አዲስ ሪፖርተር – የስጋት ትንታኔ መስጠት እሰጣለሁ ባይ ነው። ጥልቅ ትንተና እሰጣለሁ ይላል። ለኢንቨስተር ግብዓት መስጠት፣ ምክር መለገስ ኢንቨስት ከማድረጋቸው በፊት መረጃ ማቀበል የሚደርስብኝ የለም ሲል ራሱን ይክባል። በኢንቨስትመንት ረገድ የሚደርስን አደጋ አስቀድሞ ለከለከል ሁነኛ መረጃ በማቅረብ “ጠንቋይ ነኝ” ይላል።
በአንድ አገር ውስጥ ያለውን የፖለቲካና የደኅንነት አደጋ “ሪስክ” በማጥናት ቀጣዩን ሁኔታ መተንበይ የተካነበትና የተቋቋመበት ዓላማው እንደሆነ ያስረዳል። እንዲህ ራሱን ሰቅሎና ክቦ የሚያቀርበው ድርጅት “ማን ነው?” ብለው ከጠየቁ ምንም መረጃ አይገኝም። በዚህ ማንነቱ ነው በ2024 ኢትዮጵያ ላይ ራሱን ደብቆ መርዙን የረጨው። ኦነግ ሸኔ ቅርጹን ቀይሮ ወደ አድብቶ ገዳይነት እንደሚቀየር ያስታወቀው። ድብቅ ይምስለ እንጂ ደራሲው ግልጽ ነበር።
የስሙ መነሻ ግንድ የሚመዘዘው ከላቲን ነው። “vates” ይባላል። ትርጉሙም “prophet” ነቢይ ማለት ነው። ወይም Fortune teller ትንቢት አብሳሪ፣ የወደፊቱን ገላጭ እንደ ማለት ይሆናል። ስሙንም ስያሜውንም ጠቅሶ ማብራሪያ ያኖረው ራሱ ቡድኑ ሲሆን ከስሙ ለመረዳት እንደሚቻለው “ሰማያዊ ቅባትን” ራሱ ላይ የደፋ የህቡዕ ድርጅት ነው። እዚህ ድርጅት ውስጥ ኢትዮጵያዊ ነን የሚሉ እንደሚርመጠመጡበት አዲስ ሪፖርተር ማረጋገጫ አግኝታለች።
ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ ላይ አተኩሮ እንደሚሠራ የሚናገረው ይህ ኅቡዕ ቡድን፣ ሪፖርቱን ባወጣበት vatescorp.com ድረ ገጹ ሲያዛው አለ፤ ሲያሻው የለም። የሚያምታታው ናይሮቢ በተከራየው አንድ ክፍል ቤት ሲሆን በገስቱ ላይ በሰፈሩ አድራሻዎች አያገኙትም። ጃዋር መሀመድ ናይሮቢን ሲለቅ፣ ድርጅቱ ትክክለኛ መንፈስ ሆኗል። ወይም ወጣ ገባ እየተቻወተ ነው። ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በተቀናበረ ሤራ፣ በገፊ ጎታች ስልት ሆን ተብሎ ለዜና ፍጆታ የሚፈጠረውን አለመረጋጋት የሚዘግቡለት መዋቅር አለው።
“ሐቅን እንዘግባለን፤ እውነትን እናጣራለን ” በማለት ለራሳቸው ማዕረግ የሰጡ አክቲቪስቶች ይህን ድርጅት ማን እንደሆነ ለመጠየቅ አልደፈሩም። ይልቁኑም ስማቸው አሁን ላይ ከድርጅቱ ጋር እየተነሳ ነው። ቬትስ ያወጣውን ዘገባ “እውነት ይሆን?” ብለው የመረጃውን ሐቅ ለማጣራት ወይም “fact check” ለማድረግ ደፋ ቀና ሲሉ አለመታየታቸው በ2014 አነጋጋሪ ቢሆንም ዛሬ ላይ ምላሽ አግኝቷል። በአጭሩ ራሱን ሰማያዊ ዘይት ከቀባው መንፈስ የሆነ ለዚህ ህቡዕ ድርጅት ጋር የሚሰሩ ሆነው ተገኝተዋል።
ኢትዮጵያ ላይ ኢንቨት አታድርጉ በማለት የትርምስ መረጃ ሰብስቦ የስጋት መረጃ የረጨውን ይህን ቡድን “ዘገባው የማን ነው? ነብዮቹስ እነማን ናችሁ?” የሚል ጥያቄ አንስቶ የጠየቀ አልነበረም። ካቀረበው ዘግናኝና አደገኛ መረጃ አንጻር እንዲፈተሽ ያልተወደደው ይህ ድርጅት፣ አሁን ላይ የናይሮቢ የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ ቅኔ ገልጦታል።
