ነዳጅ ከዋጋ ተመን በላይ የሚሸጡ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው፤ ከ 3 እስከ 10 ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ ተደረገ

Date:

አዲስ ሪፖርተር አዲስ አበባ የገንዘብ ሚኒስቴር በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ተከትሎ በዐለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የነዳጅ ዋጋ ንረት እና የአቅርቦት መስተጓጎል ለመቋቋም፣ በሀገር ውስጥ የነዳጅ ምርቶች ላይ በሌትር እስከ 10 ብር የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ።

የፌደራል የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በሰጡት መግለጫ፣ በነዳጅ ላይ አዲሱ የዋጋ ማሻሻያ ከመጋቢት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት በነጭ ናፍጣ ላይ በሊትር 10 ብር ጭማሪ ተደርጎ 139.84 ብር ገብቷል። በቤንዚን ላይ ደግሞ የ3 ብር ጭማሪ ተደርጎ በሊትር ወደ 132.18 ብር ከፍ እንዲል እና በኬሮሲን ላይም የ7 ብር ጭማሪ ተደርጎ 146.14 ብር እንዲሆን ተወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪም እንደ ፕሮጀክቶች፣ ማዕድን እና ፋብሪካዎች ያሉ “የቀጥታ ተጠቃሚዎች” የሚባሉ አካላት የአንድ ሊትር ናፍጣ ዋጋ 185 ብር እንዲሆን መደረጉን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ስኬታማ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እያደረገች መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ መንግሥት ለነዳጅ አቅርቦት በየዓመቱ ከአራት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ እንደሚመድብ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን የምንዛሪ ለውጥ ቢኖርም፣ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ መንግሥት በመቶ ቢሊዮኖች  የሚቆጠር ብር  የነዳጅ  ድጎማ እያደረገ መሆኑን አብራርተው፣ መንግሥት  አሁንም ቢሆን ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ወቅት የአለም የነዳጅ ዋጋ ጅቡቲ ላይ ከሚረከብበት ዋጋ አንጻር ሲታይ፣ መንግሥት በአንድ ሊትር ቤንዚን ላይ 73.56 ብር እንዲሁም በአንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ ላይ 98.29 ብር ድጎማ እያደረገ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

የገንዘብ ሚኒስሩ በህገወጥ ግብይት ላይ የተሰማሩ አካላትን አስጠንቅቀዋል። መንግሥት በውጭ ምንዛሪ ከፍተኛ ድጎማ የሚያደርግበት ነዳጅ ከተቀመጠለት የዋጋ ተመን በላይ በገበያ ላይ እየዋለ መሆኑ በጥናት ተደርሶበታል ብለዋል፡፡ አክለውም “በዚህ ህገወጥ የግብይት ሰንሰለት ላይ የተሳተፉ አካላት የመንግሥት ተቋማትንም ጨምሮ ወደ ህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ሥራ ተጀምሯል” ሲሉ ተናግረዋል።

“መንግሥት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እየመደበ እና ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ የሚያቀርበው ነዳጅ፣ በህገወጥ ነጋዴዎች እና ተባባሪዎቻቸው አማካኝነት መንግሥት ከወሰነው ዋጋ ውጪ እየተሰራ ያለው ሥራ በአፋጣኝ ቁጥጥር ስር ለማዋል የተጀመረው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል።

በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ጦርነት ምክንያት የአለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን የጠቀሱት ሚኒስትሩ፣ የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ከ69 ዶላር ወደ 98 ዶላር፣ የቤንዚን ዋጋ ደግሞ ከ75 ዶላር ወደ 139 ዶላር በበርሜል ማደጉን ለዋጋ ማሻሻያው እንደ ምክንያት አቅርበዋል።

በመጨረሻም ሚኒስቴሩ የአቅርቦት መስተጓጎልን ለመከላከል በአማራጭ መንገዶች አጣዳፊ የነዳጅ ግዢዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁሞ፣ መላው የነዳጅ ተጠቃሚ ማህበረሰብ ነዳጅን በከፍተኛ ቁጠባ እንዲጠቀም ጥሪ አቅርቧል።

“ሁሉም የነዳጅ ተጠቃሚ አካላት… ነዳጅን በከፍተኛ ቁጠባ መጠቀም እንዳለባቸው ማሳሰብ እንፈልጋለን፤ በቅርቡ በተጠና ሁኔታ ተጨማሪ የቁጠባ እርምጃዎች በቀጣይ ለህብረተሰቡ የሚገለጹ ይሆናል” በማለት አስረድተዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የ“ትዕይንተ ሕዝቦች አዘጋጅ ግብረ ኃይል የቴክኒክ ኮሚቴ” የአመጽ ጥሪ መግለጫ የመሩት ያሬድ በማግስቱ የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገቡ

አዲስ ሪፖርተር - በትናንትናው ዕለይ ራሱን “ትዕይንተ ሕዝቦች አዘጋጅ ግብረ-ኃይል...

“ኦፐሬሽን ኢርቡ ሺኒጋ ፤ “የሰማዕታት ቃል ኪዳን” የጃዋር መሐመድ የህቡዕ ፕሮጀክት 

አዲስ ሪፖርተር - የስጋት ትንታኔ መስጠት እሰጣለሁ ባይ ነው።...

አሜሪካ የጄነራል አልቡርሃን  መንግስትን በሽብርተኝነት ፈረጀች፤ ውሳኔ ወዳጅ ለሆኑት ለኤርትራና፣ለትህነግ መርዶ ሆኗል

ጃዋር መሐመድና አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የአልቡርሃን ደጋፊ ሆነው ኢትዮጵያን...

ኢትዮጵያ የUAE “ጉዳይ ፈጻሚ” (proxy)?!

የአፍሪካ ቀንድ የረዥም ጊዜ ቀጠናዊ ጥልፍልፎሽ (regional security complex)...