ለህፃፅና አከባቢው  የተላከው 257 ሚሊዮን የሚያወጣ እህልና 55.5 ሚሊዮን ብር ጥሬ ብር ምን ዋጠው? ሪፖርታዥ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ለአሰገደ ወረዳና ለሀፃፅ ካምፕ የተላከው 257 ሚሊዮን ብር የሚገመት 12.1 ሚሊዮን ኪሎ ግራም እህልና በትሬው ለተፈናቃዮቹ የተላከ 55.5 ሚሊዮን ብር የት ገባ? ምን ዋጠው? ወዴት ደረሰ? የሚለው ጉዳይ ሊመረመር ይገባል። ከሀፃፅ የወጣው የረሃብ ዜና ለምን እስካሁንስ ዝም ተባለ? ተፈናቃዮቹ በተጠቀሰው ስፍራ መኖር ከጀመሩበት ቀን አንስቶ እስከ አለፈው ሳምንት ድረስ 340 ሰዎች ሞተዋል። ባለፉት አራት ወራት ደግሞ ሰማኒያ የሚሆኑ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል? በረሃብ? በዕድሜ፣ በበሽታ? ወይስ በምን? ይህ ሁሉ ሳይጣራ ዜጎችን የፖለቲካ ማገዶ ለማድረግ መጯጯህ ሃዘኑን ድርብ ያደርገዋል። መፍትሄውንም ያርቀዋል።

መረጃዎች እንደሚያመልክቱት በየወሩ ያለማቋረጥ ስንዴ፣ አልሚ ምግባና የአትክልት ዘይት ከፌደራል መንግስት በተጠቀሱት ካምፖች ላሉ ተፈናቃዮች ተልኳል። ትህነግ “ትግስትም ልክ አለው” በማለት ባወጣው መግለጫ ይህን አላስተባበለም። ወይም በዝርዝ “ይሄ አልተደረገም” ሲል በደል አልዘረዘረም። ተከሰተ ለተባለው “ረሃብ” የፌደራል መንግስት የከሰሰው መግለጫ ሕዝብ መዝኖ እንዲፈርድ በዳታ የተመሰረተ፣ በመረጃ የተደገፈ ጉድለት አላቀረበም።

ዜናውን እንደ ዜና የዘገቡ ሚዲያዎችም ሆኑ የማህበራዊ ገጽ አምደኞች እንደየ አሰላለፋቸው በበጎና አፍራሽ መልኩ ወገንተኛነት የተላበሰ መረጃ ከማሰራጨት በዘለለ ጉዳዩን በቅጡ ለመመርመር ጊዜ የወሰዱ አይመስልም። አሁን ላይ እየወቱ ያሉ መረጃዎች ግን ጩኸቱ እንዲመረመር የሚያስገድዱ ናቸው።

በሀፃፅ ካምፕ መረጃ ያሰባሰበ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ እንዳለው፣ ካምፑ ውስጥ ያሉት ተፈናቃዮች ከሰማኒያ በመቶ በላይ አዛውንቶች ናቸው። ራሳቸው አዘጋጅተው መመገብ የሚችሉ ቁጥራቸው ብዙ ነው። ክልሉ በጎ ፈቃደኞችን አዘጋጅቶ ሊረዳቸውና የሚሰጣቸውን ምግብ ወደ ቀላል አዘገጃጀት መቀየር ግዴታው እነሆነ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።  

የረሃብ ዜና በማህበራዊ ገጾች ከመበተኑ አንድ ቀን በፊት የክልሉ ጊዜያዊ አሰተዳደር መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። ከዛ ቀደምም በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ውይይት አድርገዋል። አብረዋቸው የመጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ማግኘት ባይችሉም የተለያዩ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናትን አግኝተው መክረዋል። አሜሪካና እንግሊዝ ኤምባሲ ገብተው ተወያተዋል። ምላሹ እንደታሰበው ባይሆንም!!

