ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

Date:

“በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ የለም በግል የሎቢና የማሳመን ስራ ይቅደም” የሻዕቢያ ወኪል ነዓምን

አዲስ ሪፖርተር – አብዛኞቹ ከድርጅት ይልቅ በግል እንደመጡ ተናግረዋል። ጃዋር በስብሰባው እንደሚሳተፍ ይፋ ከሆነ በኋላ ቀርቷል። አንድም የኦሮሞ ተወካይ አልተገኘም። አቶ ልደቱና ኢንጂነር ሙሉጌታ “ሰብሳቢ አይደለንም” እያሉ ይደጋግማሉ። አስራ ሰባት ሰዎች ተጠርተው የተገኙት ዘጠኝ ብቻ ናቸው። የፕሪቶሪያው ስምምነት ሲፈረም ከሻዕቢያ ጋር ሆነው በኩርፊያ ከለውጡ ባቡር የዘለሉት ኤርትራዊው አቶ ነዓምን መመሪያ ይሰጣሉ፤ “እሳቸው እንዳሉት እየተባለ ይደጋገማል። ኢትዮጵያን በህዝብ እንቢተኛነት ለማተራመስ ከሻዕቢያ የወረደውን መመሪያ ለመተግበር አስቻይ ሁኔታ እንደሌለም ይገለጻል። አብሮነት የጠራው ስብሰባ፤

“ታዋቂ ዲፕሎማት፣ የትም መግባት የሚችሉ መሪ” እየተባሉ የተሞካሹት አቶ ገዱ ፓርኪንግ ስራ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ስብሰባውን ሲካፈሉ “አቶ ነዓምን እንዳለው” ከማለት የዘለለ ምን አላሉም። ይህን የመስለው ስብሰባና ነው “አገር አንቀጥቅጥ” የተባለ ሰልፍ በሳይበር፣ በዲሲና በሎንዶን ለማድረግ የተነሳው። ከዛም አልፎ ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከ ዳር አመጽ ለማቀጣተል የተነሳው። ይህን ስንቅ ሰንቆ የተጀመረው የግብርኃይል ስብሰባ “የተባለውን ዓይነት ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታ የለም” ተባለ። የሻዕቢያ ወኪል ነዓምን ዘለቀ፤ በዋሽንግቶን ዲሲም ሆነ በሎንደን ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራ ማንም አይወጣም አሉ፤ ቅድሚያ በግል የሎቢ ስራ እንዲሰራ መመሪያ ሲሰጡ ተሰማ። ሎቢ!!

በዘር ግንዳቸው ኤርትራዊ የሆኑት አቶ ነዓምን ቅዳሜ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው የዙም ስብሰባ ላይ ከውይይቱ በፊት “አስተያየት ልስጥ” በማለት በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ ዋሽንግቶን ዲሲም ሆነ በሎንዶን ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራ የሚወጣ ሕዝብ እንደማይኖር ተናገሩ። አሁን ላይ ባለው መሰነጣጥቅና ወቅታዊ ሁኔታ፣ እንዲሁም የአማራ ኃይሎች እንኳን አንድ ስላልሆኑ ከሰልፉ በፊት ቅድሚያ የሎቢና የማሳመን ስራ ሊሰራ እንደሚገባ መመሪያ ሰጡ። በሚዲያዎች ሕዝብ እንዲነሳና አመጽ እንዲቀጣጠል ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑንም አመልከቱ። ሚዲያዎቹን ግን አልዘረዘሩም።

በኢትዮጵያ ህዝባዊ እምብተኛነትን ከጠብመንጃው ትግል ጋር ጎን ለጎን ለማካሄድ በተነደፈው ዕቅድ መሰረት “የሰላማዊ ትግል አቀንቃኝ” የሚባሉት አቶ ልደቱ በዋናነት ባደራጁት ይህንኑ የሚያመቻች ግብረኃይል ምስረታ፣ አስራ ሰባት ተሳታፊዎች እንደሚገኙበት አስቀድሞ ተገልጾ ነበር።

