የፅምዶ ውጤት – ናቅፋ ትግራይን ወረረ፤ ሻዕቢያ በናቅፋ የኢትዮጵያን ብር ይገዛል፣ በብር ዶላር ይሰበስባል፣

Date:

ሻዕቢያ በናቅፋ ከኢትዮጵያ የቀንድ ከብት፣ ወርቅ፣ ነዳጅና የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ ይሸምታል። ጥሬ ብርም ዝቅ አድርጎ በናቅፋ ይገዛል። ብሩን በባንክ ወይም በሰው አማካይነት እያዘዋወረ ዶላር ያጥባል። ትህነግ የፈጸመለት ጽምዶ በኢትዮጵያ እንዳሻው እንዲፈነጭ ስለሚፈቅድለት ከትግራይ ሕዝብ ጉሮሮ እየተነጠቀ ስንዴና አልሚ ምግብ ይቸበቸብለታል። ትንሽ ጠበቅ ሲል በሚከፍላቸው ሚዲያዎችና ባንዶቹ አማካይነት የጩኸት ዘመቻ ይከፍታል። ትህነግ ትግራይን የሻዕቢያ መጨፈሪያ አድርጎ አገር በማተራመሱ ድራማ ውስጥ ግንባር ቀደም ተላላኪ የሆነው ይህንኑ ለማስፈጸም ነው። ይህ ድርጅት ነው እንግዲህ ረሃብ ገባ እያለ የሚያላዝነው”

አዲስ ሪፖርተር – በኮንትሮባንድ የኢትይጵያን ገንዘብ በገሃድ መሰብሰብ “ሃይ” የሚለው ያጣ የኤርትራ መንግስት የዕለት ተዕለት ስራ ነው። ትግራይ ሳይሆን በአዲስ አበባ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የኢትዮጵያን ብር ሲያሻቸው በባንክ፣ ሲያሻቸው በፌስታል ማከማቸት ለኤርትራዊያን ክለከላ የሌለው የጠራራ ጸሐይ ተገባራቸው ነው። ስንቶቹ በመዋቅር ከኢትዮጵያ የዘለዓለም ጠላት ከሆነው ሻዕቢያ ጋር አይሰሩም የሚለው ጉዳይ ያከራክር ካልሆነ በቀር ሁሉንም ዜጎች ከንፈር የሚያስመጥጥ ጉዳይ ነው።

“ከፍተኛ ብር ሲሆን በራይድና በሞተረኛ ነው የምናደርሰው” ስትል አዲስ አበባ ሆና ብር የምታጥበው የሻዕቢያ ተከፋይ አገልግሎቱን ለሰጠችው ዲያስፖራ ቡና እየጠጡ እንዳጫወተችው ገልጸን መዘገባችን አይዘነጋም። በርካቶች እንደሚሉት ሻዕቢያ ምንም ሳያወጣ ከኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬና ቁሳቁስ ይዘርፋል።

“በሌብነት የተካነና የመንግስት ቅርጽ የለውም” የሚባል ስብስብ ኤርትራ በገሃድ ከከተመበት ጊዜ አንስቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ እየጋጠ፣ ከዕለት ጉርሳቸው እየነጠቀ፣ የኢኮኖሚ ደባ እያከናወነ ዛሬ ላይ ደርሷል። ኢትዮጵያን “ቅኝ ገዢ” ብሎ በፈጠራ ትርክት ጫካ ከገባበት ጊዜ አንስቶ በባንዳነት ለኢትዮጵያ ውጋት ሆኖ የኖረው ሻዕቢያ ከተገነጠለ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ያፈለሳቸው የ“ንጻነት” ድምጽ ሰጪዎች ሚሊዮን ደርሰዋል። ከነዚህ መካከል አዲስ አበባን በወንጀል፣ በገንዘብ አጠባና በኮንትሮባንድ በማመስ ተሳትፎ ያላቸው ስለመኖራቸው “ኢትዮጵያዊያንን መንካት ግፍ ነው” የሚሉ ለህሊናቸው ያደሩ የሚመሰክሩት ጉዳይ ነው።

ከላይ የተገለጸው አግባብ ግልጽ ቢሆንም የሚከናወነው በሚስጢር እንደሚከናወን በማስመሰል ነው። ሰሞኑን ከትግራይ የሚወጡት መረጃዎች ግን በትህነግ “አይዟቹህ” ባይነት ሉዓላዊነትንና ሕገመንግስትን የሚጻረር የአደባባይ እብሪት እንደሆነ ውንብድናውን ዩእሚያውቁ እየመሰከሩ ነው።

