የ“ትዕይንተ ሕዝቦች አዘጋጅ ግብረ ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” የአመጽ ጥሪ መግለጫ የመሩት ያሬድ በማግስቱ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በትናንትናው ዕለይ ራሱን “ትዕይንተ ሕዝቦች አዘጋጅ ግብረ-ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” የሚለውን ቡድን የሰጠውን መግለጫ እያስተባበሩ ሲመሩ የነበሩት አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ራሳቸውን ከቦርዱ ማሰናበታቸውን አስታወቁ። ይህን ውሳኔ ይፋ ከማድረጋቸው አንድ ቀን በፊት ከአዲስ ሪፖርተር ጋር የስልክ ምልልስ አድረገው ነበር። በምልልሱም እሳቸው ባሉበት ቦርድም ሆነ በተባለው የቴክኒክ ኮሚቴ ውስጥ ከሱዳ፣ ከግብጽና ከሻዕቢያ ጋር የሚሰሩ መኖራቸውን ስለማውቃቸው ተነስቶ ነበር።

ከዚህ የስልክ ምልልስ አንድ ቀን ብኋላ “የተከበራችሁ ወንድሞቼ፤ እስከ አሁን አብሬያቹሁ በመሥራቴ እና ስላወኳችሁም ትልቅ ክብርና ደስታ ይሰማኛል። አብሬያችሁ ብዙ ርቀት ብጓዝና የትግሉንም መጨረሻ ባይ ደስ ይለኛል። ነገር ግን አሁን ካለሁበት የሥራ ባህሪና የሙያ ጏላፊነት አንጻር እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ስለገጠሙኝ ከዚህ በኋላ በዚህ ኮሚቴ ውስጥ መቀጠል ያማልችል መሆኔን ትልቅ ሀዘን እየተሰማኝ በታላቅ ትህትና እና አክብሮት ለመግለጽ እወዳለሁ፤ እጅግ አክባሪ ወንድማችሁ” በማለት አቶ ያሬድ ለቦርዱ መልቀቂያ ማስገባታቸው ከቦርዱ አባላት ለአዲስ ሪፖርተር መረጃ ተልኳል።

መልቀቂያቸውን ተከትሎ “በጣም አዝናለሁ፤ የጓጓንበት የሰከነ አመራርህ ገና ሳናጣጥም ለሟቋረጥ መወሰንህ ለግበረሃይሉ ከፍተኛ ጉዳት ነው፤ ሆኖም ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ካጋጠመህ መልካሙን በመመኘት ከኮሚቴው ውጭም ቢሆን በኢትዮጵያ ጉዳይ የበኩልህ አስተዋፅኦ እንደምታደርገና ከግብረ ሃይሉ ጎን እንደምተቆም በመተማመን ነው። Hope everything going to be oka” በማለት አቶ አባይ የተባሉት በቦርዱ የትህነግ ተወካይ ስሜታቸው ገልጸውላቸዋል።

አቶ ኃይለማሪያም እሳቸው በቦርድ አባልነት ያሉበትና በትናንትናው ዕለት በተሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያዊያን አመጽ እንዲያቀጣጥሉ ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል። ይህንኑ ስብስብ ከጀርባ ሆኖ የሚመራው ሻዕቢያ እንደሆነ በርካታ መረጃ ስለሚቀርብ፣ አዲስ ሪፖርተር አቶ ያሬድን በቃለ ምልልስ መልክ ሲሆን በዜግነት አጋብ ጥይቋቸው ነበር። ምንም እንኳን መደበኛ ቃለ ምልልስ ባይሆንም አዲስ ሪፖርተር አቶ ያሬድ ያሉበት ስብሰብ የሻዕቢያንና የግብጽን ጥምር አጀንዳ ያነገቡ የሚመሩት ስለመሆኑ በተደገጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

በቦርዱ ያሉት አብዛኞቹ ከተጠቀሱት “ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላት” ከሚባሉት ቡድኖችና አገራት ጋር ያላቸውን ግንኙነት የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ማስረጃ በማጣቀስ ሲዘገብ እንደነበር ይታወሳል። የዙም ስብሰባ ቅጂያቸውን በማተም ጭምር “ስለ ኤርትራ አታንሱ” በማለት በብሄራዊ ጥቅም ዙሪያ ለሚነሱ ጥያቄዎች አቶ ነዓምንና አቶ ገዱ ምላሽ ሲሰጡ፣ አቶ ያሬድም “ይህን መንግስት ለማውረድ ከማንም ጋር እንሰራለን” ብለው እንደነበር በወቅቱ ተመልክቶ ነበር።

አቶ ያሬድ እሳቸው የመሩት መግለጫ የተዘጋጀው በሻዕቢያ ሰዎች ስለመሆኑ ምን ያህል እውቂያ እንዳላቸው በስልክ ንግግሩ ወቅት ተነስቶላቸው ነበር። አገራቸውን በፍጹ ልባቸው የሚወዱና አቶ ኢሳያስን በግብራቸው አቶ ያሬድ፣እሳቸው በተገኙባቸው ከሶስት የማይበልጡ ስብሰባዎች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጻረር ጉዳይ ሲነሳ እንዳልሰሙ፣ ቢሰሙ በዝምታ እንደማያልፉ አመልክተዋል። በተለይ ለአቶ ኢሳያስ ክብር እንደሌላቸው እየገለጹ አሳባቸውን ሲገልጹ ስድብ እንደሚሰነዘርባቸው በስልክ ጭውውቱ ወቅት አስታውቀዋል።