መንግስት ለተጠቀሱት አካባቢዎች ሲያደርግ ከነበረው ድጋፍ ውስጥ  ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ ባሉት ወራት  ተፈናቃዮች (IDPs) የተደረገውን የእህል፣ አልሚ ምግብ፣ ዘይትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ስርጭት ይፋ አድርጓል። ተፈናቃዮቹ የሚሰጣቸው በቤተሰብ 15 ኪሎ ማሽላ ብቻ እንደሆነ መስክረዋል። ከመንግስት የሚወጡ standard ወይም መለኪያ በተበጀለት አሰራር በቤተሰብ 17 ኪሎ ሲሆን በቆሎ፣ ስንዴ፣ ጥራጥሬ፣ አልሚ ምግቦችን ያካተተ እርዳታ ነው።  ታዲያ እንደ ሚዲያ፣ ዜጋና ሰው ሲታሰብ “ሲላክ የነበረው ድጋፍ ሁሉ የት ገባ?” የሚያስብል ነው።  ይህ ጥያቄ መልስ ያሻዋል። ትህነግ በጮኸ ቁጥር አብሮ መጮኽና መጯጯህ እስከመቼ ይቀጥላል? የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥያቄ ብቻ ሊሆን አይገባም። የሳልሳዊ ትግራይ፣ የባይቶና፣ የስምረት ፓርቲ አመራሮች ጉዳዩን ከማንም በላይ ስለሚያውቁት “ትህነግ ጦርነት ሲፈልግ የፈጠረውን ረሃብ አጀንዳ ያደርጋል” በማለት በተመሳሳይ የተናገሩት ከምን ተነስተው ይሆን? ሚዲያዎች በገለልተኛነት ሊመረምሩት ይገባል።

በትግራይ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ራሱን በተገንጣይ ስም የሚጠራው ትህነግ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሁዋላ ለሁለት የተከፈለበት ዋና ምክንያት የተፈናቃዮችን ታጋች አድርጎ መያዝና ሌብነት እንደሆነ ልዩነታቸው ጎልቶ ሲወጣ ይፋ ያደረጉት ራሳቸው ናቸው። በዚህ መነሻ፣ ተፈናቃዮችን የፖለቲካ ጋሻ ማድረግ ለምን ተመረጠ? ለተፈናቃዮች ሲሰጥ የነበረው እርዳታ ካልተቋረጠ፣ ረሃቡን ማን ፈጠረው? ለምንስ ተፈለገ? አጀንዳውስ ዛሬ ላይ እንዲቀጣጠል እንዴት ተወሰነ? የሚሉትን ጉዳዮች መመርመር፣ መርምሮም አቋም መያዝና ሕዝብን አስቦ መራመድ እንደሚያስፈልግ ፓርቲዎቹ እየገለጹ ነው።

አንደኛው ወገን “ቅድሚያ ሕዝብ ወደ ተፈናቀለበት ስፍራ ይመለስ” ሲል፣ ሌላኛው ወገን ደግም “ቅድሚያ ትህነግ ትዳን” በዚህ ልዩነት ሳቢያ ጊዜ ባክኖ ተፈናቃዬች በመከራ እየተጠበሱ ነው። ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ አምስት ዓመታትን በመጠለያ ማሳለፍ ለማንም እዕምሮ ላለው ዜጋ ሁሉ ረፍት የሚነሳ፣ ህሊናን የሚፈትን፣ መፈጠረን

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት፣ በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አማካኝነት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ወገኖች እያደረገ ያለው ሰፊና ያልተቋረጠ የሰብአዊ ድጋፍ፣ መንግስት ለዜጎቹ ደህንነትና ክብር ያለውን ጽኑ አቋም በተግባር ያሳየ እንደሆነ ይገልጻል። የኮሚሽኑ የአራት ወራት (ከመስከረም እስከ ታህሳስ 2018) የእርዳታ አፈፃፀም ተጨባጭ መረጃ እንደሚያሳየው፣ መንግስት እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሀብትና ሎጂስቲክስ በመመደብ ተፈናቃዮችን ከረሃብና ከጤና ቀውስ ለመታደግ ሰፊ ርብርብ ማድረጉን ነው።

