ካይሮ ያቀኑት ኢሳያስ “ግብፅ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት አደንቃለሁ” አሉ፤ ግብጽ ለኤርትራ ሉዐላዊነት “የማይናወጥ ድጋፍ አለኝ” አለች

Date:

ኢዲስ ሪፖርተር ካይሮ — የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በትላንትናው እለት ወደ ካይሮ በማቅናት ዛሬ ከግብፁ አቻቸው አብደል ፈታህ አልሲሲ ጋር የተወያዩ ሲሆን፣ ውይይቱ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የኃይል ሚዛን ለመቀየርና በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠረ ስትራቴጂካዊ ከበባን የሚያሳይ እንደሆነ ጉዳዩን የሚከታተሉ ተንታኞች እየገለጹ ነው።

የግብፅ ፕሬዝደንት ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ መሪዎቹ በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በሱዳን ቀውስ እና በቀይ ባህር ደህንነት ዙሪያ መክራቸውን ይፋ አድርጓል። የፕሬዝደንት ኢሳያስ “ግብፅ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የምታደርገውን ጥረት አደንቃለሁ” ማለታቸው፣ ካይሮ በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ጋር ባላት ፍጥጫ ዙሪያ እየተከተለችው ካለው የጂኦ-ፖለቲካ እንቅስቃሴ አንጻር ትልቅ ትርጉም ያለው እንደሆነ ተመልክቷል። መልዕክቱም ግልጽ እንደሂነ ተገልጿል።

የካይሮ ስትራቴጂ፡ ኢትዮጵያን በሶስት አቅጣጫ የመክበብ እቅድ?

የቀጠናው የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ ይህ የሁለቱ መሪዎች የድንገት በሚመስል መልኩ መገናኘት በይፋ ከተነገረው የኢኮኖሚና የንግድ ትብብር በላይ የጠለቀ የወታደራዊና የዲፕሎማሲ ስሌት አለው። ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ (GERD) ሳቢያ ከኢትዮጵያ ጋር የገባችበትን የከረረ ውጥረት ተከትሎ፣ አዲስ አበባን በአጎራባች አገራት በኩል የመክበብ ስትራቴጂ (Encirclement Strategy) በግልጽ እየገፋችበት እንደሆነ ይታወቃል።

  • በሱዳን በኩል፡ በሱዳን ካለው የርስበርስ ግጭት ጀርባ የራሷን ተፅዕኖ በማጠናከር በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ድንበር ላይ ጫና መፍጠር፤
  • በሶማሊያ በኩል፡ ከሞቃዲሾ ጋር የጦር ቃልኪዳን በመፈራረም እና ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ በመላክ በኢትዮጵያ ምስራቃዊ ድንበር ላይ ስጋት መጋረጥ፤
  • በኤርትራ በኩል (አዲሱ ምዕራፍ)፡ ከአስመራ ጋር የባህር ትራንስፖርትና ወታደራዊ ትብብሮችን በማጠናከር፣ በሰሜን አቅጣጫ የኢትዮጵያን በር መዝጋት።

የአስመራ ስጋት፡ “የኢትዮጵያ ፍርሃት” የፈጠረው ጥምረት?

በውይይቱ ወቅት ፕሬዝደንት አል-ሲሲ ለኤርትራ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ያላቸውን “የማይናወጥ ድጋፍ” ማረጋገጣቸው፣ አስመራ በአሁኑ ወቅት ካለባት “የኢትዮጵያ ፍርሃት” የመነጨ መሆኑን ተንታኞች ያሰምሩበታል። የጉዟቸውም ዋና ምክንያት ዋስትና ፍለርጋ መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑ ተመልክቷል።

የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊና ስትራቴጂካዊ ጥረት እንደ ቀጥተኛ የሉዓላዊነት ስጋት የሚመለከተው ሲሆን፣ ይህ የኢትዮጵያ ስጋት ፕሬዝደንት ኢሳያስን ግብፅ እቅፍ ውስጥ እንዲገቡ ገፊ ምክንያት እንደሆነ፣ ይህ ስጋት ግብጽ ኢትዮጵያ ወደ ቀይ ባህር እንዳትገባ ካላት የኖረ ፍላጎት አንጻር የሚደገፍ መሆኑ በተደጋጋሚ በባለሙያዎች ሲገልጽ ቆይቷል። አስመራ ይህንን ስጋቷን ለመመከት የካይሮን ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ እንደ ዋስትና ለመጠቀም ደፋ ቀና ማለቷና ግብጽም የኤርትራን ጥያቄ መቀበሏ ብዙም አስገራሚ እንዳልሆነ እነዚሁ ወገኖች ደጋግመው አመልክተዋል።

የትችት ነጥብ፡ ፕሬዝደንት ኢሳያስ ግብፅ በቀጠናው “ሰላምና መረጋጋት” ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት ማድነቃቸው አስገራሚ ሆኖ ተገኝቷል። ግብፅ በሱዳን ግጭት ውስጥ የራሷን ጥቅም ለማስጠበቅ የምታደርገው ጣልቃ ገብነት እና በሶማሊያ የምታሳየው ወታደራዊ ጡንቻ ማሳየት ቀጠናውን ወደ በረታ ቀውስና የጦርነት አዙሪት እየገፋው ባለበት ወቅት፣ ይህንን እንቅስቃሴ “ለሰላም የሚደረግ ጥረት” ተብሎ መገለጹ የዲፕሎማሲያዊ ግብዝነት ማሳያ ነው በሚል እየተተቸ ነው።

የባህር ትራንስፖርት ስምምነቱ እና ቀጣዩ ምዕራፍ

ፕሬዝደንት ኢሳያስ ወደ ካይሮ ያቀኑት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የትራንስፖርት ሚኒስትር በአስመራ ተገኝተው የባህር ትራንስፖርት ትብብር ስምምነት ከተፈራረሙ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው። ይህ የሚያሳየው ስምምነቱ የንግድ ብቻ ሳይሆን፣ ግብፅ በቀይ ባህር እና በኤርትራ ወደቦች ላይ ያላትን ወታደራዊና የባህር ኃይል ተደራሽነት ለማስፋት የተነደፈ ስትራቴጂ መሆኑን ነው።

ባጠቃላይ፣ የካይሮ እና አስመራ ጋብቻ የኢኮኖሚ ትብብር ሽፋን የተሰጠው ቢሆንም፣ ዋና ግቡ ግን ኢትዮጵያን በሁሉም አቅጣጫ በመክበብ ቀጠናዊ ተፅዕኖዋን ማዳከም እና ለአስመራ ደግሞ የህልውና ስጋት ከተባለችው አዲስ አበባ እራሷን የመከላከያ ስሌት መሆኑን የክስተቱ ሂደት በግልጽ ያሳያል።

ይህ ዘገባ በአፍሪካ ቀንድ ካለው ወቅታዊ የጂኦ-ፖለቲካ ፍጥጫ አንጻር የተጠናቀረ የትንተና ዜና ነው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አንደበት የቆለፈው የትራምፕ መመሪያ ተቃዋሚዎች ተስፋ አስቆርጧል፤ አሜሪካ ስለምርጫው ለምን ዝም አለች?

አሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ የአገሪቱ ዲፕሎማቶች በሌሎች አገራት...