈጸመ የሥራ በደል ሁለት ጊዜ ቀርበው ሪፖርት እንዲያቀርቡ በማለት ደብዳቤ ቢደርሳቸውም እንዳልተገኙ የሚያትት ሲሆን የተፈጸመው የሥራ በደልን በተመለከተ የቤተክርስቲያኒቱን ንብረት በመመበዝበር ዋነኛው ጉዳይ ሲሆን በወቅቱ ቤተክርስቲያኒቱ የወሰደችው የመጀመሪያ እርምጃ ማንኛውንም በገዳሙ የሚገኝ ንብረት ሆነ የሂሳብ አካውንት እንዳያንቀሳቅሱ የሚያግድ ደብዳቤ በቀን 18/06/2013 እና በቁጥር 1/11545/2013 ተጽፎ ለሚመለከተው አካል መላክን ነበር ፡፡
ሜሪ አለንም ደረጀ ተክሌም የሚስማሙበት ነገር ቢኖር እንዲህ ዓይነት የቤተክርስቲያን ስር የሰደደ መዋቅራዊ “ሽፍታነት” በሚያመልኩትም በሚያስመልኩትም ምዕመን ዘንድ ጸያፍ ከመሆኑም ባሻገር የቤተክርስቲያኒቱን ተልዕኮ ከመገዳደር አልፎ ለሁከት እና ብጥብጥ መንስኤ መሆኑ አይቀርም ፡፡ የክርስቶስ ተምሳሌት የሆነቸውን ቤተ ክርስቲያንንም… ይቀጥላል …..
ዝግጅት ክፍሉ / ይሕ ጽሁፍ የዝግጅት ክፍሉ አቋም አይደለም። ጽሁፉ የጸሐፊው አስተያየት ብቻ ሲሆን ምላሽ ወይም ተቃውሞ ላላቸው ሁሉ መደረኩ ክፍት ነው
foto credit tp TRIB media
#ይከታተሉን #ይጎብኙን #ሃሳብ_አስተያየትዎን_ይላኩልን
ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ 0981866434





