የትግራይ ሰላም ሃይል የተሰነዘረብኝን ጥቃት መከትኩ አለ፤ በመቶ የሚቆጠሩ ከዱ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – አሁን ላይ ከኤርትራ መንግስት ጋር ግንባር የመሰረተው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር/ ትህነግ በሶስት አቅጣጫዎች ከፍቶት የነበረውን ጥቃት መመመከቱን የትግራይ ሰላም ሃይል አስታወቀ። ለትግራይ ሰላም ሲባል ታጣቂዎች የሰላም ኃይሉን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀርቧል። ከተለየዩ የአርሚ ምድቦች ግምታቸው ሁለት መቶ አርባ የሚሆን ተዋጊዎች ትህነግን ከድተው የትግራይ ሰላም ሃይል ጦርን መቀላቀላቸው ተሰምቷል።

ራሱን የትግራይ ሰላም ሃይል ብሎ የሚጠራው ወገን ዕሁድ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “ቆሞ ቀሩ፣ የኋላቀር ስብስብ የህወሓት ቡድን በራያ እና በዓዘቦ ጥቃት ሰንዝሮብናል፤ ለሰላም ስንል ከመሃል ትግራይ ርቆ እንዲሰፍር ባደረገነው ሰራዊታችን ላይ ጥቃት ፈጽሟል” ሲል ከሷል። መግለጫው “ኋላ ቀር” ያለው በእነ ዶክተር ደብረጽዮን የሚመራውንና ከሻዕቢያ መመሪያ በመቀበል ትግራይን የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየሰራ ያለውን ቡድን መሆኑንን በተደጋጋሚ ማስታወቁ አይዘነጋም።

“የትግራይ ሰላም ሃይል የመረጃና ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ የተሰጠ መግለጫ” በሚል በትግርኛ የተሰራጨው መረጃ እንዳለው ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም የትግራይን ጊዜያዊ መንግስት በኃይል ያስወገደው ቡድን ውጊያ ከፍቷል። መግለጫው የታጠቀ ኋላ ቀር ቡድን በራያ አዘቦ እና በዋጅራት ጥቃት ቢሰነዘርበትም ለትግራይ ሕዝብ ሰላም ሲል እንደ ሌሎች ጊዜያት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቦ ትንኮሳውን በጥበብ ማለፉን አስታውቋል።

” ሰራዊታችን ላይ በተደጋጋሚ እይደረሰ ያለውን ትንኮሳ በትዕግስት እያለፍነው እንገኛለን ። ቆሞ ቀሩ ቡድን በሻዕቢያ እየታገዘ የትግራይ ልጆች እርስ በርስ እንዲጫፋጨፉ በትጋት እየሰራ ነው ።
እንደ ከዚህ ቀደሙ አሁንም ከዚህ መሰል ትንኮሳው እዲቆጠብ እጥብቀን እናሳስባለን” ያለው የትግራይ ሰላም ኃይሎች መግለጫ፣ ” እስካ እሁን ድረስ ሲውርድብን ለነብሩ ጥቃቶች እና ትንኮሳዎች ለትግራይ ሕዝብ ሰላም ስንል መልስ ከመስጠት ተቆጥበን ቆይተናል። ይህ ግን በጥፉት ሃይሉ እንደፍራቻ የሚታይ ሆናል ።በመሆኑም ከአሁን በኋላ ለሚፈጸምብን ማንኛው ጥቃት ተገቢውን ምላሽ የምንሰጥ መሆኒን እናሳውቃለን” ሲል አስጠንቅቋል።

” ከጦርነቱ ውጭ ለመኖር ፈቃደኛ ያልሆነው ፀረ ሰላም ቡድን የከፈተውን ጥቃት ያወገዘው መግለጫው፣ ” በግዴታ አሊያም ተታላቹህ ከቡድኑ ጋር የምትገኙ ወጣቶች በእዚህ ቆሞ ቀሩ ቡድን ከተደገሰላቹ የሞት ድግስ ራሳቹን እንድታድኑ ኣናሳስባለን” ሲል ምክርና ማሳሰቢያ አቅርቧል።

የትግራይ የሰላም ኃይሎች ጥቃቱ “የሻዕቢያ ፈረሶች” ሲል የሚጠራቸው የእነ ዶክተር ደብረጽዮን አንድ የትህነግ ክፋይ፣ በሻዕቢያ ትዕዛዝ የትግራይን ህዝብ አንድነትና ለማዳከም፣ አቅሙን ለማላላትና መሳለቂያቸው ለማድረ ያቀዱት የጥፋት ወጥመድ እንደሆነ አመልክቷል።

የትግራይ ህዝብ የሚፈልገውና የሚገባው ሰላም ብቻ እንደሆነ ያመለከተው የትግራይ ሰላም ኃይሎች መግለጫ፣ በዚህ ያለ ጦርነት መኖር በማይችለው ቡድን ውስጥ ያሉ ታጣቂዎች በእነሱ ቁጥጥር ስር ወደሚገኙ አካባቢዎች በመሄድ የሰላም ኃይሉን እንዲቀላልቀሉ አበረታቷል።

ይህ በንዲህ እንዳለ በዛሬው ዕለት ከትንኮሳው በፊት ይሁን በሁዋላ ባይገልጽም አርሚ 33፣ 43 እና 44 የተውጣጡ 240 የሚልቁ ተዋጊዎች ወደ ሀራ መሬት በማምራት በማምራት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ኃይል መቀላቀላቸው የተለያዩ ሚዲያዎች ምስል አስደግፈው አስታውቀዋል።

#ይከታተሉን #ይጎብኙን #ሃሳብ_አስተያየትዎን_ይላኩልን

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/

ኢሜል፡ info@addisreporter.com

ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11

X፡ https://x.com/addisreporter

ስልክ ቁጥር፡ 0981866434

በእኛ ላይ በተደጋጋሚ እይደረሰ ያለውን ትንኮሳ በትዕግስት እያለፍነው እነገኛለን ። ቆሞ ቀሩ ቡድን በሻዕቢያ እየታገዘ የትግራይ ልጆች እርስ በርስ እንዲጫፋጨፉ በትጋት እየሰራ ነው ።
እንደእዚህ ቀደሙ ኣሁንም ከእዚህ ትንኮሳው እዲቆጠብ እጥብቀን እናሳስባለን። እስካ እሁን ድረስ ሲውርድብን ለነብሩ ጥቃቶች እና ትንኮሳዎች ለትግራይ ሕዝብ ሰላም ስንል መልስ ከመስጠት ተቆጥበን ቆይተናል። ይህ ግን በጥፉት ሃይሉ እንደፍራቻ የሚታይ ሆናል ።በመሆኑም ከኣሁን ብሓላ ለሚፈጸምብን ማንኛው ጥቃት ተገቢውን ምላሽ የምንሰጥ መሆኒን እናሳውቃለን ። በተጨማሪም በግዴታ ኣሊያም ተታላቹ ከቡድኑ ጋር የምትገኙ ወጣቶች በእዚህ ቆሞ ቀሩ ቡድን ከተደገሰላቹ የሞት ድግስ ራሳቹን እንድታድኑ ኣናሳስባለን።

የትግራይ ህዝብ ሃይል
trigay peoplele froce

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...