ጄ.አልቡርሃን በአሸባሪነት ከተፈረጁ በኋላ፤ የፋኖ ስም ተከተለ፤ ፋኖ አሸባሪ ነው?

Date:

የአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን (ICE) በይፋዊ የX ገጹ ያሰራጨው መረጃ አስከትሎት የመጣው ውዝግብና ጭንቀት ቀላል አልሆነም። በተለይም ከሱዳኑ መሪ ጄነራል አልቡርሃን በአሸባሪነት መፈርጅ ጋር ተከታትሎ ፋኖን ሶስተኛ ደረጃ የሽብር ጠለል ስር በመመደብ የወጣው መግለጫ ጭንቀቱን አክብዶታል። ስሙና ማንነቱ ተጠቅሶ ከአሜሪካ መባረሩ የተገለጸለት ኢትዮጵያዊ የፋኖ አባልና ደጋፊ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎችና ቪዲዮዎች ይፋ መሆናቸው ደግሞ ጉዳዩን ትልቅ አጀንዳ በማድረጉ በየአቅጣጫው ብዙ እየተባለ ነው።

“ሰለሞን ቦጋለ ማን እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም፣ ነገር ግን ፋኖ ከሽብርተኝነት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ምንም ጥርጥር ሊኖር አይገባም። ፋኖ በመንግስት ለሚመራው ጥቃት እና ስደት ምላሽ ለመስጠት የተቋቋመ የአማራ ህዝብ ራስን የመከላከል ንቅናቄ ነው። ፋኖን የሽብር ድርጅት አድርጎ የሚፈርጅ ማንኛውም አባባል ፖለቲካዊ ትርክትን የሚያንፀባርቅ እንጂ የአማራ ማህበረሰብ ያለበትን ተጨባጭ ሁኔታ አይወክልም። እባካችሁ ይህን የተሳሳተ መረጃ አርሙት” በማለት ቀደም ሲል ኤርትራ ገብተው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር ከተገናኙት የትጥቅ ትግል አራማጅ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የነበሩት አቶ የኤፍሬም ማደቦ የጻፉትን አቶ ነዓመን ዘለቀ በኤክስ ገጻቸው አጋርተዋል። አቶ ነዓምን በሻዕቢያ የሚረዳውን የዲያስፖራ ክንፍ የሚያደራጁ መሆናቸው ይታወቃል።

“አቶ በምስራቅ አፍሪካ ጂኦፖለቲካ ተንታኝነቱ የሚታወቀው ራሺድ አብዲ (Rashid Abdi) “ፋኖ የእስልምና ሚሊሻ ቢሆን ኖሮ፣ በአለም አቀፍ ኃይሎች በፍጥነት ‘አሸባሪ’ ተብሎ በተፈረጀ ነበር” ሲሉ አቶ ነዓምን ከአቶ ኤፍሬም ቀድተው ላሰራጩት መልዕክት ምላሽ ሰጥተዋል።

“ሰዎችን በህይወት ማቃጠል፣ ወይም የሰውን ጭንቅላትን በዱላ ላይ ሰክቶ ማሳየት ፋኖ የሚፈጽመው የመካከለኛው ዘመን አረመኔነት በቀጥታ ከእስላማዊ መንግስት (ISIS) ጋር ያመሳስለዋል” በሚል ሞግተዋል። በዚሁ አቶ ነዓምን ባጋሩት መረጃ ስር ብዙ ብዙ ተብሏል።

የዚህ የከረረ ጉዳይ መነሻ የአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን (ICE) ያሰራጨው የአቶ ሰለሞን ቦጋለ የተባለ ኢትዮጵያዊ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና በዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ምክንያት ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ መላኩን ይፋ ካድረገ በኋላ ነው።

መግለጫው በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ሲሰራጭ መነጋገሪያ የተደረገው የተጠቀሰው ወንጀል ሳይሆን፣ የአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን አቶ ሰለሞንን “የፋኖ አባል” አድርጎ መግለጹና ፋኖን ሶስተኛ ደረጃ የሽብርተኛ መደብ ላይ ማስቀመጡ ነው።