የስሙ መነሻ ግንድ የሚመዘዘው ከላቲን ነው። “vates” ይባላል። ትርጉሙም “prophet” ነቢይ፣ ወይም Fortune teller ትንቢት አብሳሪ፣ የወደፊቱን ገላጭ፣ ጠንቋይ እንደ ማለት ነው። ስሙንም ስያሜውንም ጠቅሶ ማብራሪያ ያኖረው ራሱ ቡድኑ ሲሆን ከስሙ ለመረዳት እንደሚቻለው “ሰማያዊ ቅባትን” ራሱ ላይ የደፋ የህቡዕ ድርጅት ነው።
የአደባባይ የድረገጹ ስምና መገኛው vatescorp.com ነው። ምርመራና የሥጋት ቅድመ ትንተና ማድረግ ዋናው የሥራው የጀርባ አጥንት እንደሆነ የሚጠቁመው ይኸው ቡድን ከስያሜውና ለራሱ ከሰጠው የነቢይነት አክሊል ውጪ ሌላ ዝርዝር የማንነት መገለጫ የለውም። ራሱን ሰማያዊ ቅባት ከመቀባቱ በቀር ስለ ምንነቱና ማንነቱ ምንም መረጃ ባለመሰጠቱ ጥሞናን የሚያስቀድሙ ዜጎች ሁሉ “ማነህ ነቢዩ? እነማን ናችሁ ትንቢት አብሳሪዎቹ?” ወዘተ የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ አስገድዷቸው ነበር።
ይህ ከተግባሩ በላይ ማንነቱ ህቡዕ መሆኑ ቀድሞ መነጋገሪያ የሆነበት ማኅበር፣ ቡድን፣ የመናፍስት ስብስብ ወይም ተላላኪ ስለ ራሱ በድረገጹ ሲገልጽ “ቬትስ” ከሚለው ስሙ በስተቀር ራሱን አለማጥራቱ በትክክለኛ ቁመናው ለመጥራት አስቸጋሪ ያደረገዋል። ስለዚህ “የኅቡዕ ቡድን” በሚል መጥራቱ ተቀባይነት ያለው ሃሳብ በመሆኑ በዚህ ሪፖርት እንደተለመደው “የኅቡዕ ቡድን” በሚል ሰይመነዋል።
እንደ “ነብይነቱ፣ የወደፊቱን ተንባይነቱ” አስቀድሞ የሥጋት ዳሰሳዎችን በማዘጋጀት ለኩባንያዎች በተለይም ለኢንቨስተሮች መረጃ እንደሚሰጥ፣ ስጋትና አደጋ (ሪስክ) ለመቀነስ የሚጠቅም ግብዓት አስቀድሞ እንደሚያቀርብ፣ ለዚህም እንደሚተጋ፣ ተግባሩም እንደ “ብርሃን አምላክና መልዕከተኞች” ዓይነት እንደሆነ ያለ ሥጋት ይገልጻል።
ቡድኑ “መቀመጫዬ ናይሮቢ ነው” ከማለቱ በስተቀር የሃብት ምንጩ፣ ማን እንደሚመራው፣ ኃላፊው፣ ሴክሬታሪው፣ አባላቱም ይሆኑ ደጋፊዎቹ እነማን እንደሆኑ የማይገልጽ የኅቡዕ አደረጃጀት ያለው ነው። ስለ ራሱ ባወጣበት የማኅደሩ ገጽ ላይም በኅቡዕ መስራት የመረጠበትን ምክንያትም አላብራራም።
ራሱን ምናብ አድርጎ ሕያው መረጃ አቀርባለሁ ባዩ ቡድን ኢትዮጵያ ላይ ኢንቨስት እንዳይደረግ በይፋ ጎራዴ የሰበቀ ለመሆኑ ከዚያም ከዚህም የለቀማቸውና እንደ ጥሬ ሐቅ የተጠቀመባቸው መረጃዎቹና ድምዳሜው ያጋፍጡበታል። የኅቡዕ ቡድን የመሆኑ ምሥጢርም እዚህ ላይ ፍንትው ብሎ ይወጣል። እዚህ ላይ ናይሮቢ የነበሩትና በሚዲያ የተካነ ልምድ አለን የሚሉትን፣ በተለያዩ የውጭ ሚዲያዎች የሚሰሩትንና መረጃ የሚያቀብሉትን “ኢትዮጵያዊያኖች” ማስታወስ ግድ ይላል። ጃዋር መሐመድና ጭፍሮቹ!!