“የኤርትራ መገበያያ ገንዘብ የሆነው ናቅፋ በትግራይ ክልል የንግድ ልውውጥ ውስጥ በስፋት መስፋፋቱ የሁለቱን አጎራባች አካባቢዎች የኢኮኖሚ ትስስር ጥልቀት የሚያሳይ አዲስ እና አሳሳቢ ክስተት ሆኗል” የሚሉ እየበዙ ነው። ትህነግ ከሻዕቢያ ጋር አዲስ ለጀመረው “ፍቅር” አንዱ ማሰሪያ ውል በናቅፋ መጠቀም እንደሆነ ሰል ስምምነቱ ወይም ፡ጽምዶ” የሚያውቁ ለአዲስ ሪፖርተር አመልክተዋል።

ቀደም ሲል በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ብቻ ተወስኖ ውር ውር ሲል የነበረው በናቅፋ መገበያየት አሁን ላይ ወደ ገፋ ኮንትሮባንድ ንግድ አድጓል። ትህነግ ጭራውን እየቆላ ካራጁ ጋር በጀመረው የጫጉላ ጨዋታ ናቅፋ ትግራይ አንዳንድ  ከተሞችን ሳይቀር እየወረረ ነው። ከማዕከል የሚላከውን የትግራይን ሕዝብ ድርሻ እየሸመተ የሚያግዘውም በዚሁ ቅጠሉ አማካይነት ነው።

የናቅፋ መስፋፋት እስከ አዲግራት እና አደዋ ድረስ መድረሱ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ነጋዴዎች የገለጹት ሲሆን ይህም በድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ያልተገደበ እና ሕገወጥ እንቅስቃሴ መረን መልቀቅ ያሳያል። በዚህ አግባብ እየሆነ ያለውን የሚከታተሉ የትግራይ ክልል ተቀናቃኝ ድርጅቶችና ገለልተኛ ነዋሪዎች ባዝተው ይቃወማሉ።

የሁለቱ አገራት ድንበር መከፈቱን ተከትሎ የኮንትሮባንድ ንግድ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉ የናቅፋ ስርጭት ዋና መነሻ እንደሆነ ተመላክቷል። ይህ የንግድ መስፋፋት የናቅፋን ተጠቃሚነት ከጥቂት ውስን ነጋዴዎች እጅ አውጥቶ ወደ በርካታ ትናንሽ ነጋዴዎች እንዲደርስ አስችሏል።

የባንክ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት የናቅፋ መስፋፋት በትግራይ ክልል ካለው የኢትዮጵያ ብር አቅርቦት እጥረት ጋር ተያያዥነት አለው።

በባለሙያዎቹ አስተያየት የጸጥታ ስጋት በርካታ ሰዎች ጥሬ ገንዘብ ከባንክ አውጥተው በቤታቸው እንዲይዙ በመገፋፋቱ የብር እጥረትን አስከትሏል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ ባለው በዚህ መደበኛ ባልሆነ እና ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ አዳዲስ ነጋዴዎች ደላሎችና የኮንትሮባንድ አንቀሳቃሾች ከሁለቱም ወገን እየተራቡ ይገኛሉ።

ይህ እንቅስቃሴ ያለ ፌዴራል መንግስት እውቅና የክልላዊ ትስስር የመፍጠር ዝንባሌን የሚያሳይ በመሆኑ የፖለቲካዊ እና ሕገ መንግስታዊ ጥሰት ትርጉምም አለው። ይህ የተነጋደደ ግንኙነት፣ በቅድሚያ የትግራይን ሕዝብ የሚጎዳ ሲሆን በቀታይነይ የአገር ኢኮኖሚም የሚበላ ውንብድና ነው።

የአንድ ክልል የገንዘብ ልውውጥን በተመለከተ ከማዕከላዊው መንግስት እውቅና ውጭ ከሌላ ሀገር ጋር መግባባት የሀገሪቱን የገንዘብ ሉዓላዊነት የሚጥስ አደገኛ ተግባር መሆኑን የሚናገሩ እንደሚሉት አካሄዱ ጸረ ህገ ብቻ ሳይሆን ዓላማው ልዩ ነው።

ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ኮምኒኬሽን ኃላፊ አቶ ብርሀነ አፅባህ ለአዲስ ሪፖርተር በሰጡት አስተያየት- ይህ የንግድ ፍሰት በሕወሓት እና በኤርትራ መንግስት የጋራ እቅድ አካል የተፈጸመ መሆኑን በመጥቀስ የታዛቢዎችን ስጋት ይጋራሉ።

አቶ ብርሀነ “በፌደራል ሥርዓት ውስጥ ያለ አንድ ክልል ያለ ማዕከላዊ መንግስት ውሳኔ እንደ አንድ ነጻ ሀገር ከሌላ አገር ጋር የኢኮኖሚ ግንኙነት መፍጠር አይችልም” ሲሉ የሕግ ጥሰት መሆኑን ይናገራሉ።