በሰብአዊ መብት ተቆርቋቅሪነት የሚታወቁት አቶ ያሬድ በዚህ ስብስብ ውስጥ ገብተው ከእነ አቶ ጃዋር፣ በቅርቡ በከፍተኛ የጦር ወንጀል ከተከሰሰው ኦነግ ሸኔ ወኪል አቶ ጅሬኛ፣ አቶ ነዓምና በሻዕቢያ ታዘው ካደራጁት ኃይልናጋር በክህደት ከሚታወቁ ጋር መታየታቸው በርካቶችን አስገርሞ ነበር። በተለይም የመብት ተከራካሪ ሆነው በሰው ልጅች መብት ጥሰት ስማቸው ከሚነሱት ጋር መሰለፋቸው ግራ ያጋባቸው ጥቂት አልነበሩም።

“ምንም ዓይነት የፖለቲካ አቋም ቢኖራቸውን በዚህ መልኩ ኢትዮጵያን ለሌላ አካል አሳልፈው ለመስጠት ከሚማማሉ ጋር መታየታቸው ያስገረማቸው።እውነት አውቀውና አምነውበት ነው እዚህ ስብስብ ውስጥ የገቡት” በሚል አዲስ ሪፖርተር ጥያቄ እንድታቀርብላቸው የሚቀርቧቸው ሰዎች ብተደጋጋሚ አዲስ ሪፖርተር ስለቡድኑ የምታወጣውን ሪፖርት የሚከታተሉ ጠይቀው ነበር።

እንደማይታተም ተገልጾላቸው ከአዲስ ሪፖርተር ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት መነሻ ይሁን በሌላ ምክንያት ባይታወቅም ውይይቱ በተደረገ ማግስት አቶ ያሬድ በደፈናው ቦርዱን መሰናበታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ አስገብተዋል። ሌሎችም እሳቸውን ተከትለው እንደሚወጡ ይጠበቃል። ቀደም ሲል ፕሮፌሰር ሕዝቅዔል መሰናበታቸው የሚታወስ ነው። እሳቸው የራሳቸውን አዲስ ስብስብ እንደሚያቋቁሙ መግለጻችንም አይዘነጋም።

በቦርዱ ውስጥ ከሱዳን መንግስት ጄኔራል አልቡርሃንና ከሳቸው ጋር አብረው በይፋ ከሚሰሩት የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ ጋር  ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ እንዲሁም በቅርቡ በተፈጠረ “ጽምዶ” የተባለ ህብረት ትህነግ በገሃድ የተቀላቀለውን የሁለቱን አገራት ወታደራዊ ሰነሰልት ውስጥ ስላሉበት፣ የጄነራሉ በሽብርተኛነት መፈረጅ መዘዝ ያመጣብናል በማለት የፈሩ እንዳሉ አዲስ ሪፖርተር መረጃ ደርሷታል። የአቶ ያሬድ ሽሽትም ከዚሁ ጋር ይያያዝ አይያያዝ የታወቀ ነገር የለም። “ትዕይንተ-ሕዝቦች አዘጋጅ ግብረ-ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” ያስላስተላለፈው የትርምስ ጥሪ የተስፋ መቁርጥ እንደሆነ፣ በመግለጫው ላይ ይገናል የተባለው ጃዋር ግብጽ በመሄድ አስተላልፎት በነበረው መግለጫ ላይ አለመገኘቱ ከወዲሁ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

“ኦፐሬሽን ኢርቡ ሺኒጋ ፤ “የሰማዕታት ቃል ኪዳን” የጃዋር መሐመድ የህቡዕ ፕሮጀክት 

አዲስ ሪፖርተር - የስጋት ትንታኔ መስጠት እሰጣለሁ ባይ ነው።...

አሜሪካ የጄነራል አልቡርሃን  መንግስትን በሽብርተኝነት ፈረጀች፤ ውሳኔ ወዳጅ ለሆኑት ለኤርትራና፣ለትህነግ መርዶ ሆኗል

ጃዋር መሐመድና አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአልቡርሃን ደጋፊ ሆነው ኢትዮጵያን...

ኢትዮጵያ የUAE “ጉዳይ ፈጻሚ” (proxy)?!

የአፍሪካ ቀንድ የረዥም ጊዜ ቀጠናዊ ጥልፍልፎሽ (regional security complex)...

አስመራና መቀለ “ጽምዶ” የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት ተብሎ በይፋ ሊታወጅ እየተመከረ ነው፤

አዲስ ሪፖርተር - በትህነግ የሰዓት አቆጣጠር የጦርነት ማስጀመሪያ ግብአቶች...