ቡድኑ አንዳንድ ታዋቂ ነን ባይ ግለሰቦች፣ አገር ውስጥ ሆነው ተቀጥረው የሚሠሩ ሚዲያዎችና ተላላኪዎች፣ በጋዜጠኛነት ታፔላ የሚንቀሳቀሱና በስም ለማይናገሩት ቡድን የሚሠሩ፣ በጋራ ተናብበው ኢትዮጵያ ላይ ሲተፉት የከረሙትን መርዝ ጨምቆ ያቀረበ የምናብ ተቋም ነው። ይህ ቡድን ኦነግ ሸኔን የሞተ አስመስሎ ያገዝፈዋል። ዛሬ ይህን ቀደም ሲል የተረጨ መርዝ ማስታወስ የተፈለገው በምክንያት ነው። አሁን እዚህና እዚያ የሚሰሙት የቅጥር ነበሰ ገዳዮች እንዲሁ በድንገት የተወለዱ እንዳልሆኑ ለማስጨበጥ ነው። ነገርን ከስሩ ማይትም አግባብ ስለሆነ ነው። በ2024 የተያዘ አጀንዳ መሆኑን ለማታውቁም ለማስረዳት ነው።
ይህ ራሱን ጨለማ ያደረገ የኅቡዕ ቡድን ለሚፈለገው ዓላማ ማሳኪያ የሚሆኑ ቃለ ምልልሶችን በማዘጋጀት ከሚያሰራጩለት ወገኖች የሚላክለትን መረጃዎች ሰብስቧል። በቀጥታና በተዘዋዋሪ ከአሜሪካ ክፍያ ሲፈጸምላቸው የነበሩና አዲስ አበባ መሽገው ኢትዮጵያን ከሚቦረቡሩ ሪፖርተሮችና ዓለምአቀፍ ጋዜጠኛ ነን ባዮች ጋር ባለው ግንኙነት የሚፈልገውን ዜና አስቀድሞ አሰርቷል። ከዚህ በተጨማሪም ተዓማኒ ለመምስል የዓለም ዓቀፍ ተቋማትን በማካተት ተጨምቆ የወጣው situation analysis የሁኔታዎች ትንተና መሳይ አዘጋጅቷል። በዚህ መልኩ ተደርቶና በቅንብር እንደ ቲያትር የተቀነባበረው የዘገባው መጠሪያ Ethiopia: Situational Analysis (Horn of AfricaSituational Analysis Series (HoA-SA)), July 04, 2024; Reporting Period:
June 20 – July 03, 2024. ይላል።
ሪፖርቱ ምሥጢር ነው? ሪፖርቱ በየገጹ በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ራሱን ሲሰቅልና ሲያገን “ምሥጢር” (ኮንፊዴንሻል) የሚል ታቤላ ለጥፎባቸዋል። ያለ ቡድኑ ፈቃድና ይሁንታ ማሰራጨትንም ሆነ በግብዓትነት መጠቀምን ይከለክላል። በቡድኑ ውስጥ የተካተቱት የስፔሻል ኦፕሬሽን ፎርስ ልምድ ያላቸው፣ የሕግ ዕውቀት ያካበቱ፣ የአካባቢውን ባሕል የሚያዉቁ ስለመሆናቸው በደምሳሳው ከመገለጹ ውጪ ቡድኑ አግዝፎ ስለጠራቸው አባላቱ ማንነት አንዳችም ጉዳይ አያነሳም። በዚህ ደረጃ የቡድኑ አባላት ራሳቸውን በመንፈስ መስለው “የተደበቁት ነቢዮች” ለመባል መምረጣቸው ከቀረበው ሪፖርት በላይ መነጋገሪያ ሆኗል። ጃዋር ናይሮቢ መሽጎ እንዲህ ነበር የሚሰራው።
