ዶ/ር አብርሃም በላይ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከማንነት እስከ ክህደት በዝርዝር ተቹ፤ “ሁሉም ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል”

Date:

አዲስ አበባ — አሁን በስደት አሜሪካ ያሉትንና በትጥቅ ትግል መንግስትን ለመገልበጥ እየሰሩ ያሉትን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከባህሪያቸው በመነሳት በክህደት ፈርጀው የተቿቸው ዶክተር አብርሃም በላይ “ሁሉም ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል” በማለት ነው የጀመሩት።

ዶክተር በላይ በግል የፌስ ቡክ ገጻቸው አቶ ገዱን ሰሞኑን በሰጡት አስተያየት ላይ ነው ተንተርሰው ትችቱን በየፈርጁ ያስቀመጡት ሙሉውን ያንብቡ፤ አቶ ገዱ መልስ ከሰጡ የምናትም ይሆናል።

“ሁሉም ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል” እንዲሉ አበው፣ ለሆነውም-ላልሆነውም እንተ-ፈንቶ መልስ ከመስጠት መቆጠብ የሚለውን መርሕ የማስቀድም ብሆንም፤ ሰሞኑ አቶ ገዱ በሰጡት“ቃለ-መጠይቅ” ሰምቼ ግን ሀሳቤን ላክፍል ወደድኹ::

ቅድመ-ሐሳብ

የህብረትን ዋጋ፣ በጋራ የመሆንን ልዕልና በጫካ ምሳሌ ካቀረበው የአለማየሁ ዋሴ “ጫካ” መፅሓፍ ውስጥ “እነ ዝሆን-አንጀት አና ግንዳሞቹ ” በስራ እና በባህርያቸው የተጠሩት እፅዋት ፤ ከሰሞኑ “ የአቶ ገዱ፣ ልጅ ቴዎድሮስ ፀጋዬ እና አቶ ልደቱ “ቃለ-መጠይቅ” ትኩረቴን ሳበ፡፡ ፀሐፊው ስለጫካ ስያወራ የተለያዩ የጫካ እፅዋት እንዳሉ፣በግብርና ባህርያቶቻቸው በመመርኮዝ እፅዋቱን የተለያየ ስም ይሰጣቸዋል::

ትንሽ ትልቁን ዛፍ ለአደጋ የሚጥሉ አለቅጥ ሰፍተው ስፍራ ያልበቃቸው መሬት በቃኝ የማይሉ ግንዳሞቹ ይላቸዋል፤ በአንፃሩ፣ የተባለውን ከተባለበት ዓውድ እና መጠን እያወጡ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ ያልተባለውን እየፈጠሩ፣ ጫካውን ከዳር እስከዳር በሃሜትና በጥላቻ፣ በወሬ እና በነገር እንዲሞላ እና ሌሎችም ሐረጋት በሃሜቱና ዝንጠላው እንዲዋደዱ የሚተጉ “እነዝሆን አንጀት” ሲል ሰይሟል፡፡

እናም በቃለ መጠይቁም“ዝሆን-አንጀት እና ግንዳሞቹ” የተባሉትን ለማየት እምብዛም አልቸገረኝም::

የነገሬ አስኳል ሐሳብ

የፖለቲካ ሂደታችን የግድ “በበሬ ወለደ…” አስተሳሰብ ቀድሞ በራሳችን ስንፍና እና እምነት ጉድለት ያጣነውን ለመመለስ መፈጨርጨር መሆን የለበትም፡፡ የትም አያደርስም፤ ከመላላጥ ውጪ፣ ትዝብት ከማስቀረት በቀር፡፡ እየተባላን ያጣነውን ይመልስልናል ብለን ባሰብንበት መንገድ ሁሉ መፍጨርጨር አያስፈልገንም::

በመግቢያዬ ላይ እንደጠቀስኩት፣ አቶ ገዱን እና ስለወቅቱ የመሬት እና አስተዳደር ጥያቄዎች ጉዳይ የፌታውራሪ አቋማቸውን በተመለከተ፣ ራሳቸውንም ማስታወስ ዳር ሆኖ ለሚታዘበን አድማጭ ተመልካቾችንም ግልፅ መረጃ ማቅረብ ያስፈልጋል ::