“ይህ የፅምዶ ኢኮኖሚ ትስስር ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግስት ቁጥጥር ውጭ የሆነ ራሱን የቻለ የኢኮኖሚ ቀጣና ለመፍጠር እና የሁለቱን ድርጅትች ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ፣ የማይዘልቅ ዕቅድ ነው” ብለውታል። አቶ ብርሀነ “ይህ ተግባር ሕገወጥ ብቻ ሳይሆን የክልሉን ሕዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

|ከነዳጅና ከእህል ምርቶች በተጨማሪ የቁም እንሰሳት እና የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ከትግራይ ወደ ኤርትራ በብዛት ይላካሉ” በማለት ማስረጃ እያጣቀሱ የሚናገሩት አቶ ብርሃነ፣ በተለይም ወጣቶች እነዚህን ምርቶች በከፍተኛ ዋጋ ለመሸጥ ለኤርትራ ገበያ ያቀርባሉ ብለዋል። ሻዕቢያ ናቅፋ እያተመ ይሸምታል። የሸመተውን በውጭ ምንዛሬ ይሸጣል። ያሻውን ለአገር ውስጥ ገበያ ያውላል።

ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅም ድንበር ላይ እንደሚዘዋወር የጠቀሱ ሲሆን ይህም የሀገርን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ  የሚጎዳ ከባድ ሕገወጥ ንግድ እንደሆነም አመልክተዋል።

ለወርቅ ክፍያ የኤርትራ ነጋዴዎች አልፎ አልፎ በዶላር ጭምር እንደሚከፍሉ የተናገሩ ሲሆን ይህም ወርቁን ለመግዛት የውጭ ምንዛሪ መጠቀማቸው የንግዱን ዓለም አቀፋዊ ሕገወጥነት አመላካች እንደሆነ ጠቁመዋል። ይህ የሚሆነው ትህነግ እሸምታለሁ ለሚለው መሳሪያ እንደሆነ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ጠቁመዋል።

ከፊደራል መንግስት የሚላከውን ነዳጅና ሸቀጣ ሸቀጥ ጨምሮ፣ ከኢትዮጵያ ይህ ሁሉ ሃብት ሲጋዝ፣ ከኤርትራ ሲጋዝ ወደ ትግራይ ከሚገቡት ፍጆታዎች መካከል ሳሙና ዘይትና በኮንትሮባንድ ከሱዳን የሚገባ ኤሌክትሮኒክስ ይገኙበታል።

እነዚህ ፍጆታዎች ከአዲስ አበባ ከሚገዛበት ዋጋ ባነሰ ዋጋ በድንበር በኩል ስለሚመጡ ለነጋዴዎች የተሻለ ትርፍ ያስገኛል በዚያ ምክንያት ሕገወጥነቱን መንሰራፋቱን አብራርተዋል።

|”ነዳጅ ከክልሉ ወደ ኤርትራ በከፍተኛ ደረጃ መጓጓዙ በትግራይ ክልል የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት ዋና ምክንያት ሆኗል” በማለት ትህነግ በነዳጅ አቅርቦት ችግር ክስ የሚሰነዝረውን ራሱ እየቸበቸበው መህኑን ያጋልጣሉ። እንደ እሳቸው ገለጻ በኤርትራ ድንበር አካባቢዎች ደግሞ አንድ ሊትር ቤንዚን ከ300 ብር በላይ እየተሸጠ መሆኑ በመጥቀስ የችግሩን ስፋት እና ሕገወጥነት ያመላክታሉ።

”አቶ ብርሀነ የሸቀጦች በተለይም የነዳጅ እና የምግብ ፍጆታዎች ወደ ውጭ በኮንትሮባንድ መውጣት በትግራይ ክልል የሸቀጦች እጥረት እንዲፈጠር እና ለከፋ ረሀብ መከሰት አስተዋጽኦ እያደረገ ነው” ብለው ተችተዋል። የክልሉ ሀብት እና መሰረታዊ ፍጆታዎች በሕገወጥ መንገድ ወደ ውጭ እንዲወጡ መፈቀዱ የክልሉን ሕዝብ በቀጥታ የሚጎዳ ፀረ-ሕዝብ ተግባር መሆኑንም አብራርተዋል።

ለጥቃቅን ንግዶች ወደ ኤርትራ ከተሞች የሚያቀኑ ወጣቶች ምርታቸውን በናቅፋ በመሸጥ ወደ ትግራይ ተመልሰው በጥቁር ገበያ ወደ ብር እንደሚለውጡት አመልክተዋል።