ባለፉት አራት ወራት በተከናወነው የድጋፍ ስራ፣ በየወሩ በአማካይ ከ912,476 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች የዕለት ደራሽ የምግብና የገንዘብ እርዳታ ተደራሽ ሆኗል። በዚህም መሰረት በየወሩ ከ136,871 ኩንታል በላይ ስንዴ እና ከ51.5 ሚሊዮን ብር በላይ ቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ ሲቀርብ ቆይቷል። ይህ የአቅርቦት ሂደት ያለ ምንም መቆራረጥ እና በወጥነት መከናወኑ፣ ከፌደራል መንግስት የወጣው መረጃ ያመልክታል።

በተለይም በጦርነቱ ምክንያት ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋላጭ የሆኑ እናቶችንና ህጻናትን ለመታደግ የተደረገው ጥረት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። በየወሩ በአማካይ 2,133 ኩንታል አልሚ ምግብ (CSB+) እና 1,288 ኩንታል የአትክልት ዘይት ተደራሽ ተደርጓል። ይህ እርምጃ መሰረታዊ የምግብ ፍላጎትን ከማሟላት ባለፈ፣ በክልሉ ሊከሰት የሚችለውን የተመጣጠነ ምግብ እጥረትና የረጅም ጊዜ የጤና ቀውስ ለመከላከል ትልቅ ሚና እንደሚጫወት የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። መንግስት ይህን መሰል ግዙፍ ድጋፍ ሲያቀርብ፣ የዜጎችን ሰብአዊ መብት የማክበርና የመጠበቅ ግዴታውን በግንባር ቀደምትነት እየተወጣ መሆኑን በማስታወቅ ነው። ትህነግ ኝ ይህን ያጣጥላል። ትህነግ ይህን ሲያታጥል ከመንግስት ወገን በአሃዝ፣ በጊዜና፣ በመጠን ተገልጹ በተቀመጠው ልክ ዝርዝር መረጃ በማቅረብ አለመሆኑ ግራ የሆነባቸው ብዙ ናቸው።

ከምግብ አቅርቦቱ ጎን ለጎን፣ መንግስት ተግባራዊ ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ባለፉት አራት ወራት ውስጥ ብቻ ከ 206 ሚሊዮን ብር በላይ ነው። ይህ ገንዘብ በቀጥታ በተፈናቃዮች እጅ እንዲገባ መደረጉ፣ ተፈናቃዮች እንደየፍላጎታቸው የተለያዩ አልሚ ግብዓቶችን ከአካባቢ ገበያ እንዲገዙ ዕድል እንዲፈጥርላቸው ታስቦ ነው። ይህ አሰራር የተረጂዎችን የመምረጥ መብትና ክብራቸውን ከመጠበቁም በላይ፣ በጦርነቱ ምክንያት ተዳክሞ የነበረውን የአካባቢ ገበያ እና የንግድ እንቅስቃሴ መልሶ እንዲያንሰራራ ትልቅ ሞተር ሆኖ ይሆናል የሚል አመክንዮ የሚቀርብበት ጉዳይ ነው።