ብልጽግናን የሚደግፉ እንደሆኑ የሚታወቁና በተለይ በማኅበራዊው ሚዲያ ጎልተው የሚታዩት ሪፖርቱ ምን እንደሚልና በምን ይዘት ላይ እንደተቸከለ በወቅቱ አልተረዱትም ነበር። ዘገባውን ሳያነብቡ የሪፖርቱ ዋና አስኳል ጉዳይ ጋርም ፍጹም ተለያይተው “የመፈንቅለ መንግስት ሤራ” በሚል ያሰራጩት ሪፖርት ሲጨመቅ ዓላማውና የትኩረት አቅጣጫው እነርሱ እንዳሉት ሳይሆን ሌላ ነው።
በሪፖርቱ ውስጥ “መረጃ” በሚል የተካተተውን በጥንቃቄ ለሚያነብ ዘገባው በግልጽና በተዘዋዋሪ መንገድ የሚናገረው አንድ መልዕክት ነው፡- “የውጭ አገር ኢንቨስተሮች ሆይ! ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ አደጋ ስላለና አለመረጋጋት ስለሰፈነ ኢንቨስት አታድርጉ፤ ኢንቨስት ያደረጋችሁም ጊዜው ሳያልፍባችሁ ቶሎ ውጡ” የሚል ነው።
በአጫጭር ንዑስ ርዕስ ስለ ኦነግ ሸኔ፣ ስለ ትሕነግ ዳግም ሕጋዊ የመሆን አካሄድ፣ ስለ ፕሪቶሪያው ስምምነት፣ ስለ ዓለም ባንክና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም፣ ስለ አልፋሽካ፣ ስለ ፋኖ፣ ስለ ሚታገቱ ሰዎች፣ ስለ አገራዊ ዕርቅ ኮሚሽኑ ወዘተ አገር ውስጥ የሚታተሙ እንደ ሪፖርተር ያሉ ጋዜጣዎች የዘገቡትን እና የሚዲያ ውጤቶችን፣ የመረጃ ምንጮችንና ለሪፖርቱ ይጠቅማሉ የተባሉ ግለሰቦችን ቃለ ምልልስ ዋቢ አድርጎል። ይህ ራሱን “በነቢይነት” ማዕረግ ሰይሞ በተዘረዘሩት ልቅምቃሚና ሆን ተብለው እንዲዘገቡ የተደረጉ መረጃዎችን ተንትኖ ትንበያ ሰጥትቷል።
ይህ ራሱን የወደፊቱ ጠንቋይ አድርጎ ያቀረበው ቡድን ሪስክ ለመቀነስ በሚል ለኢንቨስተሮች ቅድም መረጃ ማበጀቱን የሚናገረው ከላይ የተባለውን መረጃ ከተነተነ ብኋላ ነው። በጥቅሉ በኅቡዕ የተደራጀው ቡድንና ሪፖርት ሲጨመቅ እንዲህ ይመስላል።
“ሸኔ ተመቷል” ብሎ የሚጀምረው የኅቡዕ ቡድኑ ሪፖርት፣ እዚያው እጥፍ ብሎ ሸኔ መንፈሳዊ ዓላማ መሸከሙን ይናገራል። ራሱን “ነቢይ፣ የወደፊቱን አስቀድሞ ተንባይ” እንዳለው ሁሉ ኦነግ ሸኔም “ኦፐሬሽን ኢርቡ ሺኒጋ” የተሰኘ አዲስ ትግል መጀመሩን ያስተዋውቃል። ትርጉሙም “የሰማዕታት ቃል ኪዳን” ማለት እንደሆነ ትምህርት ይሰጣል። ኦነግ ሸኔ ይህንን በተለይ ሕዝብን በማሸበር፣ በማገት፣ ለይቶ በመግደል፣ ወዘተ ዘመቻ የጀመረው ደግሞ በሕዝብ ዘንድ ያጣውን ተቀባይነት ለመመለስ እንደሆነ ዘገባው ይገልጻል። አስቡት በማገትና በመግደል ስምን ማደስ!!