በድንበር አካባቢ ባለው ጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሰረተ ንግድ ወደ ትግራይ የሚገባው ናቅፋ በትይዩ ገበያ ወደ ብር የሚቀየርበት ሕገወጥ ሁኔታ መስፋፍቱን በማመልከት የኢትዮጵያ ብር እየተዘረፈ መሆኑን አመልክተዋል። ብሩ ወደ መሃል አገር ተዛውሮ ዶላር እንደሚሰበስብበት፣ ሻዕቢያ ምንም ሳይለፋ በሚያገኘው ብር ለምዛሬ ከፍተኛ የምንዛሬ ተመን በማቅረብ የትይዩ ገበያውን እንደሚያንረው ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።

በውጭ አገር ባሉ የሻዕቢያ የገንዘብ አስተላላፊዎች አማካይነት ለዘመዶቻቸው ለሚልኩ በትግራይ በካሽ እንደሚከፈልና፣ አዲስ አበባና ሌሎች አካባቢ ላሉ ደግሞ ከትግራይ በኢትዮጵያ ባንኮች አማካይነት ላሰማሯቸው ኤርትራዊያን ወይም ራሳቸውን ቀይረው በኢትዮጵያዊ ስም በሚጠሩ የሻዕቢያ ሰዎች ገንዘብ በማስተላለፍ የውጭ ምንዛሬ እንደሚሰበስቡ አሰራሩን የሚያውቁ ይናገራሉ። መንግስት ከትግራይ በሚወጡና ወደ ትግራይ በሚደረግ የገንዘብ ዝውውር ላይ ጠበቅ ያደረገ ቁጥጥር ሲያደርግ ጩኸት የሚነሳውም በዚሁ ምክኛት መሆኑን ይናገራሉ።

የሚያስገርመው በአዲግራት ባሉ ድንበር አቅራቢያ ከተሞች አንድ የኤርትራ ናቅፋ ከ12 እስከ 15 ብር እየተለወጠ የመሆኑ ዜና ነው። በዚህ የምንዛሬ መጠን የኢትዮጵያን ብር የሚያፍሰው ሻዕቢያ ኢትዮጵያ እንደተተራመሰች እንድትቆይ የሚሰራው ከዚሁ ፍላጎቱ አንጻር እንደሆነ በርካታ መረጃ በመትቀስ አገር ወዳዶች ቀድመው ሲናገሩ የነበረውን ሃቅ ገሃድ አድርጎታል።

ይህ የዋጋ ልዩነት በሕገ ወጥ ገበያው ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር እና ትርፋማነት እንደሚያመልክት፣  ይህም የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም እንደሚጎዳ አቶ ብርሃኑ ተናግረዋል። የድንበር ንግድ በስፋት የሚካሄድባቸው ከተሞች ባድመ ራማ ጾረና እና ዛላምበሳ መሆናቸው አክለዋል። አካሄዱ የሕገወጡ ንግድ በተደራጀ  መንገድ በስልጣን ላይ ባሉ አካላት የሕግ ጥሰት እየተፈጸመ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነ ጠቁመዋል።

የኤርትራ ወታደሮች አልፎ አልፎ ከትግራይ ነጋዴዎች ላይ እያስገደዱ ገንዘብ እንደሚቀሙ፣ ፈቃደኛ ካልሆኑ ድብደባ የሚፈጽሙ  መሆናቸውን መረጃ እንዳላቸው አቶ ብረሃነ አክለው ገልጸዋል።

የናቅፋ መስፋፋት በትግራይ ክልል ኢኮኖሚ ውስጥ የገንዘብ አቅርቦትን በማመጣጠን ረገድ ጊዜያዊ አዎንታዊ ሚና ቢኖረውም የብርን የመግዛት አቅም የማሳጣት እና የዋጋ ግሽበትን እንደሚያባብስ ባለሙያዎች አመልክተዋል።

 “በትህነግና እና በኤርትራ መንግስት መካከል የተፈጠረው ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን የጣሰ እና የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ሽርክና ጣጣው ዞሮ ዞሮ ለትግራይ ሕዝብ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የማዕከላዊው መንግስት ይህን ሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የኮንትሮባንድ ንግድ ለመቆጣጠር ፈጣን እና ውጤታማ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ አቶ ብርሀነ አፅባህ ምክር ይለግሳሉ።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

ለኢትዮጲያ ሲሉ ቀይ ባሕር ላይ የወደቁት ጀግኖች አደራ ተቀባይ

ኢትዮጵያ ቀይ ባሕር የትናንትና ታሪኬ ኾኖ አይቀርም የሚል አጀንዳዋን...

ሀሰን ሼኽ በመጨረሻ “እኔም የቬንዙዌላ ፕሬዚዳንት ዕጣ ይደርሰኛል” በሚል ጭነቀት ውስጥ መሆናቸው ተሰማ

አዲስ ሪፖርተር - እስራኤልን ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከሶማሊላንድ ጠራርገው...