አዲስ ሪፖርተር – ጄኔራል አብዲሪዛክ መሀሙድ ሀጂ ‘ቃሎምቢ’ በቅፅል ስማቸው “አብዲሪዛክ ኤርትራ” ይባላሉ። የተወለዱት በምዕራብ ሶማሊያ ቋራክሲ ግዛት ቀቢሪዳሃር ነው። የተወለዱት ከሟቹ አጎታቸው ዶክተር መሐመድ ሲራድ ሲሆን የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር የስራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ነው። ዶክተር መሐመድ እ.እ.አ በ2009 ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር እየተዋጉ መገደላቸውን ታሪካቸው ይናገራል።
ኤርትራ የኦብነግ ተዋፊዎችን ታሰለጥን እንደነበር ምስክር የሆኑት አባል “አብዲሪዛክ ኤርትራ” የሶማሊያ አየር ኃይል አዛዥ ሆነ ተሹመዋል።
በ2005 የኦብነግ አባል ሆነው የተመለመሉት የዛሬው የአየር ኃይል አዛዥ አብሪዛክ ወደ ኤርትራ በወጣትነታቸው የሽምቅ ውጊያና ተዛማጅ ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰድ ወደ ኤርትራ ተጓዙ።
ከሽብር ጋር በተያያዘ በ2006 አሜሪካ በሶማሊያ ላይ በወሰደችው ጥቃት የተሰደዱና ሌሎች ሶማሊያውያንን በስልጠና ወቅት ኤርትራተገናኛቸው። ኤርትራ በወቅቱ ከምዕራብ ሶማሊያ እና ከደቡብ ሶማሊያ የመጡ በርክታ ሶማሊያውያንን ታሰለጥን ነበር። በዚህም ተግብሯ በኢፋድ፣ አፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግስታት ማዕቀብ ተጥሎባት እንደነበር ይታወሳል።
ኦብነግ ከኤርትራ በርካታ የሰለጠኑ ወጣት ተዋጊዎችን በማስለፍ ሶማሊያ መዋጋቱ ይታወሳል። በዚህ መልኩ ከሰለጠኑት መካከል አንዱ የሆኑትና የትግርኛ ቋንቋን አቀላጥፈው የሚናገሩት አብዲሪዛክ ኤርትራ የሶማሊያ አየር ኃይል አዛዥ ሆነ መሾማቸው መነጋገሪያ የሆነበት ምክንያትም ይህ ነው።
ሹመት የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት የአገሪቱን የመከላከል አቅም ለማሳደግና በተለይም የአየር ኃይሉን መልሶ በማዋቀር ለማዘመን ታስቦ እንደሆነ ቢገልጽም፣ በቅጽል ስማቸው አብዲሪዛክ ኤርትራ የተባሉት መኮንን መሾማቸው ኤርትራ በሶማሌያ ውስጥ ሲያሻት አሸባሪ፣ ሲያሻት መንግስትን የምትደግፍ፣ ይህንንም የምታደርገው ኢትዮጵያን ታሳቢ አድርጋ እንደሆነ የሚያሳይ እንደሆነ እየተጠቆመ ነው።
ጄኔራል አብዲሪዛክ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ፋርማጆ እና የኤርትራ ፕሬዝዳንት አፍወርቂን የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር ትልቅ ሚና መጫወታቸው ይነገራል። በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሌያ መከላከያ አባላት በኤርትራ እንዲሰለጥኑ አድርጓል። ከአስር ሺህ በላይ የሶማሊያ ተዋጊዎች የሰለጠኑትም በዚሁ ግንኙነት አማካይነት ነው።
በአሁኑ ሀሰን ሼክ መሀሙድ አስተዳዳሪ አብዲሪዛክ እንደ ሞቃዲሾ እና አስመራ ግንኙነት ቁልፍ ሚና እየተጫወቱ ያሉት አብዲሪዛክ ኤርትራ፣ የአየር ኃይል አዛዥ ሆነው መሾማቸው የኤርትራ እና የምዕራብ ሶማሌ ክልልን ውስጣዊ ግንኙነት የሚያሳይ እንደሆነ ተመልክቷ።
ጄኔራሉ በኤርትራ ቆይታቸው ከሶማሊያ የመጡ ሰልጣኞች በቅርበት ሲከታተሉ እና ሲያስተባብሩ የነበረ በመሆኑ፣ አሁን የአየር ኃይሉን ሲረከቡ አብዛኞቹ የበታች መኮንኖች እና ባለሙያዎች እርሳቸው የሚያውቋቸው እና አብረዋቸው የቆዩ እንደሆኑ ታውቋል።
ሜጀር ጄኔራል አብዲሪሳክ ማህሙድ ሃጂ “ኤርትራ” በኤርትራ ሳዋ የሰለጠኑ፣ የትግርኛ ቋንቋ አቀላጥፈው የሚናገሩ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፣ በኤርትራ በእሳቸው አስተባብሪነት የሰለጠኑ ከአስር ሺህ የሚልቁ ተዋጊዎችን ይመሩ የነበሩ የሻዕቢያ ታማኝ መሆናቸውን የሶማሊያ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው።
የ40 ዓመቱ የአየር ኃይል አዛዥ፣ ሶማሊያ ከፓኪስታን የጄኤፍ-17 ተዋጊ ጄቶችን ለመግዛት ውል ከመፈረሟ ጋር ተያይዞ የአየር ኃይሉን አቅም ለማዘመን ካለው ዕቅድ ጋር ስማቸው በስፋት እየተነሳ ነው።
ሶማሊያን ከአል-ሸባብ ነጻ ለመውጣት በሚል “ሁለገብ ዘመቻ” የአየር ኃይልን ማጠናከርና በሶማሊያ የሚገኙ የውጭ አገራት ሰላም አስከባሪዎችን ለማስወጣት በየተያዘው ዕቅድ መሰረት፣ የሰላም አስከባሪዎቹ ሲወጡ፣ ክፍተቱን ለመሙላት ሶማሊያ ዝግጅት እያደርገች ያለችው በኤርትራ እና በቱርክ የሰለጠኑ ወታደሮቿን እንደሆነ ጉዳዩን አስመልክቶ ከሚወጡ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።
አዲሱ የሶማሊያ አየር ኃይል አዛዥ መሰረታቸው የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር በመሆኑ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለመክፈት ደፋ ቀና የሚለውን ያሳደጋቸውን፣ ኤርትራ ስልተና የላካቸውን ድርጅታቸውን እንደሚረዱ ይጠበቃል። ኤርትራም ይህንኑ ታሳቢ አድርጋ ለሹመት እንዳበቃቻቸው ተመልክቷል።
ግብጽ የምትመራው ኃይል ኢትዮጵያን ዙሪያዋን የመክበብ እቅድ እንዳላቸው፣ በቅርቡ ግብጽና ቱርክ የጀመሩት ህብረትና የደረሱበት ስምምነት የዚሁ አካላ ሊሆን እንደሚችል ጉዳዩን የሚከታተሉ አየገለጹ ነው።
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393