አሜሪካ “ፋኖ”ን Tier III ወይም ምድብ ሶስት ሽብርተኛ ቡድን መፈረጇ ከፋኖ ጋር በተያያዘ በይፋ የውጭ አፈር ወኪል ነን በሚሉ፣ ፋኖን በገንዘብና በሚዲያ በሚያግዙ፣ እንዲሁም አደረጃጀቱን በውጭ አገር ሆነው በይፋ የሚመሩና እንደሚመሩ ለሚገልጹ የተለያዩ ወገኖች ዜናው አስደንግጧል። አነጋጋሪ ሆኗል።

ሰለሞን የተባለው ግለሰብም የተወነጀለው ቀደም ሲል በነበረው ጦርነት ወቅት “በትግራይ ተወላጆች ላይ ” የዘር ማጽዳት ” እንዲካሄድ እና ጥቃት እንዲሰነዘር በማህበራዊ ሚዲያ ሲቀሰቅስ ነበር” ተብሎ ሲሆን፣ ዜናው ስጋት የሆነባቸው ክፍሎች “ለምን ዛሬ ተመርጦ ይህ ጉዳይ ተነሳ? ከጄነራል አልቡርሃን አሸባሪ ተደርጎ መፈረጅ ጋር ለምን ተከታተለ?” የሚል ጥያቄ እያነሱ ነው።

የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ በርካታ ችግሮችን የተሸከመ፣ በደል የደረሰበት እንደሆነ የሚያምኑ፣ ነገር ግን የአማራን ሕዝብ ችግር ለመታደግ በሚል የሚደርገውን ትግል አካሄድ፣ የሚፈጸመውን አስነዋሪ ተገባራት የሚቃወሙ በበኩላቸው “የሚሆነውን ማየት ነው” እያሉ ነው።

ትህነግ፣ ሻዕቢያ፣ ፋኖ ህብረት ፈጥረዋል ተብሎ በይፋ በሚነገርበት በአሁኑ ሰዓት፣ ይህ ጥምረት ደግሞ ከሱዳንና ግብጽ ጋር አብሮ እንደሚሰራ መረጃ መውታቱ፣ ግብጽ፣ ሱዳንና ኤርትራ በገሃድ ከኢራን ጎን መሆናቸው ዜናውን ሊያወሳስበው እንደሚችል የሚናገሩም አሉ።

አሚሪካ ወደ አገሩ ላኩት ያለችው አቶ ሰለሞን፣ በአሪዞና፣ ፊኒክስ ባሉ የICE አባላት አማካኝነት እ.ኤ.አ መጋቢት 5 ተይዞ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል።

ICE እ.ኤ.አ. ከ2003 ጀምሮ በጦር ወንጀል እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚጠረጠሩ ወይም የተፈረደባቸውን 1,178 ግለሰቦችን ከአሜሪካ ማባረሩ ይታወቃል። “አሜሪካ እንዲህ አይነት ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች መደበቂያ እንዳትሆን የትራምፕ መነግስት ከወትሮው በተለየ አቋም መያዙ ስለሚታወቅ ውሳኔው የዚሁ አካል እንደሆነ ተመልክቷል።

ከላይ የተጠቀሰው እንደ መግቢያ ይሁንና ለመሆኑ አሜሪካ ” ፋኖን ” በይፋ አሸባሪ ቡድን ብላ ፈርጃለች? ወይስ ዜናውን የተለያዩ ወገኖች ከራስ የፖለቲካ ፍላጎት ጋር በማሳሳም አጦዙት ።

ይህን ጉዳይ እንዲያብራራልን አቶ ጃዋርን ጠይቀን ነበር። አቶ ጃዋር ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆነም። በሮመዳን ጾም ላይ እንደሆነ ጠሰው አሁን ላይ ምላሽ እንደማይሰጥ የቅርብ ወዳጃችርው ነገረውናል። አቶ ጃዋርን የመረጥነው በተመሳሳይ ክስ ተሰምቶባቸው ከጠበቃቸው ጋር ተነጋግረው ክስ ለመመስረት ዝግጅት ላይ እንዳሉ ገልሰው ስለነበር ነው።

