በአርሲ “ተፈጸመ” የተባለው ግድያ ሪፖርት ይፋ ይሆናል፤ “ግድያውን ለራሳቸው ዓላማ ይጠቀሙበታል” የተባሉት አልተደሰቱም

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን የተፈጸመውን ግድያ የሚያጣራ ገለልተኛ ኮሚቴ ሰይሞ ወደ ስፍራው ማሰማራቱ የሚታወስ ነው። በዚህ መሰረት ኮሚቴው የደረሰበትን የመጀመሪያ ደረጃ ወይም ቅድመ ሪፖርት በነገው ዕለት ይፋ እንደሚያደርግ ታውቋል። ዜናው ግድያውን ለራሳቸው አጀንዳ ግብአት እያደረጉት ባሉት ቡድኖች ዘንዳ ከወዲሁ አልተወደደም።

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ጉባዔ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ተፈጸሙ የተባሉ ግድያዎችን ለማጣራ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተወከሉበት አንድ አጣሪ ኮሚቴ በአስቸኳይ በማቋቋም ጥቅምት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ተጠቀሱት አካባቢዎች ማሰማራቱን ሲያስታውቅ በተቻለ ፍጥነት የተደረሰበትን ግኝት እንደሚያስታውቅ አመልክቶ ነበር። ጉባዔው ይህን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ግድያውን በመሰላቸውና ለራሳቸው አጀንዳ በሚያመች መንገድ ሲጠቀሙ የነበሩ ወያው ተቃውሞ አሰምተው ነበር።

አዲስ ሪፖርተር በኢትዮጵያ ነብሰ ገዳዮችን ለምን ኃላፊነት አይወስዱም?” የንጹሃን ግድያ በፖለቲካ እየተሰላ እስከመቼ?በሚል ርዕስ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን በማነጋገር፣ በግድያው ዙሪያ መግለጫና ውግዘት የሚያወሩ ቡድኖች “ስለምን ገዳዮችን በስም መጥራት ይፈራሉ” በሚል አነጋጋሮ ሰፊ ሪፖርት ማቅረቡ አይዘነጋም።

አስተያየት እንዲሰጡ ከተጠየቁት መካከል ከኦፌኮ በስተቀር የተቀሩት ምላሽ የሰጡት በቁጣ ነበር፡፡ ” ለምን ይህን ጥያቄ እንጥርይርቃለን” ያሉም ነበሩ። የኃይማኖት ጉባኤው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን እንደሚያቀርብ መግለጹን አስመልክቶ በተመሳሳይ ካነጋገርናቸው መካከል አብዛኞቹ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ከፍተኛ አመራር “ኢትዮጵያ ሰላም እንድትሆን ያማይፍለጉ የንጽሃንን ሞት ለግል አጀንዳቸው ማገዶነት ስለሚጠቀሙበት ፍትህን የማስፈንና ገዳዮችን የማጋለጡ ስራ ብዙም አይፈለግም። እንደውም የሰላም ፍንጭ ሲታይ ተቃውሞ ይነሳል” በማለት ባለፈው ሳምንት ለሪፖርተር ተናግረው ነበር።

የኢትዮጵያ ኃይማኖት ጉባኤ ዜናው እንደተሰማ ይሰራጩ የነበሩ መረጃዎችን ሳይዘረዝር ” ይህ ተግባር የማጣራቱን ሂደት የሚጎዳ እና አንዳንድ አካላትን ወደ ተሳሳተ ድምዳሜ ሊወስድ የሚችል ተግባር በመሆኑ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃ የምታሰራጩ አካላት በሙሉ ከፍ ያለ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን ” ብሎ ነበር። በተመሳሳይ ከኃይማኖት ጋር የሚያያዝ ጉዳይ አደጋው ሰፊ በመሆኑ ሳይጣራ ኃላፊነት የጎደለው መግለጫና አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ያሳሰቡ ” ከጥንቃቄ ጉድለት ለጠላት መጠቀሚያ እንዳንሆን” በሚል ሲያሳስቡም ነበር።

” የልዑካን ቡድኑ የማጣራት ሥራውን ጨርሶ የመጨረሻ ሪፖርቱን ሲያቀርብ በጉዳዩ ላይ በጉባኤችን በኩል ይፋዊ መግለጫ እና ማብራርያ የሚሰጥ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ በትዕግስት የማጠቃለያ ሪፖርቱን እንዲጠብቅ ጉባኤችን በአክብሮት ይጠይቃል ” በማለት ስጋቱን በማሳሰቢያ አስታኮ አቅርቦ ነበር።

ቃል በገባው መሰረት የኢትዮጵያ ኃይማኖት ጉባኤው ለመገናኛ ብዙኃን ባሰራጨው የጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ መሰረት የልዑካን ቡድኑ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱን ነገ ይፋ ይደረጋል። በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና ሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች መሆናቸው የተገለጸ ሰዎች መገደላቸውን ቤተ ክርስቲያን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የእስልማና ጉባኤ እና በርካታ በሁኔታው ያዘኑ ማውገዛቸው አይዘነጋም።

የኢትዮጵይ እስልምና ጉባኤም ቁጥራቸውን አይገልጸ እንጂ ተከታዮቹ በተመሳሳይ ስፍራ “ያልታወቁ ታጣቂዎች” በተባሉ አካላት መገደላቸውን ማስታወቁ አይዘነጋም።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related