በብልሹ አሰራር ሳቢያ የአፈር ማዳበሪያ ግዢ በጠ/ሚ ጽሕፈት ቤት እንዲመራ ተወሰነ

Date:

ከቅርቡ ከቻይና ወደ ኢትዮጵያ የገባውን ደረጃውን ያልጠበቀ ማዳበሪያ ግዥ ተከትሎ ወሳኝ በሆነው የግብርና ግብዓት አቅርቦቶች ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት እንዲቆጣጠር መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት አስታውቋል። ተፈጸመ የተባለው ብልሹ አሰራር እየተመረመረ ነው።

ፅሕፈት ቤቱ ከቻይና የገባውን ደረጃውን ያልጠበቀ ማዳበሪያ ግዢ አስመልክቶ እንከኑን የሚመረምር ልዩ የተባለ ኮሚቴ ማቋቋሙን፣ የተቋቋመው ኮሚቴ የማታራት ስራውን እየሰራ መሆኑ በተገለጸበት ዜና ከዚህ በኃላ የአፈር ማዳበሪያ ግዢና ወሳኝ የግብርና ግብዓቶች ግዢ በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት እንዲመራ ውሳኔ ላይ መደረሱን ታውቋል።

ቀደም ሲል ከውጭ አገር የሚገባው የአፈር ማዳበርያ የቁጥጥር ሂደቱን በግብርና ሚኒስቴር በኩል የሚመራና በግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) በበላይነት ቁጥጥር ሲደረግለት እንደነበር የሚታወቅ ነው። አሁን ላይ የተፈጠረውንና እየተመረመረ ያለውን ብልሹ አሰራር ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት የቁጥጥር ሒደቱን ይከታተላል ተብሏል።

ባለፉት ጊዜያት ማዳበሪያ ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገባበትን ሂደት የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽንን ጨምሮ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት የቁጥጥር ሂደቱን የሚከታተሉት ነበር ተብሏል ።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽንን (ኢግሥኮ) እና የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት (ኢባትሎ) ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም የቦርድ ሰብሳቢዎች ሙሉ ለሙሉ መቀየራቸውንና ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ከደረሱ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቢኔያቸው ኃላፊ ቦርዱን በቀጥታ እንዲመሩ መሾማቸውን ተገልጿል።

ወደ አገር ውሰጥ የሚገባውን የአፈር ማዳበሪያ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ቀጥተኛና ወሳኝ የተባሉትን የስራ እንቅስቃሴዎች ቁጥጥር እንደሚያካሂድና አዲስ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ የተሰየመዉ ቦርድ የሚመራ መኾኑንና እንዲሁም የቦርዱ ሰብሳቢ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ ሆነው መሾማቸውን ታውቋል።

በተጨማሪም በግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢግሥኮ) ቦርድ አባላት የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋን ምክትል ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸውንና የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማን ጨምሮ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴን የቦርዱ አባላት ሆነው መሰየማቸውን ፅህፈት ቤቱ አስታውቋል ።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...