በሰሜን ጎንደር ወላዶች ጤና ጣቢያ መሄድ አይችሉም፤ ” ፋኖ መንገድ ይዘጋል፤የጤና ባለሙያዎችንም ይጎዳል”

Date:

አዲስ ሪፖርተር- ” እናቶች የእርግዝና ሕክምና መከታተል ሳይችሉ ቀርተዋል። ብዙዎች በቤት ውስጥ ወልደዋል። ሕጻናት መሰረታዊና የሕይወት ዘመን አስገዳጅ ክትባት ሳያገኙ ቀርተዋል። የጤና ክብካቤ ከቶውንም የሚታሰብ አልሆነም። በዚህ ሳቢያ በወሊድ በቤታቸው ሕይወታቸው ያለፈ፣ በቤታቸው ከተገላለግሉ በኋላ ልጆቻቸውን ያጡ፣ በሽተኛ ሆነው የቀሩና የሚሰቃዩትን ቤቱ ይቁጥራቸው” ነው የሚሉት የአጋባቢው ነዋሪዎችና በተለያዩ ኃላፊነት ላይ ያሉ።

ይህ እየሆነ ያለው በሰሜን ጎንደር ዞን ከጃናሞራ፣ከበይዳና ከጠለምት ወደ ደባርቅ መንገድ እንዲዘጋ በማደረጉ ነው። ምክንያቱ ደግሞ ፋኖ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ ወይም እንዲስተጓጎል በማድረጉ የተነሳ ነው። ላለፍጉት ሁለት ዓመታት የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖር ከምንም በላይ ነፍሰጡር እናቶችን፣ ሕጻናትንና ቋሚ መደሃኒት በሚወስዱ ዜጎች ላይ እያሳደረ ያለው ችግር በቃላት የሚገለጽ አይደለም።

በሰሜን ጎንደር ዞን ላለፉት ሁለት ዓመታት በአከባቢው የሚንቀሳቀሰው ራሱን ፋኖ ብሎ የሚጠራው ኃይል የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ በማድረጉ ምክንያት ነፍሰ ጡር እናቶች ለወሊድ ፣ለሕክምና ክትትል ወደ ጤና ጣቢያ መሄድ እንዳልቻሉ ለአዲስ ሪፖርተር ያስረዳው የዞኑ ትራንስፖርት መምሪያ ነው።

“በአከባቢው በተፈጠረው የሰላም እጦት ሳቢያ በርካታ እናቶች የእርግዝና ሕክምና መከታተል አልቻሉም። በርካቶቹ የተገላገሉት በቤት ውስጥ ነው፤ በመከራና ስቃይ የተወለዱት ሕጻናት ክትባት አያገኙም። ይህ እስከመቼ ይቀጥላል? ምንስ እየሆነ ነው? በዚህ ደረጃ ወገን ላይ መጨከን ምን ምክኛት ይቀርበለታል?” ሲሉ ሃዘን የተቀላቀለበት መረጃ የሰጡት ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የመምሪያው ሰራተኛ ናቸው።

 በአካባቢው የተፈጠረው የሰላም እጦት እናቶች የቅድመ ወሊድ ክትትል ለማድረግ አስቸጋሪ አድርጎባቸው እንደነበር እኚሁ ስምቸውን በስጋት ምክክንያት መግለጽ ያልፈለጉት የመመሪያው ሰራተኛ ናቸው፡፡ “ዛሬ ውጊያ አለ፣ ዛሬ መንገድ ይዘጋል” ስለሚባል በስጋት የተነሳ እናቶች ተከታታይ ሕክምና ማድረግ እንደማይችሉ ገልጸዋል።

“ምጥ በሌሊት የሚመጣባቸው እናቶች ወደ ሕክምና ተቋማት አይሄዱም፡፡ በቤታቸው ይወልዳሉ፡፡ አምቡላንሶች እና ሌሎች ተሸከርካሪዎች በነጻነት አይሠሩም፡፡ እናቶችም ስጋት ስላለባቸው፣ ከምጡ ይልቅ ወደ ህክምና ሲሄዱ የሚገጥማቸው አደጋ ያስፈራቸዋል። ‘ሌላ የሚገድለን ነገር መንገድ ላይ ይጠብቀናል’ ስለሚሉ የደፈረ አሽከርካሪ ቢገኝ እንኳን በስጋት መጓጓዝ አይፍለጉም።” ሲሉ የችግሩን ግዝፈት ያስረዳሉ።