የወረዳዎች የድጋፍ አፈጻጸም ዝርዝር ትንታኔ

የመንግስት የሰብአዊ ድጋፍ ስርጭት የተፈናቃዮችን ቁጥርና የፍላጎት ደረጃ መሰረት በማድረግ ሁሉንም ተጋላጭ አካባቢዎች ያካተተ ነው። በዚህም መሰረት ከፍተኛው የተፈናቃይ ቁጥር በሚገኝበት የሽሬ (Indaselassie) ማዕከል ለሚገኙ 312,852 ተፈናቃዮች በየወሩ 46,927.80 ኩንታል ስንዴ እና 731.39 ኩንታል አልሚ ምግብ (CSB+) ሲከፋፈል ቆይቷል። በአድዋ ከተማ የሚገኙ 108,126 ተፈናቃዮችም በተመሳሳይ ወርሃዊ 16,218.90 ኩንታል ስንዴ እና 252.79 ኩንታል አልሚ ምግብ ተደራሽ ተደርጎላቸዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በአስገዴ ወረዳ ለሚገኙ 76,011 ወገኖች 11,401.65 ኩንታል ስንዴ እና 177.70 ኩንታል አልሚ ምግብ የቀረበ ሲሆን፣ በህጻፅ መጠለያ ለሚገኙ 44,484 ተፈናቃዮች ደግሞ 6,672.60 ኩንታል ስንዴ እና 104 ኩንታል አልሚ ምግብ በየወሩ እየተሰራጨ ይገኛል። የኢንዳባጉና ወረዳም የዚሁ ድጋፍ አካል ሲሆን፣ ለ42,913 ተፈናቃዮች 6,436.95 ኩንታል ስንዴ እና 100.32 ኩንታል አልሚ ምግብ እንዲደርሳቸው ተደርጓል። ይህም እርዳታው ለተረጂዎች ከሚሰጠው ቀጥታ ጠቀሜታ ባለፈ፣ በአካባቢው የሚገኙ ዜጎች በፌደራል መንግስቱ ላይ ያላቸውን እምነት የሚያጠናክርና ማህበራዊ መረጋጋትን የሚፈጥር ነው።

የድጋፍ አሰባሰብ ሂደት፡ ስርዓትና ህግን መከተል

ማንኛውም ለተፈናቃዮች የሚደረግ ድጋፍ በተበታተነ መልኩና ለተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች ማስፈጸሚያነት በሚውል መንገድ መከናወን የለበትም። የድጋፍ አሰባሰብና ስርጭት ሂደት ግልጽነትና ተጠያቂነትን በሰፈነበት መልኩ፣ የአገሪቱን የሰብአዊ ድጋፍ ህግና ስርዓት ተከትሎ በፌደራል አደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩል ብቻ መፈጸም ይኖርበታል።

ድጋፉን ማዕከላዊ በሆነ መንገድ ማስተዳደር፣ እርዳታው ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ለማረጋገጥ፣ ድግግሞሽን ለማስቀረትና ፍትሃዊ ስርጭት እንዲኖር ለማድረግ ወሳኝ ነው። በተለያዩ አካላት የሚሰበሰቡና ስልታዊ ባልሆነ መንገድ የሚሰራጩ ድጋፎች፣ ለሙስናና ለፖለቲካዊ መጠቀሚያነት የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ በመሆኑ፣ ሁሉም ለጋሾችና ረዳት ድርጅቶች በፌደራል መንግስቱ የተቀመጠውን መመሪያና አሰራር በጥብቅ ሊከተሉ ይገባል። ይህም እርዳታው ለፖለቲካዊ ግፊት ሳይሆን ለሰብአዊ አገልግሎት ብቻ መዋሉን ያረጋግጣል።

የፕሪቶሪያው ስምምነት ተፈጻሚነት

መንግስት እያደረገ ያለው ሰፊ የሰብአዊ ድጋፍ የሚበረታታ ቢሆንም፣ ዜጎች ለረጅም ጊዜ በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ መቆየታቸው ግን ዘላቂ መፍትሄ ሊሆን አይችልም። ስለሆነም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ መኖሪያ ቀያቸው የመመለሱ ስራ በልዩ ትኩረት ሊሰራበት ይገባል።

