“እስክንድ ነጋ አልታሰረም” እስክንድር “የሰላም ንግግር የጀመረው እሱ ነው” በሚል በዘመቻ ውግዘት እያስተናገደ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር – እስክንድር ነጋ መታሰሩን በመግለጽ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች የሚጽፉትና የሚያሰራጩት ዜና ስህተት መሆኑ ተሰማ። ለጊዜው የት እንደሚገኙ ከመግለጽ ተቆጥበው ከስክንድር ጋር አብረው እንደሚሰሩ የተናገሩ ለአዲስ ሪፖርተር እንዳሉት እስክንድ ባለበት ስፍራ ላይ ነው።

በምሬ የሚመራው ኃይል እንዳሰረውና ወደ የትም መሄድ እንደማይችል ተገልጾ መረጃ የሚሰራጨው በሰላም ድርድር ተስማምቶ ሊገባ ይችላል ከሚል ፍርሃቻ እንደሆነም ገልጸዋል። ሰላምን አስመልክቶ አሁን ላይ የተደረሰ ነገር ስለመኖሩ ዝርዝር አልተናገሩም።

ዜናውን ይበልጥ ለማስጥራት እስክንድርን ማናጋገር የሚቻልበት አግባብ እንዳለ ተጠይቀው “ለጊዜው አይሆንም” ብለዋል።

በርካታ በውጭ አገር ያሉ የቀድሞ የእስክንድር ወዳጆችና ተከታዮች ጭምር ሰሞኑን “ከሃዲ” በሚል እየዘለፉት ይገኛሉ። ከትናንት ጀምሮ “ምሬ አስሮታል” የሚል መረጃ እያወጡ ነው!! “ሰበር ዜና” በማለት “አቶ እስክንድር ነጋ እነ መከታው ማሞ በሚመሩት ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተብሎ በሚጠራው ኃይል ቁጥጥር ውስጥ መሆኑ ታወቀ” የሚል ዜና ካሰራጩት ቡድኖች ውጪ ዜናውን በድርጅት ደረጃ ወይም በሚታወቅ አካል ያረጋገጠ የለም።

“አቶ እስክድር ነጋ የበላይነት ሲደረግ በነበረው ድርድር መሰረት የተወሰኑ የአፋህድ ከፍተኛ አመራሮች ለአገዛዙ አምልጠው እጅ ሲሰጡ አቶ እስክንድር ነጋ ግን በእነ መከታው ማሞ በሚመሩት ኃይል የቁም እስር ላይ መሆኑ ታውቋል” የሚሉት ዜና አቅራቢዎች፣ በዛው ዜናቸው ላይ “እስክንድር ነጋ ማምለጥ በማይችልበት ደረጃ ላይ ነው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል” ሲሉ መታሰሩን ጥያቄ ውስጥ የሚከት መረጃ አክለዋል።

ለአዲስ ሪፖርተር መረጃ የሰጡት ሰው እንዳሉት ከሆነ የሚባለው ሁሉ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ የሚወጡ የስጋት ዜናዎች እንጂ፣ እውነታ የላቸውም። አዲስ ሪፖርተር በኮሎኔል ፋንታሁን ሙሃባ ከሚመሩት የፋኖ አካል ውስጥ ካሉት የመረጃ ምንጮች ለማረጋገጥ ሞክራ “መረጃ የለኝም” የሚል ምላሽ አግኝታለች፤ እነሱ “ተከበዋል” የሚባለውን ግን አፋቸውን ሞልተው አስተባብለዋል። የአገር መከላከያ ከከበባ እንዳስለቀቃቸው የመከላከያ ምንጮቻቸውን ጠቅሰው ስለዘገቡት እግረምነገዳቸውን ጠይቀናቸው “አሁን ባለንበት ቦታ ላይ አለን” ብ፤ለዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...