ጥቂቶች በ”ወንጀል” ያዋለዱት የሱማሌዎች መከራ በአሜሪካ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በሀገራቸው ረሃብ እና ሰላም እጦት ቢበረታባቸው የተሻለ ህይወትን ፍለጋ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ የዘር ሀረጋቸው ከምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሶማልያ የሚመዘዝ ስደተኞች ላይ የአሜሪካ መንግስት ብትር ጠንከር ብሎ መሰንዘር ጀምሯል።

እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 15 2025 ሲቢኤስ ዜና ሚኒሶታ እንደዘገበው የሚኒፖሊስ እና የኢሚግሬሽን ወኪሎች (ICE) የሶማሌ ማህበረሰብ ማእከል በሆነው በካርሜል ሞል ዙርያ ኦፕሬሽን አካሂደዋል። በርካታ ግለሰቦችንም በቁጥጥር ስር በማዋል እና በማሰር በአካባቢው በሚገኙ ሶማሌዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የፍርሀት ድባብ ፈጥረዋል።

አዲስ ሪፖርተር ከዚህ ቀደም እንደዘገበችው በሚኒሶታ የሚገኝ መጠነ ሰፊ የማጭበርበር ድርጊት ለሕዝባዊ አገልግሎት የተመደበን በቢሊዮን የሚቆጠር የግብር ከፋዮች ገንዘብ በመደበኛ ባልሆነ የገንዘብ ዝውውር አማካኝነት ወደ አልሸባብ እጅ እንዲገባ ማድረጉን አመልክቷል። ይህ ድርጊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በምስራቅ አፍሪካ ተወላጆች ላይ ጠንከር ያለ የቪዛ ማዕቀብ እና የማባረር እርምጃ እንዲዝቱ መነሻ ሆኗቸዋል።
ከዚህ አፈሳ እና ግጭትን በስተጀርባ ያለው መንስኤ እጅግ ብዙ የሶማሊያ ተወላጆችን ያካተተው እና ለአሸባሪው አል-ሸባብ የጀርባ አጥንት የሆነው የቢሊዮን ዶላሮች ዘረፋ ነው።

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ተራምፕ በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያዎችን ‘ሀገራቸው መጥፎ የሆነችው በምክኒያት ነው ምክኒያቱም እነርሱ ቆሻሾች ናቸው’ በማለት ገልፀዋቸዋል።

ከሀገሩ የወጣ ካገሩ እስኪመለስ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ ነውና ነገሩ ሶማሊያ ዎችም የሚደርስባቸውን ክብረነክ ስድብና ድርጊት ተቋቁመው በረሃብና በፍርሃት በራቸውን ቆልፈው መቀመጥ ምርጫቸው አድርገዋል።

ነዋሪዎች እንደሚናገረ‍ኡት በአንድ ወቅት እንደ ሴዳር-ሪቨርሳይድ እና ካርሜል ሞል ባሉ ሬስቶራንቶች እና የገበያ ኮሪደሮች ይታይ የነበረው ጫጫታ እና ሳቅ በፍርሀት እና በአርምሞ ተቀይሯል።

ኤምፒአር ዜና እንደዘገበው ጥቃቱን ተከትሎ ብዙዎቹ የአእምሮ ህክምና ደ‍ጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አምናለሁ ያሉት በሚኒያፖሊስ የካፒቶል ካፌ ባለቤት የሆኑት ፋርሃን አህመድ “ለንግድ ስራዬ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸው እየደረሰባቸው ያለውን ፍርሃት ለሚመለከቱ ህጻናት ጭምር እጨነቃለሁ” ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

አጭበርባሪ የሶማሊያ ዲያፖራዎች እናት ሀገራቸውን እንደ ምስጥ እየበላ ለሚገነድስ አሸባሪ ቡድንን ማደራጀታቸው ሳያንስ ይባስ ዛሬ በሰላም ሀገር ህይወታቸውን አቃንተው ወገን ዘመዳቸውን ረድተው ለሚኖሩ ሶማሊያውያን ሳይቀር መዘዛቸው መትረፉ ዛሬም በምስራቅ አፍሪካ እና በኢትዮጵያ የእናት ሀገራቸውን ሞት ለማፋጠን ለሚታትሩ ትልቅ ማስተማሪያ እንደሚሆን ግልፅ ነው።

