ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ከማኅበራዊ ልማት ቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ተፈቀደ::

Date:

ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስና የደኅንነት ተቋማት የሚያስገቧቸው መሣሪያዎች ከማኅበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ ገንዘብ ሚኒስቴር መፍቀዱ ተገልጿል።

የቀረጥ ነፃ መብቱ የተፈቀደው የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ባወጣው መመሪያ ሲሆን፤ በመንግሥት ባለቤትነት ሥር ያሉ ወይም ለኅብረሰሰቡ ነፃ አገልግሎት ለሚሰጡ የትምህርት ተቋማት፣ ለጤና ተቋማት፣ ለሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን፣ የአዕምሮ ሕመምተኞችና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅቶች ከውጭአገር በዕርዳታ የሚላኩ ዕቃዎች ከማኅበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ሆነዋል፡፡ በተጨማሪም፣ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረስባቸው ወገኖች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ለሚሰጡ ድርጅቶች ከውጭ ሀገር በዕርዳታ የሚላኩ ዕቃዎች ከማኅበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ተደርዋል።

እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ተቋሞች፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎትና ኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር በሕግ በተፈቀደው መሠረት ወደ ሀገር የሚያስገቧቸዉ የመከላከያና የሕዝብ ደኅንነት መሣሪያዎች፣ ለነዚሁ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችናና አክሰሰሪዎችም በተመሳሳይ ከማኅበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ መወሰኑ ተዘግቧል።

ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ከቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው ወደ ሀገር እንዲገቡ የተፈቀዱ ዕቃዎች እንዲሁም በብሔራዊ ባንክ ወደ አገር የሚገቡ ሳንቲሞች፣ የገንዘብ ኖቶች እንዲሁም የብርና የወርቅ ጠገራዎች በተመሳሳይ ከማኅበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ ተደርገዋል።

ለኅብረተሰቡ በነፃ የሚሰጡ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እንዲሁም፤ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ችግር ላይ የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት ከውጭ አገር በዕርዳታ የሚላኩ ዕቃዎች ከማኅበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ መደረጋቸውን መመሪያው ያመለክታል።

በመመሪያው መሠረት ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተፈቀዱት ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ከቀረጥ ነፃ ሆነው ሊገቡ የሚችሉት፤ ዕቃዎቹ በዕርዳታ የተገኙ መሆኑን የሚያረጋግጥ የዕርዳታ የምስክር ወረቀት ሲቀርብ ነው ተብሏል፡፡

ለማኅበራዊ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ከማኅበራዊ ልማት ቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ ቢፈቀድም፤ ይህንን መሠረት በማድረግ ያልተገባ ጥቅም የመሰብሰብ ድርጊት እንዳይፈጠር የተወሰኑ ዕቃዎች የቀረጥ ነፃ መብቱ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ክልከላ ጥሏል።

ክልከላ የተጣለባቸው ዕቃዎች ተብለው በመመሪያው የተጠቀሱት፣ ከስምንት መቀመጫ በታች ያላቸው አውቶሞቢሎችና የእነዚህ መለዋወጫዎች፣ ባለአንድ ወይም ባለሁለት ጋቢና ፒካፕና የእነዚህ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች እንዲሁም ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችና መሣሪያዎች እንደሆኑ ዘገባው አመላክቷል፡፡

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...