ኦነግ ሸኔ ከሕዝብ ያጣውን ተቀባይነት ዳግም ለማስመለስ የመረጠው አዲስ ትግል የመንግሥት ደጋፊዎች ቀደም ሲል “አባ ቶርቤ” በሚል ግለሰቦችን በመግደል ላይ የተመሠረተውን የኖረ አካሄድ በማጽናት ነው።
አድራሻ እንጂ የሚታወቅ ይፋዊ ባለቤት የሌለው ይህ የኅቡዕ ሪፖርት እንደዘገበው፤ አዲሱ የኦነግ ሸኔ ስልት የቀጥታ ጦርነት ግጥሚያ ማቆም ነው። አድፍጦ የማጥቃት ስልትን ዋንኛው ዘዴው አድርጓል ይላል። በዚሁ መሠረት ኦነግ ሸኔ አሁን ላይ ራሱን ያዘጋጀው የመንግሥት ሃብትን መዝረፍ፣ ትጥቅ የሚከማችባቸውን መጋዘኖች ማጥቃት፣ የመንግሥት ባለስልጣናትን ማደን፣ በጥቅሉ የፌደራልና የክልሉን መንግሥት ያዳክማል ተብሎ በሚታመንባቸው አግባቦች ሁሉ በኅቡዕ ወይም በደፈጣ አደጋ ማድረስ ነው በማለት አዲሱን የሸኔ ዘመቻ ይተርካል።
“ተመትቷል” ያለውን ሸኔ አዲስ ሥልትና ዘዴ ተጠቅሞ ኃይሉን ለመጎናጸፍ እየተጋ ነው በማለት የኅቡዕ ድርጅቱ ሪፖርት መርዙን ይተፋል። ዓላማው ስለ ሸኔ ብርታት ለማውራት ብቻ ሳይሆን የሸኔ በአዲስ ዘመቻ መምጣት ኢንቨስተሮችን ወደ ኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዳያደርጉ ለማሳመን ወይም ቢያንስ እንዲጠራጠሩ ለማድረግ ነው። አሁን ላይ እነ ጃዋር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ፣ በጥቅሉ በግራጫው ጦርነት ስም በኢትዮጵያ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ የጀመሩት ዘመቻ የዚሁ አካል ነው። አዲስ ሪፖርተር ይህንን ቀደም ባሉት ሪፖርቶቿ በቅጡ ማቅረቧ ይታወሳል።
ከሪፖርተር ጋዜጣ የፎቶና የዜናውን ክሬዲት ሰጥቶ፣ ከሌሎችም ሚዲያዎች አጣቅሶ፣ ከኦፌኮ ባለሥልጣናት ቃለ ምልልስ ሃሳብ ወስዶ የሸኔ እንቅስቃሴን መንፈሳዊ ቅባት አላብሶ ያቀረበው ድብቁ ቡድን የኦነግ ሸኔን “አባ ቶርቤ” የሚባል የገዳይ መንፈስ ሲፈጸም የነበረውን እኩይ አሠራር በመሸፈን በአዲስ የዳቦ ስም “የሰማዕተት ቃልኪዳን” በማለት ነው።
ዘገባው እያለ ያለው ባጭሩ ሸኔ የሞተ መስሏችሁ ኢንቨስተሮች እንዳትሸወዱ፤ ይልቁንም ሸኔ በአዲስ ቃልኪዳን አገር ሊያሸብርና ኩባንያዎችን ሊያወድም ተዘጋጅቷልና ወደ ኢትዮጵያ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ላይ እንዳትሰማሩ የሚል የጥርጣሬ ከዚያም ሲያልፍ የማስፈራሪያ መረጃ ነው እየሰጠ ያለው። ይህንን የህቡዕ ሪፖርት ያዘጋጁት ቡድኖች ናቸው አሁን ላይ ያለውን ሴራም እየገመዱ ያሉት። ማንም አመነ አላመነ ጩኸቱ ለሰዎች ሞት መቆርቆር ሳይሆን ለተፈለገው ዓላማ ማሳኪያ ግብዓት እንዲሆን ነው።