በሀገራቸው ረሃብ እና ሰላም እጦት ቢበረታባቸው የተሻለ ህይወትን ፍለጋ ወደ አሜሪካ የተሰደዱ የዘር ሀረጋቸው ከምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሶማልያ የሚመዘዝ ስደተኞች ላይ የአሜሪካ መንግስት ብትር ጠንከር ብሎ መሰንዘር ጀምሯል።

እ.ኤ.አ. በዲሴምበር 15 2025 ሲቢኤስ ዜና ሚኒሶታ እንደዘገበው የሚኒፖሊስ እና የኢሚግሬሽን ወኪሎች (ICE) የሶማሌ ማህበረሰብ ማእከል በሆነው በካርሜል ሞል ዙርያ ኦፕሬሽን አካሂደዋል። በርካታ ግለሰቦችንም በቁጥጥር ስር በማዋል እና በማሰር በአካባቢው በሚገኙ ሶማሌዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የፍርሀት ድባብ ፈጥረዋል።

አዲስ ሪፖርተር ከዚህ ቀደም እንደዘገበችው በሚኒሶታ የሚገኝ መጠነ ሰፊ የማጭበርበር ድርጊት ለሕዝባዊ አገልግሎት የተመደበን በቢሊዮን የሚቆጠር የግብር ከፋዮች ገንዘብ በመደበኛ ባልሆነ የገንዘብ ዝውውር አማካኝነት ወደ አልሸባብ እጅ እንዲገባ ማድረጉን አመልክቷል። ይህ ድርጊት ፕሬዝዳንት ትራምፕ በምስራቅ አፍሪካ ተወላጆች ላይ ጠንከር ያለ የቪዛ ማዕቀብ እና የማባረር እርምጃ እንዲዝቱ መነሻ ሆኗቸዋል።
ከዚህ አፈሳ እና ግጭትን በስተጀርባ ያለው መንስኤ እጅግ ብዙ የሶማሊያ ተወላጆችን ያካተተው እና ለአሸባሪው አል-ሸባብ የጀርባ አጥንት የሆነው የቢሊዮን ዶላሮች ዘረፋ ነው።

ዘ ጋርዲያን እንደዘገበው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ተራምፕ በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ ሶማሊያዎችን ‘ሀገራቸው መጥፎ የሆነችው በምክኒያት ነው ምክኒያቱም እነርሱ ቆሻሾች ናቸው’ በማለት ገልፀዋቸዋል።

ከሀገሩ የወጣ ካገሩ እስኪመለስ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ ነውና ነገሩ ሶማሊያ ዎችም የሚደርስባቸውን ክብረነክ ስድብና ድርጊት ተቋቁመው በረሃብና በፍርሃት በራቸውን ቆልፈው መቀመጥ ምርጫቸው አድርገዋል።

ነዋሪዎች እንደሚናገረ‍ኡት በአንድ ወቅት እንደ ሴዳር-ሪቨርሳይድ እና ካርሜል ሞል ባሉ ሬስቶራንቶች እና የገበያ ኮሪደሮች ይታይ የነበረው ጫጫታ እና ሳቅ በፍርሀት እና በአርምሞ ተቀይሯል።

ኤምፒአር ዜና እንደዘገበው ጥቃቱን ተከትሎ ብዙዎቹ የአእምሮ ህክምና ደ‍ጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አምናለሁ ያሉት በሚኒያፖሊስ የካፒቶል ካፌ ባለቤት የሆኑት ፋርሃን አህመድ “ለንግድ ስራዬ ብቻ ሳይሆን ቤተሰቦቻቸው እየደረሰባቸው ያለውን ፍርሃት ለሚመለከቱ ህጻናት ጭምር እጨነቃለሁ” ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።

አጭበርባሪ የሶማሊያ ዲያፖራዎች እናት ሀገራቸውን እንደ ምስጥ እየበላ ለሚገነድስ አሸባሪ ቡድንን ማደራጀታቸው ሳያንስ ይባስ ዛሬ በሰላም ሀገር ህይወታቸውን አቃንተው ወገን ዘመዳቸውን ረድተው ለሚኖሩ ሶማሊያውያን ሳይቀር መዘዛቸው መትረፉ ዛሬም በምስራቅ አፍሪካ እና በኢትዮጵያ የእናት ሀገራቸውን ሞት ለማፋጠን ለሚታትሩ ትልቅ ማስተማሪያ እንደሚሆን ግልፅ ነው።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...