የአሜሪካ ኢሚግሬሽንና ጉምሩክ ባለስልጣን የፋኖን ስም አንስቶ “Tier III ” ወይም ምድብ ሶስት ደረጃ ላይ የሚቀመጥ የሽብር ስም ሰጥቷል። ለመሆኑ አንድ ሁለት ሶስት የተባሉት የሽብር ቡድን መለያዎች ምንድን ናቸው? በመግለጫው ላይ አቶ ሰለሞን የፋኖ አባል መሆኑ ተጠቅሶ፣ ፋኖ ምድብ ሶስት ላይ ተመድቧል።

ምድብ ሶስት የሚባሉት “ያልተፈረጁ ወይም Undesignated ” ቡድኖች ተብለው ነው የሚገለጹት። የአሜሪካ  ኢሚግሬሽን ህግ እነዚህን ምድብተኞች በኢሚግሬሽን አግባብ እንደ ሽብር ቡድን ያያቸዋል።

በአሜሪካ ህግ ትርጓሜ “በሽብር ተግባር ውስጥ የሚሳተፍ ወይም በሽብር ተግባር ውስጥ የሚሳተፍ ንዑስ ቡድን ያለው፤ የተደራጀ ቢሆንም ባይሆንም የሁለት ወይም ከዚያ በላይ ግለሰቦች ስብስብ” ተብሎ ይቀመጣል።

Tier III (ምድብ 3) ድርጅቶች “በይፋ ያልተፈረጁ የሽብር ድርጅቶች/undesignated terrorist organizations” ተብለው የሚጠሩት እንደ ምድብ 1 እና ምድብ 2 ድርጅቶች ይፋዊ የመፈረጅ ሂደት ውስጥ ማለፍ ሳያስፈልጋቸው በሚያከናውኗቸው ተግባራት ብቻ እንደ ሽብር ቡድን ለመጠራት ብቁ ስለሚሆኑ ነው ሲል ህጉ ያብራራል።

አንድ ቡድን እንደ Tier III (ምድብ 3) ሊቆጠር የሚችለው የኢሚግሬሽን ጥቅማጥቅም ጥያቄ በሚገመገምበት ወቅት ሲሆን እንደየ ጉዳዩ ሁኔታ የሚወሰን ነው። ምድብ 3 ውስጥ ያሉ አካላት በየጊዜው የሚፈጠሩ እና በሂደትም የሚለዋወጡ ናቸው።

እስካሁን ባለው መረጃ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት “ፋኖ “ን በ “Foreign Terrorist Organization/ የውጭ አሸባሪ ድርጅት” ዝርዝር ውስጥ አላካተተም። ለመሆኑ አሜሪካ በ3 ዋና ዋና ምድቦች ከፍላ የምታየው የሽብርተኛ ፍረጃ መካከል ሶስተኛው ምን ይላል?

ነበTier III ምድብ ሶስት ስር ከሚካተቱ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው ወይም የደገፉ ግለሰቦች ወደ አሜሪካ ለመግባት ቪዛ ወይም የጥገኝነት መብት ሲጠይቁ ጥያቄያቸው ውድቅ እንዲሆንባቸው እንደ ምክንያት ሊጠቀስባቸው ይቻል። በዝርዝር ባይቀመጥም ከነዚህ አካላት ጋር በገንዘብ፣ በቁስ፣ በተገባር እንቅስቃሴዎች መተባበር እዚህ ውስጥ እንደሚካተቱ የህግ ሰዎች ይናገራሉ።

“Tier III (ምድብ 3)” በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት እንደ ምድብ አንድ በይፋ ” የውጭ አሸባሪ ድርጅት (FTO) ” ተብለው የሚፈረጁ አይደሉም። እነዚህ ” በዝርዝር ውስጥ ያልሰፈሩ (Undesignated) ” ነገር ግን በሽብር ተግባር ውስጥ የተሰማሩ ቡድኖችን የሚገልጽ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን መጠሪያ ነው።

