ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት!! እንኳን አደረሳችሁ እንላለን

Date:

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት “እያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን” ነን። መከላከያችን እኛነታችን፣ ሕልውናችን፣ የመጨረሻ መመሸጊያችን፣ የሰላማችን ሚስጢርና ቁልፍ ነው። መከላከያችን በደሙ፣ በአጥንቱ፣ በህይወቱ አገር እያጸና እዚህ ያደረሰን የዓይናችን ብሌን ያህል የምንሳሳለት ነው። መከላከያችንን የምናከብረውና የምንሳሳለት፣ ደማችንን የምናካፍለው በዚሁ መነሻ ነው። እንኳን ለ118ኛው የምስረታ ቀን በዓል አደረህ ስንል ራሳችንንም አካተን ነውና ለዚህ ቀን በመብቃታችን ኢትዮጵያዊያን ኩራታችን ትልቅ ነው።

በዚህ ስሜትና ክብር ሆነን በመከላከያችን ላይ ጣታቸውን የሚቀስሩ፣ የሚዛበቱና ቃታ የሚስቡትን ሁሉ እናቃወማለን። በእንዲህ ያለ ተግባር የተሰማሩ ሁሉ ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ጋር የተጣሉ ቅጥረኞች ናቸው ብለን እንፈርጃለን። መከላከያችን እንከን እንኳን ቢኖርበት እያረቅን እናጠነክረዋለን እንጂ ለጠላት አሳብና ህልም አሳልፈን አንሰጠውም። ይህ አይሆንም። አይደረግም። አይታሰብም። የሚያስቡና እንደ ቀድሞው እናደርጋለን ብለው ለሚውተርትሩ “ሲያምራችሁ ይቅር” እንላቸዋለን።

“ወጣ ወረደ ሄድ ነጎደ ሰራዊቱ!”
እንኳን ለ118ኛ የመከላከያ የምስረታ ቀን አድረሳችሁ፣ አደረሰን!

ኢትዮጵያዊያን ያኔ እብሪተኛዋን ወያኔ የተቃወምነው ለትግራይ ህዝብ ጥላቻ ኑሮን አልነበረም። ወይም ብልፅግናን ደግፈን ዳረጎት ስለተሰፈረልን አይደለም። ይልቅስ የሃገር ደህንነት ዋስትናችን የሆነውን መከላከያ ሰራዊት ከጀርባው ወግተው አንገታችን ስላስደፉን ነው። ስላፈሩንና ክህደትን በአደባባይ ስላሳዩን ነው። አሁንም በማናቸውም የዘውጌ ብሄርተኛ ታጣቂዎች ጥላ ከለላችን በሆነው፣ መከላከያ ሰራዊቱ ላይ የሚፈፀሙ የክህደት ጥቃቶችን የምንቃወመው በተመሳሳይ ስሜት ነው።

ጥላ ከለላህን ጠብቅ!

ሰርጌ ራስቶርጎቨ (Sergei P. Rastorguev) የድብልቅ የመረጃ ወይም የስነ ልቦና ጦርነት (hybrid information warfare) ተንታኝ ነው። ይህ ጦርነት ሃገራችንን (የበለፀጉ ሃገሮችንም ጭምር) እያሸበረ እና ሃገራትን አፅንተው ያቆዩ እሴቶችን በመበጣጠስ ወደ ገደል አፋፍ እየወሰደ ይገኛል። ሰርጌ ስለዚህ ጦርነት ዋና ግብ በሚከተለው መልኩ በኤሊ እና ቀበሮ ምሳሌ ጠቅለል አድርጎ አቅርቦታል። ከለታት አንድ ቀን አያ ቀበሮ ኤሊን አድኖ ለመብላት ቢሞክርም ኤሊ ግን ቶሎ ወደ ጉያዋ (shell) እየገባች አስቸገረችው። ቀበሮ ጉያዋን በብር ለመግዛት ቢሞክርም ኤሊ ጠባቂ መከታዋን ከሸጠች እራቁቷን ለአደን ተጋላጭ መሆኗን ተረድታ እምቢ አለች።

