ኢትዮጵያ ከሃምሳ ሺህ በላይ የውጭ አገር እንግዶች የሚሳተፉበትን የተመድ የአየር ንብረት ጉብዔ ለማዘጋጀት ተመረጠች

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ኢትዮጵያ በየዓመቱ ከሃምሳ ሺህ በላይ ከውጭ የሚመጡ ተሳታፊዎች የሚሳተፉበትን የዓለም የአየር ፀባይ ለውጥ ጉባኤ እንድታዘጋጅ መመረጧ ይፋ ሆነ። ኢትዮጵያ ይህን ታላቅ የተባለ ዓለም ዓቀፍ ስብሰባ እንድታዘጋጅ መመረጧ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ትልቅ እንደሆነ ተመልክቷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የሚከናወነው በድርጅቱ ውስጥ ባሉ አምስት ቀጣናዎች በሚገኙ አገራት በመፈራረቅ ሲሆን የያዝነውን ዓመት ብራዚል የላቲን እና የካሪቢያን ሀገራት ወክላ በመመረጧ እያዘጋጀች ነው። ኢትዮጵያም ቀጣዩን ጉባኤ እንድታዘጋጅ የተመረጠችው ተበዚሁ ብራዚል በተዘጋጀው ኮፕ 30 ስብሰባ ላይ ናይጀሪያን አሸንፋ ነው። በስፍራው የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንዳሉት የአፍሪካ አገራት ለኢትዮጵያ ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ተደራዳሪዎች ቡድን ሊቀ መንበር ሪቻርድ ሙዩንጊ ቡድኑ ኢትዮጵያን የኮፕ 32 የማስተናገድ ጥያቄ ተቀብሎ ማጽደቁን ለኤኤፍፒ ማረጋገጣቸው ታውቋል። የኮፕ 30 ፕሬዝዳንት የሆነችው ብራዚልም የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያን መምረጣቸውን አረጋግጣለች። አውስትራሊያና ቱርክ 31ኛውን ጉባኤ ለማዘጋጀት እየተፎካከሩ ሲሆን ይህ እስከታተመ ድረስ ይፋ አልሆነም።

ጉቤው “ኮፕ” የሚለው ስያሜ ይጠራል ይህ ጉባኤ የዓላማችን ዋነኛውና ትልቁ የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ በተከታታይ ዓመታት ያካሄደችው የአረንጓዴ አሻራ የተፈጥሮ ክብካቤና የደን መልሶ ማልማት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ዕውቅና ማግኘቱ ጉባኤውን አፍሪካን በመወከል ለማዘጋጀት ተመራጭ እንዳደረጋት ታውቋል።

ኢትዮጵያ በዓለም ሪኮር አሻሽላ በተከታታይ ያከናወነችውን የደን ልማት በዘፈን፣ በግጥም፣ በተለያዩ መግለጫዎችና በማህበራዊ አውዶች ያለማቋረጥ ሲቃወሙ እንደነበር ይታወሳል። ከነዚሁ መርካከል አራት ለሚሆኑት አዲስ ሪፖርተር ዛሬ ላይ ምን አስተያየት እንዳላቸው ጠይቃ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን በዘፈን ከተቃወሙ መካከል በመሆኑ ለማነጋገር ሞክረን አልተሳካልንም። ቴዎድሮስ በችግኝ ተከላ ቀን ነበር የተቃውሞ ዘፈን ያሰማው።

ከአሜሪካ በስተቀር ሌሎች የዓለም አገራት እየተሳተፉበት ያለው ይህ ዓመታዊ ጉባኤ መካሄድ የጀመረው የዓለም ሙቀት መጨመር ስጋት እየሆነ መምጣቱን ተከትሎ በ1992 ነበር።

የጉባኤው ኢትዮጵያ ውስጥ መካሄድ የገባቸው ኤኤፍፒ ይህንኑ ዜና ባሰፈረበት ዘገባ ያለውም አንስተዋል። ሪፖርቱ እንዳለው ኢትዮጵያ የዚህ ታላቅ ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ አዘጋጅ ሆና መመረጧ፣ በጉባኤው አጀንዳም ሆነ በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ በሚወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ሚናዋ ከፍተኛ ይሆናል።

ኢትዮጵያ ስብሰባውን ለማስተናገድ በይፋ ጠይቃ ያሸነፈችበት የብራዚሉ ጉባኤ የተደራዳሪ ቡድኑ መደበኛ ያልሆነ ውሳኔ በሁሉም የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት መጽደቅ እንደሚጠበቅበት እና ይህም ኮፕ 30 በሚጠናቀቅበት ህዳር 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይፋ ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከስብሰባው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።

ባለፉት ዓመታት ዓለም በአደባባይ የመሰከረውና ለውጡ በአገር ውስጥ መታየት የጀምረው የአረንጓዴ አሻራ፣ ከታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች ግንባታዎች ጋር ተዳምሮ ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ በኩል በዓለም የምትጠቀስ አገር አድርጓታል።

ኢትዮጵያ ይህን ጉባዔ የማዘጋጀት ዕቅድ እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መናገራቸው አይዘነጋም። ስብሰባው ለተጀመረው የከታማ ቱሪዝም መስፋፋት ትልቅ ዕድል እንደሆነም ከወዲሁ እየተገለጸ ነው።

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...