አሁን ላይ አዲስ ሪፖርተር ባላት መረጃ በኢትዮጵያ መሳሪያ ያነሱ ኃይሎች በቅርቡ ባደረጉት ግምገማ ይህ መንግስት በጦርነት እንደማይወድቅ በውጭ አገር ጥምረታቸው ገምግመዋል። ስለሆነም በህዝባዊ አመጽ ስም አገሪቱ ላይ ብጥብጥ ለማስነሳት ወስነዋል። ብጥብጥ ለማስነሳት ደግሞ የህቡዕ ጥቃት መፈጸም እንዳለበት ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ይህ ስምምነት ኃይማኖት ላይ ያተኮረ እንዲሆንና በውጤቱም ሕዝብ እንዲቆጣ ማስቻል ነው። ለዚህ ደግሞ በበቂ ደረጃ የተሰማራ የማህበራዊ ሚዲያ ጭፍራ ተዘጋጅቷል። የኃይማኖት ጉዳይ ነውና ያልገባቸው በቁጣ የሚሰታቸውን ይቀባበላሉ።
ከሁለት ሳምንት በፊት በኢትዮጵያ ቁጣ ለማስነሳት ሊሰጥ የነበረው መግለጫ በጃዋር የግብጽ ጉዞ ሳቢያ ቢሰረዝም፣ ዋናው ምክንያት ግነ ሕዝብ እንዲነሳ በቂ ምክንያት ባለመዘጋጀቱ እንደሆነ ታውቋል። በመሆኑም ከላይ በተገለጸው መሰረት ኦነግ ሸኔ አዲሱን እቅዱን እንዲያሰፋ፣ ፋኖ “ትግሌን ወደ ከተማ ትግል አወርዳለሁ” በማለት እንደ ኢህአፓ ያወጀውን ነጭ ሽብር እንዲያሰፋ ተብሏል።
የናይሮቢውን መርዛማ ሪፖርት እጅግ ሙያዊ አስመስለው ያቀረቡት የግብጽና የእነ ጃዋር እጅ አሁን በአሜሪካ ከተጀመረው ጥምረት ጋር እየሂደበት ያለው ርቀት ያስደነገጣቸው እንዳሉት “በውጭ አገር ባለው ፖለቲካ በዚህ ደረጃ ጥድፊያና አለመረጋጋት አይተን አናውቅም” በማለት ስጋታቸውን ይገልጻሉ።
የመንግስትን መዋቅር ውስጥ ባሉ ሽጉርጉሮች አማካይነት የህቡዕ ጥቃት በማስጀመር መንግስት ላይ ሕዝብ እንዲቆጣ፣ በተመሳሳይ ደግሞ ሻዕቢያ፣ ወያኔና፣ ፋኖ በጀመሩት ህብረት ውጊያ ሲከፈት ድጋፍ ለመስጠት እንዲረዳ ኦእነግ ሸኔ “ኦፐሬሽን ኢርቡ ሺኒጋ” ወይም በትርጉሙም “የሰማዕታት ቃል ኪዳን” የተባለውን እርምጃ እንዲያሰፋ ይጠበቃል።
በኦሮሚያ ሕዝብ ለአመጽ ፊቱን ማዞሩና ለጃዋር የቀድሞውን ዓይነት ጆሮ አለመስጠቱ በአርሲ አቅጣጫ እስከ ሶማሌና ናይሮሚ እንደተዘረጋ በሚገመተው አደረጃጀት እንዲጠቀም እንዳስገደደው እንቅስቃሴውን በቅርብ የሚያውቁ እየተናገሩ ነው። በዚህ ኃይማኖት ላይ የተንጠለጠለ አካሄድ ስልታዊ ድጋፍ የሚሰጡና ሙስሊም ተብድሏል የሚል ዘመቻ የጀመሩ አካላት አሉ።