የችግሩን ስፋትና አሳሳቢነት ያስረዱት የመመሪያው ሰራተኛ በቀንም ሆነ በሌሊት የወሊድ ቀናቸው የደረሰ እናቶች በጤና ጣቢያ ልጃቸውን መገላገል እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡ ሁሉም በቤታቸው እድላቸውን ይሞክራሉ። እሳቸው እንዳሉት ነገሩ ሁሉ ልብ የሚነካ ነው።

“በሰላሙ ጊዜ የጤና ባለሙያዎቹም፣ ነብሰጡር እናትና ሕክምና ፈላጊዎች በሕክምና ስፍራ ለመገናኘት አሳብ የለባቸውም” ሲሉ የሰላሙን ወቅትና አሁን ያለውን ቀውስ ያነጻጸሩ የሕክምና ባለሙያ እንዳሉት፣ አሁን ላይ ሕክምና ፈላጊዎቹም፣ የሕክምና በላሙያዎችም በስጋት የተነሳ ግንኙነታቸው ታውኳል። ” አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች በፋኖ ታጣቂዎች አደጋ ይደርስባቸዋል። ስለዚህ ባለሙያዎቹ አገልግሎት መስጠት ይፈራሉ። ስራቸውን መስራት የሕይወት አደጋ ሆኖባቸዋል። እኔ ለምሳሌ በሰቀቀን ውስጥ ነኝ”

ባለሞያው አክለውም ፤ አሁንም በክልሉ በቀጠለው ግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው በዞኑ በሚገኙ ሦስት ወረዳዎች የአስፋልት መንገዶች ለሕዝብ አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ መንገዶቹም ከጃናሞራ ወደ ደባርቅ፣ ከበይዳ ወደ ደባርቅና ከጠለምት ወደ ደባርቅ ያሉት የአስፋልት መንገዶች መሆናቸውን ጠቁሟል።

“በተጠቀሱት አካባቢዎች በፋኖ አማካይነት ምንም ዓይነት የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዳይሰጥ ተደርጓል። ነፍሰጡር እናቶች ድንገተኛ የአምቡላንስ አገልግሎት እንዳይጠቀሙ ብይን ተላልፏል። እንዲሁም መድኃኒት፣ ምግብ ነክና ምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶችን ወደ ወረዳዎቹ ማስገባት አልተቻለም።” ሲሉ ባለኡያው ለአዲስ ሪፖርተር አመለክተዋል።

ከአማራ ክልል ሰፊ ቁጥር ያላቸው የሕክምና ባለሙያዎች እየለቀቁ መሆኑን ክልሉ በቀርቡ ማስታወቁ አይዘነጋም። በዚሁ የሕክምና ባለሙያዎች ፍልሰት ሳቢያ ሕዝቡ ከፍተኛ ችግር ላይ እንደወደቀ በተደጋጋሚ የሚገልጽ ጉዳይ ነው።

በተለያዩ አደረጃጀቶች ስራ ያለው ፋኖ እንዲህ መሰሉን ውሳኔ በመወሰን ሕዝብ የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኝ ሲያግድ፣ የጤና ባለሙያዎችን ሲቀጣና አምቡላንሶችና የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት እንዲስተጓጎል ሲያደርግ ምን ለማሳካት እንደሆነ በይፋ ሲያብራራ አይሰማም። ከፋንቦ የተለያዩ አደረጃጀቶች ጋር አብረው የሚሰሩ ሚዲያዎችም ባላቸው ግንኙነት ተጠቅመው ምክንያቱን ሲያስረዱ አይደመጥም። ይልቁኑም የመንገዱ መዘጋትና የአገልግሎቱ መቋረጥ “ሰበር ዜናቸው” ነው።

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...