በዚህ ሂደት ውስጥ ትህነግ ተፈናቃዮችን ለፖለቲካ ትርፍና እንደ “ፖለቲካዊ ጋሻ” ከመጠቀም ተቆጥቦ፣ ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት በቅንነት መስራት ይኖርበታል። ዜጎች በገዛ ቀያቸው በሰላም የመኖር መብታቸውን ማክበርና ለዚህም ምቹ ሁኔታን መፍጠር ከማንኛውም የፖለቲካ ፍላጎት በላይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። ተፈናቃዮችን በመጠለያ ውስጥ ማቆየት ለፖለቲካዊ ጫና መፍጠሪያነት መጠቀም የዜጎችን ስቃይ ከማራዘም ባለፈ ለክልሉ ሰላም ፋይዳ የለውም።

ለትግራይ ክልል ተፈናቃዮች የሚደረገው ሰብአዊ ድጋፍ ከዕለት ደራሽ እርዳታ ባለፈ ዜጎች ራሳቸውን ወደሚችሉበትና ወደ መልሶ ማቋቋም (Recovery) ምዕራፍ እንዲሸጋገር ማድረግ ወሳኝ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎችና መረጃዎች ያመላክታሉ። የፌደራል መንግስትና ዓለም አቀፍ ረድኤት ድርጅቶች ድጋፋቸውን ዜጎች በኢኮኖሚ ራሳቸውን ወደሚያጠናክሩበት (Resilience) ተግባራት ላይ ማዞር ይኖርባቸዋል። ይህም ተረጂነትን ከመቀነስ ባለፈ፣ ወገኖች ወደ ቀደመ የግብርና እና የንግድ ስራቸው ተመልሰው የክልሉን የምግብ ዋስትና በዘላቂነት እንዲያረጋግጡ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

ተፈናቃዮች ወደ ቀደመ ቀያቸው ተመልሰው የተረጋጋ ህይወት እንዲመሩ አስተማማኝ የደህንነት ዋስትና ማረጋገጥ ሌላው ቅድመ-ሁኔታ ነው። ዜጎች ወደ መኖሪያቸው በሚመለሱበት ወቅት የጸጥታ ስጋት እንዳይኖር አስተማማኝ የደህንነት ከባቢ መፍጠርና በጦርነቱ ምክንያት የወደሙ እንደ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎችና የውሃ ተቋማት ያሉ መሰረተ ልማቶችን በፍጥነት መጠገን ያስፈልጋል። ይህም ተመላሾች መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙና ማህበራዊ ትስስራቸው እንዲቀጥል በማድረግ በኩል የማይተካ ሚና ይኖረዋል።

የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ማረጋገጥም ለዘላቂ መፍትሄው ቁልፍ ተግባር ነው። በአሁኑ ወቅት ለመጠለያ ጣቢያዎች አስተዳደርና ለዕለት ደራሽ ምግብ የሚውለው ግዙፍ በጀት፣ ወደ ዘላቂ የልማት ስራዎች እንዲዞር የተፈናቃዮች አሰፋፈር ሂደት ግልጽ በሆነ የጊዜ ሰሌዳ ተቀምጦለት በፍጥነት ሊተገበር ይገባል። ይህ ሂደት ሲፋጠን፣ ለመጠለያ የሚባክነው ሀብት ተቀንሶ ለተመላሾች ማቋቋሚያና ለቋሚ ልማት ፕሮጀክቶች የሚውልበትን ዕድል ያሰፋዋል።

በመጨረሻም፣ በክልሉ የሚገኘው የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሰብአዊ መብት ከማንኛውም የፖለቲካ ፍላጎት ቀድሞ በማስቀደም ትልቅ ሃላፊነት ሊወጣ ይገባል። አመራሩ የዜጎችን ስቃይ ለፖለቲካ ትርፍ ከመጠቀም ተቆጥቦ፣ የፌደራል መንግስት ለሚያከናውነው የመልሶ ማቋቋም ጥረት አስፈላጊውን ትብብርና ቁርጠኝነት ሊያሳይ ይገባል። የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት መንፈስ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ በቅንነት መስራት፣ ተፈናቃዮች ያለምንም ተጨማሪ መጉላላት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱና የክልሉ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ዋነኛው መንገድ ነው።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...