ከራሳቸው ቃለ-መጠይቅ እንደምንረዳው፣ የጦርነቱ ግምገማቸውና አቀረብኩት ያሉት የመፍትሔ ሐሳብ፣ “የአማራ ኃይሎችን በማስታጠቅ ዲተረንስ እንፍጠር” ሲሉ፣ የጏላ-ጏላ በግልፅ እንደተናገሩት የአካባቢ ታጣቂዎችን የኃይል ምሽግ ይዞ የራስ ፍላጎትን በተናጠል ማራመድ መሆኑን በአንደበታቸው መስክረዋል:: እንዲህ ያለውን ሲሰማ፣ “ክህደት፣ ውሸት፣ እምነት ጉድለት ዕድሜም ደረጃም አይመርጡም እንዴ?” ያስብላል፡፡ በሽማግሌ ሲስተዋል ደግሞ ይበልጥ ያስከፋል-አይጠበቅማ!!

ስለሆነም፣ የሰዎችን የሞራል ውድቀት ልክ ማጣት ምሳሌ እንዲሆኑ፣ ለቀጣይ ትውልድም እንደማስተማርያ እንዲያገለግል፣ ውሸትን በማጋለጥ ሰንዶ ማቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

“የመጣውን ለውጥ በዋና ተዋናይነት መርቻለሁ” ብሎ ከሚገልፀው፣ የመንግስትን በጣም ከፍተኛ የሀላፊነት እርከን ላይ የነበረና እስከ ጡረታ እድሜው ከመራ ሰው፣ “ይህንን አልነበርኩበትም!” አይነት “ሰማይ ተቀዶ ሲሰፋ ነበርኩ” እንዳለችው ጦጢት ጋር ያስደምማል::

የህወሓት ከፍተኛ ጥፋትና ሽለላ የፈጠረው የትግራይ ጦርነት ሲታወስም፣ በየመድረኩ የጦርነት ጎሳሚ፣ የጦር ፌታውራሪ ሆነህ ስታቅራራ ኖረህ አሁን በሌላ ቨርዥን መከሰት ምን ለማትረፍ ነው? በዚህ የህግ ማስከበር ዘመቻ አሳቦ የአካባቢ ሽሚያ፣ የማንነት ጥያቄ ተገን በማድረግ የሚደረግ ማናቸውም የመሬት ይዞታዎችን ከህጋዊ መንገድ ውጪ በጉልበት መውሰድ አግባብነት እንደሌለው ውይይት መቀመጣችን እየታወቀ፤ ከዚህ በተቃራኒ የግል ፍላጎትህን ለማሟላት ወደየ አካባቢዎቹ ተጉዘህ በሃሰት መርዝ ስትረጭ እንዳልነበረ የረሳን መስሎህ ይሄ ሁሉ የውሸት ናዳ ምን ይሉታል!!

በሶስተኛው ጦርነት ግዜ መሪዎች ወደ ግንባር በመሄድ ለመስዋእትነት ሲወስኑ ያንተ የተሸናፊነት ሀሳብ እና የተግባር ምላሽ ምን እንደነበር አልተዘነጋም፡፡ በዛው ቅፅበትም የህወሓት ሰራዊት ወደ ትግራይ ከመለስን በጏላ ለማቆም ስንወስን “ግፋ በለው” የምን ማቆም ነው ብለህ ስታናፋ እንዳልነበር ፃድቅ መስለህ መቅረብ ማንን ለማታለል ነው፡፡

ለማንኛውም፣ “ውሸት በእግሩ ሲሄድ…ይመስላል” ከሚያስብል ክህደትና ውሸት ራስን ማጽዳት ለሰማያዊው ቤትም ይጠቅማል እና ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ እውነት ምንም አገላብጠው ቢሸፋፍኗት መገለጧ አይቀሬ ነው!

ዝነኛው ድምጻዊ ኪሮስ አለማየሁ “ኩሉ ንምርኣይ ምቅናይ-ምቅናይ” ያለው፣ እንዲህ አይነቱም የክህደት እና የውሸት ጥግ ለመስማትም ለማየትም ነው እና እውነትም መቆየት ጥሩ ነው::

Website፡ https://addisreporter.com/

Email፡ info@addisreporter.com

Telegram፡ https://t.me/addisreporter11

X፡ https://x.com/addisreporter

Phone no ፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...