አንድ ቡድን እንደ Tier III (ምድብ 3) ሊቆጠር የሚችለው የኢሚግሬሽን ጥቅማጥቅም ጥያቄ በሚገመገምበት ወቅት ሲሆን እንደየጉዳዩ ሁኔታ የሚወሰን ነው። ምድብ 3 ውስጥ ያሉ አካላት በየጊዜው የሚፈጠሩ እና በሂደትም የሚለዋወጡ ናቸው።

እስካሁን ባለው መረጃ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት “ፋኖ “ን በ “Foreign Terrorist Organization/ የውጭ አሸባሪ ድርጅት” ዝርዝር ውስጥ አላካተተም።

ነገር ግን በTier III (ምድብ 3) ስር ከተካተቱ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ያላቸው ወይም የደገፉ ግለሰቦች ወደ አሜሪካ ለመግባት ቪዛ ሲጠይቁ ወይም የጥገኝነት መብት ሲጠይቁ ለመከልከል እንደ ምክንያት ሊጠቀስባቸው እንደሚችል መረጃዎች ያሳያሉ።

” Tier III (ምድብ 3) ” በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት እንደ ምድብ አንድ በይፋ ” የውጭ አሸባሪ ድርጅት (FTO) ” ተብለው የሚፈረጁ አይደሉም። እነዚህ ” በዝርዝር ውስጥ ያልሰፈሩ (Undesignated) ” ነገር ግን በሽብር ተግባር ውስጥ የተሰማሩ ቡድኖችን የሚገልጽ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን መጠሪያ ነው።

እንግዲህ የአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ ማስከበርያ (ICE)፣ ሰሎሞን ቦጋለ የተባለ ኢትዮጵያዊ በሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በሚሊሻ (Paramilitary) አባልነት እና በዘር ማጥፋት ቅስቀሳ ተጠርጥሮ ወደ ኢትዮጵያ መባረሩን ተከትሎ አየሩን የያዘው መረጃ በዚህ መልኩ የሚታይ እንደሆነ ከተለያዩ ሚዲያዎችና ባለሙያዎች ያሰባሰብነው መረጃ ይህን ይመስላል።

እንደ የህግ አስከባሪ ተቋሙ መግለጫ፣ ግለሰቡ ወደ ኢትዮጵያ የተባረረው መጋቢት 5 ቀን (March 5) ሲሆን፣ ለውሳኔው መነሻ የሆኑት ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡

የሽብር ቡድን አባልነት፡ግለሰቡ በፊኒክስ የኢሚግሬሽን መኮንኖች ክትትል ሲደረግበት የቆየ ሲሆን፣ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ራሱን የ”ፋኖ” (እንደ ICE አገላለጽ Tier III የሽብር ቡድን) አባል አድርጎ ሲያስተዋውቅ ተገኝቷል።

የጥላቻ ንግግር እና ቅስቀሳ፡ ሰሎሞን ቦጋለ በማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎቹ በትግራይ ተወላጆች ላይ ስደት እና ጥቃት እንዲፈጸም፣ እንዲሁም “የዘር ማጽዳት” (Cleansing) እርምጃ እንዲወሰድ ሲቀሰቅስ እንደነበር ተገልጿል። አሁን ላይ ፋኖና የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ህብረት ፈጥረው እየሰሩ መሆኑን እየገለጹ መሆናቸው አይዘነጋም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የክፉ ጊዜ ወዳጅነት፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኤምሬትስ ጉብኝት አንድምታዎች  

      የኢትዮጵያን ቀጠናዊ የበላይነት ለማረጋገጥ የሚከፈለው መስዋዕትነት ታሪካዊ ዋጋ...

ማርኮ ሮቢዮ ከአብይ ጋር መከሩ፤ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ በቀይ ባህርና በአፍሪቃ ቀንድ አሰላለፋቸው ይፋ እየሆነ ነው

አዲስ ሪፖርተር - አሜሪካ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የጠብመንጃ ግብግብ...

How Ethiopia Anchors the Horn Against Sudan’s Ongoing War

Civil wars are often explained as the inevitable eruption...