ያለ ኮላተራል (ማስያዣ) የሚሰጥ ብድር፡ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፋይዳ እና ስጋት

Date:

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በተደጋጋሚ የሚነሳው እና አከራካሪው ጉዳይ “ያለ ማስያዣ ብድር መስጠት” ነው። ይህ አሰራር ለአዳዲስ ፈጠራዎች እና ለጀማሪ ነጋዴዎች ወሳኝ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል የባንኮችን ህልውና እና የሀገርን ኢኮኖሚ አደጋ ላይ ሊጥል የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። የሚነሱ ሃሳቦችን መሰረት በማድረግ ነገሩን በሁለት ወገን እንመልከተው።

ያለ ማስያዣ የማበደር አደጋዎች

አንድ ባንክ ያለ ተመጣጣኝ ማስያዣ ብድር ሲሰጥ፣ ብድሩ በሚበላሽበት ጊዜ ገንዘቡን መልሶ የማግኘት እድሉ እጅግ ጠባብ ነው። ይህ ሂደት ተከታታይ የሆነ የኪሳራ ሰንሰለት ይፈጥራል፡-

የባንኮች መክሰር ተበዳሪው ሲከስር ባንኩም አብሮ ይከስራል። ባንኮች ከሰሩ ደግሞ መንግስት ጣልቃ ገብቶ እንዲደጉም ያስገድደዋል። ይህ በአሜሪካ በኦባማ ዘመን የነበረውን የፋይናንስ ቀውስ ያስታውሰናል። ኢትዮጵያ ደግሞ እንደ አሜሪካ ባንኮችን የመደጎም አቅም የላትም።

የተዓማኒነት መሸርሸር፡ ባንኮች እየከሰሩ ነው የሚል ወሬ ሲሰማ፣ ደንበኞች ገንዘባቸውን ለማውጣት ይሯሯጣሉ ። ማንም ሰው ከሚከስር ባንክ ጋር መስራት ስለማይፈልግ ገንዘቡን እያወጣ ባንኩን ይሸሸዋል።

የሙስና በር መከፈት  በተለይ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ብድሮች ያለ ማስያዣ ሲሰጡ፣ ለሙስና እና ለዘመድ አሰራር የተመቻቹ ይሆናሉ። ብድር የሚሰጠው በብቃት ሳይሆን በውል እና በግንኙነት ሊሆን ይችላል።

የነባሩ ስርዓት ችግር አለው

በአሁኑ ሰዓት ያለው የኢትዮጵያ የባንክ አሰራር እጅግ ጠንካራ እና “ሪጂድ” (Rigid) ነው። ብድር ለማግኘት የግድ ሀብት ሊኖርህ ይገባል።

  • የእንቁላል እና ዶሮ ታሪክ –  አንድ ወጣት አዋጭ የሆነ ቢዝነስ ሀሳብ ይዞ ቢመጣ፣ ባንኮች መኪና ወይም ቤት ማስያዣ ይጠይቁታል። ይህ ወጣት መኪና ወይም ቤት ቢኖረው ኖሮ፣ ያንኑ ሸጦ ወይም አከራይቶ ቢዝነሱን ይጀምር ነበር።
  • የድህነት አዙሪት –  ባንኮች “ላለው ሰው” ብቻ የሚያበድሩ ከሆነ፣ ድሃው በድህነት እንዲቀጥል፣ ሀብታሙ ደግሞ ይበልጥ እንዲከብር ያደርጋል። ይህ ስርዓት አዳዲስ ጀማሪዎችን ከጨዋታ ውጪ ያደርጋል።

መፍትሄው ምንድን ነው?

ችግሩን ለመፍታት ሚዛናዊ የሆነ አካሄድ ያስፈልጋል

ለአነስተኛ ብድሮች ልዩ ትኩረት መስጠት፡ ከ1 ሚሊዮን ብር በታች ላሉ፣ ለጀማሪ ቢዝነሶች የሚሆኑ ብድሮችን ያለ ግዙፍ ማስያዣ ማበደር ይቻላል። ለዚህም እንደ ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን አይነት ተቋማት ዋስ የሚሆኑበትን መንገድ ማጠናከር ያስፈልጋል።

ጥብቅ ቁጥጥር ያለ ማስያዣ የሚሰጡ ብድሮች ላይ የባንኮች ክትትል ጠንካራ መሆን አለበት። ገንዘቡ ለታሰበለት ፕሮጀክት መዋሉን ማረጋገጥ ይገባል። ለከፍተኛ ብድሮች ማስያዣን ማስቀጠል፡ አገርን ሊያንገዳግዱ የሚችሉ ከፍተኛ መጠን ያላቸው ብድሮች ግን ያለ ተመጣጣኝ ማስያዣ መሰጠት የለባቸውም።

በቅርቡ የተጀመረው ዋስትና አልባ ብድር አቅርቦት ከዚህ ቀደም የንግድ ሃሳብ እያላቸው በዋስትና እጦት ምክንያት ወደ ተግባር መግባት ያልቻሉ ዜጎችን ወደ ሥራ በማስገባት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ

የባንክ ዘርፍ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ የዚህ አይነቱ የብድር ስርዓት ዋነኛው ጥቅም የፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋፋት ነው። የንግድ ሥራ ለመጀመር የሚፈልጉ ነገር ግን ባህላዊ ዋስትና ማቅረብ ያልቻሉ አዳዲስ ፈጣሪዎች የገንዘብ ምንጭ የሚያገኙበትን ዕድል ይፈጥራል።

ጥንቃቄ እና ቁጥጥር ያስፈልጋል ብለዋል።ይሕንን ሲያስረዱ

ዋስትና አልባ ብድር ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍተኛ ቢሆንም፣ ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ተመላክቷል። ብድሩን የሰጡ የፋይናንስ ተቋማት አደጋን ለመቀነስ የሚከተሉትን ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ማተኮር አለባቸው፡

  • የክትትል እና ግምገማ ሥርዓት ማጠናከር: ብድር የተሰጣቸው ፕሮጀክቶች አፈጻጸም እና የገንዘብ አጠቃቀም በየጊዜውና በጠበቀ ሁኔታ መከታተልና መገምገም አለበት።
  • ጠንካራ የአዋጭነት ምርመራ ብድር ከመሰጠቱ በፊት የቀረቡት የቢዝነስ ሃሳቦች አዋጭነትና ትርፋማነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በጥልቀትና በጠንካራ ሁኔታ መረጋገጥ አለበት። ይህ ካልሆነ ግን የብድር የመመለስ አደጋ ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል።

ለኢኮኖሚው ያለው ጠቀሜታን በተመለከተ

በሌላ በኩል፣ ባለሙያዎቹ እንዳብራሩት፣ ዋስትና አልባ ብድር በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ተጽዕኖ ሰፊ ነው። ከዚህ ቀደም በዋስትና እጦት ወደ ተግባር ሳይገቡ የቀሩ ጠቃሚ የንግድ ሥራዎች አሁን ወደ ሥራ ሲገቡ፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚውን እንቅስቃሴ ያጠናክራል እንዲሁም አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ለዜጎች ተጠቃሚነት አስተዋጽኦ ያደርጋል።

በመጨረሻም፣ ባንኮችና የፋይናንስ ተቋማት ይህንን አዲስ አሰራር በጥንቃቄና በስፋት ተግባራዊ በማድረግ በተለይም ፈጠራ ያላቸው የንግድ ሃሳቦችን በማስቀደም ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...