በህቡዕ ስም ኢትዮጵያ ላይ ኢንቨስት አታድርጉ በሚል የተዘጋጀው ሪፖርት፣ ከሪፖርተር ጋዜጣ የፎቶና የዜናውን ክሬዲት ሰጥቶ፣ ከሌሎችም ሚዲያዎች አጣቅሶ፣ ከኦፌኮ ባለሥልጣናት ቃለ ምልልስ ሃሳብ ወስዶ የሸኔ እንቅስቃሴን መንፈሳዊ ቅባት አላብሶ ያቀረበው ድብቁ ቡድን የኦነግ ሸኔን “አባ ቶርቤ” የሚባል የገዳይ መንፈስ ሲፈጸም የነበረውን እኩይ አሠራር በመሸፈን በአዲስ የዳቦ ስም “የሰማዕተት ቃልኪዳን” በማለት ነው።
በአርሲ አቅጣጫ ያለውን የኦነግ ሸኔ “ኦፐሬሽን ኢርቡ ሺኒጋ” በሚል መንፈሳዊ ይዘት ካላው ስም ጋር አመሳስሎ ያስጀመረውና ፋይናንስ በማድረግ ያፈረጠመው ጃዋር እንደሆነ ናይሮቢ ያሉ ምስክሮች አመልክተዋል። በናይሮቢ ቆይታው ሲሰራቸው ከነበሩት ጉዳዮች መካከል አንዱና ዋናው ይህ እንደሆነ የሚገልጹት ወገኖች በ2014 በጥንቆላ ስም የተጻፈው ሪፖርት ዝም ብሎ የተጻፈ አይደለም።
በውቅቱ FDI / Foreign Direct Investment ወይም “የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት”እጅግ በከፍተኛ ደረጃ ያደገበት። ሶስት ቢሊዮን ዶላር የተመዘገበት በመሆኑ እነ ጃዋር ከግብጽ ወኪሎች ጋር ሆነው ባወጡት የቬትስ ዘገባ ኢትዮጵያ ከምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ እድገት ማሳየቷን ያምናሉ። ለስልት ይህን እውነት አምነው፣ ፋኖን፣ ኦነግ ሸኔን እና አብረዋቸው የሚሰሩትን ዘርዝረው ሥጋት በመሆናቸው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቱ እንደሚያውኩ አስፈራርተው ነበር።
ዛሬ ላይ ሆነን ሪፖርቱን ስናየው፣ በአሜሪካ የተፈጠረው ጥምረት፣ እነ ጃዋር የሚመሩት የአመጽ ዘመቻና በህቡዕ ሰዎችን ከዕምነት ጋር አያይዞ መግደልና በሚዲያ በሚፈለገው አውድ ምስጮህ በዕቅድ የሚሰራ መሆኑን ነው።
ለዚሁ ዓላማቸው የመንግስትን ካባ አብረው ለብሰው የሚሰሩ የሁለት ሰፈር ሰዎችን እንደሚጠቀሙ ሕዝብ እየጠቆመ ነው። ቀን በመንግስት ካባ፣ ማታ በሽፍታ ካባ የሚቻወቱ አካላት ላይ ጥብቅ የማጥራት እርምጃ ካልተወሰደ ልክ በጎንደር እንደሆነው በጠራራ ጸኃይ ግድያው ይቀጥላል። በአርሲ እንደሆነው ወገን ያልቃል። ሕዝብ በመንግስት ላይ ዕምነት እንዲያጣና ጥርጥር ላይ እንዲወድቅ ያደርጋል። ይህ ስንጥቅ ለጠላት አመቺ መንገድ ስለሚፈጥር በቀላሉ ማስተካከል የማይቻልበት ደረጃ ይደርሳል።
አዲስ ሪፖርተር የናይሮቢውን ሴልና አዲስ አበባ ያለውን መረብ አስመልክቶ ተከታታይ መረጃ እንደምታወጣ አስቅድመ ለመግለጽ እንወዳለን።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393