ጊዜው ነጎደ። አንድ ቀን ኤሊ ዘና ብላ ሳር እየነጨች ሳለች፣ ዛፍ ላይ በተሰቀለው የቴሌቪዥን መስኮት ውስጥ ኤሊዎች እራቁታቸውን ክንፍ አውጥተው እየተሳሳቁ በጋራ ሲበሩ ተመለከተች፣ ደነገጠች። ‘ራቁት መብረር ለደህንነታቸው ስጋት አይሆንም?’ እያለች ብቻዋን እያጉረመረመች ሳለ አንድ ማስታወቂያ አስተጋባ፡ “አያ ቀበሮ ከዛሬ ጀምሮ አትክልት ተመጋቢ (vegeterian) መሆናቸውን ገለፁ” የሚል። ይህን በሰማች ጊዜ “እስከመቸ ጉያየ ውስጥ ተደብቄ እኖራለሁ፣ እንደ ባልንጀሮቼ ዘና ብየ እንድኖር ይህን ቋጥኝ ከላይቴ ላይ አውልቄ መጣል አለብኝ” እያለች ማሰላሰል ጀመረች።

ቀበሮም የኤሊን ምኞትና ፍላጎት ስለተረዳ “የሚበሩትን ኤሊዎች” ማስታወቂያ ብዙ ገንዘብ በማውጣት በዓለም ዝነኛና ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃን ደጋግሞ እንዲነገር አስደረገ። የፌስቡክ፣ የቲውተርና ዩትዩብ ad እየገዛ ማስታወቂያውን በኤሊ ግዛት ውስጥ forced popup እያደረገ እንዲታይ ሆነ። ኤሊ ከቴሌቭዥኑ ባለፈ በእጅ ስልኳ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ተመለከተች፣ የጭቆና ስሜት ይበልጥ ተሰማት። ቋጥኟን መጣል እንዳለባት አመነች። አንድ ቀን ጧት፣ ምስኪን ኤሊ ሃገር ሰላም ብላ ቋጥኟን፣ ጥላ ከለላዋን፣ ጠባቂዋን ከላይዋ ላይ አውልቃ ጣለች። አያ ቀበሮም ይች ቀን እንደምትመጣ ያውቅ ነበርና በትዕግስት ጠብቆ ህልሙ ተሳካለት። የኤሊን ግዛት ወርሶ እንዳሻው ተንፈላሰሰበት።

እኛም እንደኤሊ እየተታለልን ነው። ጥላ ከለላዎቻችንን፣ ከፋም ለማም የሰላምና ደህንነት ቋሚ ዋስትናዎቻችንን ሌላ አማራጭ ያለን ይመስል እምነት እንዳናጥልባቸው እየተደረገ ነው። አውልቀን እንድንጥላቸው ድብልቅ የሆነ ከፊል እውነት ከፊል ውሸት፣ ነጭ ውሸት፣ አንዳንዴም በእውነት ብቻ የተቀነበበ አሳማኝና ግልፅ ትርክት እየጋቱን ይገኛል። እኛም ጊዜ ሰጥተን ከሃገራችን ብሄራዊ ጥቅምና ዘላቂ ደህንነት አንፃር ትርክቱን ከመመርመር ይልቅ ወጥመዱ ብሄራችንን፣ ጎጣችንን፣ አጥቢያችንን፣ አንዳንዴም ሃገራችንን እየጠቀመን እየመሰለን ካላፈረስናቸው ብለን ያዙኝ ልቀቁኝ እያልን ነው።

ካልነቃን ሃገራችንን ማጣታችን ነው!

ጥላ ከለላችን፣ የሃገራችን ሰላም፣ ደህንነትና ሉዓላዊነት የሆነውን መከላከያ ሰራዊታችንን ከማናቸውም ጊዜ በበለጠ ልንደግፈው ይገባል። ላብና ደሙን የሚያፈሰው አጥንቱን የሚከሰክሰው ሰራዊት ሞራሉን፣ ክብሩንና ዝናውን ልንጠብቅለት ቃላችንን ማደስ አለብን። ከትንሹ like and share እስከ ትልቁ የሕይወት መስዋዕትነት ድረስ ከጎኑ ልንሆን ይገባል።

ዛሬ የሠራዊታችን የምስረታ ቀን ነው! እንኳን አደረሳችሁ።
የኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት በዘመናዊ መልኩ “በጦር ሚኒስትር” ደረጃ የተደራጀው በዘመነ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም ነው። ይህንኑ ታሪካዊ እለት በማስመልከት ነው ቀኑ ለመከላከያ ሠራዊት ቀንነት የተመረጠው። በዚሁም መሠረት 118ኛው የሠራዊት ቀን “የማትደፈር ሃገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ ቃል ቢሾፍቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ማሠልጠኛ ማዕከል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል። ክብር ለመከላከያ ሠራዊት!!

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...