አዲስ ሪፖርተር እጅ የገባው ሙሉ የስብሰባው ቅጂ እንዳመለከተው የተገኙት ዘጠኝ ብቻ ናቸው። አቶ ገዱ “አሌክስ ጂ” በሚል ስም ዘግይተው በተገኙበትና ኢንጂነር ሙሉጌታ ባመቻቹት ስብሰባ ላይ ነው አቶ ነዓምን ቅድሚያ ተናጋሪ ሆነው መመሪያ የሰጡት።

በስብሰባው ላይ ይገኛሉ ተብለው ማረጋገጫ ከሰጡ በሁዋላ ያልተገኙት፣ አቶ ዩሱፍ ያሲን የኤርትራ አፋር ተወላጅ ከኖርዌይ፣ አቶ ያሬድ ኃይለማሪያም፣ አቶ አሻራ፣ ኢንጂነር ይልቃል፣ በአቶ ነዓምን በኩል የታጩት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ፣ መሆናቸው ከተገለጸ በሁዋላ የስብሰባው ተካፋይ የሆኑት ዶክተር ኢሳማኤል “አቶ ጃዋር ይገኛሉ ተብሎ ነበር ለምን ቀሩ” የሚል ጥያቄ አንስተዋል። አቶ ልደቱም “ይቅርታ ዘንግቼ ነው። ቨርጂኛ የፈጠርነው ፎረም አለ፣ ይህ ፎረም ጃዋርንና አቶ አባይን ወኮሏል። ውክልናውን ያውቃል ለምን እንዳልተገኘ አላሳወቀም። በሚቀጥለው ስብሰባ ይገኛል። የንቅናቄው አባል ነው። ስላስታወስከን ዶክተር አመስግናለሁ” አሉና ወደ ቀጣዩ ጉዳይ አመሩ። የአዲስ ሪፖርተር ተባባሪ ባለው መረጃ ጃዋር ብረት ካነሱ ስብስቦች ጋር በይፋ መቀላቀሉ በአዲስ ሪፖርተር ከተዘገበ በሁዋላ ከስብሰባው ለመቅረት ወስኗል። ይህን አስመልክቶ በኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረንስ ውስጥ ይፋ ከሆነው መሰነጣጠቅና የሽግግር መንግስት ምስረታ የእስር ቤት ምክክር ጋር በማያያዝ ሰፊ መረጃ እናቀርባለን።

በስብሰባው መገኘት አለባቸው የተባሉት ቁልፍ ሰዎች ስልክ እንዲደወልላቸውና እንዲቀላቀሉ እስኪደረግ ከአጀንዳ ውጪ የማሟሟቂያ ወሬ መሰል አስተያየት ተጀመረ። በዚሁ ውይይት የምስራቅ አፍሪቃ ጉዳይ ውስብስብ እየሆነ መምጣቱ ተነሳ። ይህን ጊዜ አቶ ነዓምን መካከል ገብተው “ለስማሌ ላንድ የተሰጠው ዕውቅና ነው ወይስ ሌላ ገፊ ምክክያት አለ” ሲሉ አሳቡን ላነሱት ጥያቄ አቀረቡ።

ዶክተር ኢሳማኤል ቀጠናውን በመተንተን የሚታወቁ ናቸውና “አይምስለኝም። የየመን፣ የኢራን፣ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የጅቡቲ፣ የሱዳን ጉዳይ አለ። ሰዎቹ ስትራቴጂካል ዕቅድ አላቸው” የሚል መስል ሰጡ። “ሰዎቹ” ሲሉ አሜሪካና እስራኤልን ማለታቸው ነው።

ከትግራይ የተለያዩ ተቋማት ጋር እንደሚሰሩ ያስታወቁት አቶ አባይ ግደይ ተመሳሳይ አሳብ ሰንዝረው በሱዳን ያሉ ሰባ ሺህ ተፈናቃዮች ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ አመለከቱ። አያይዘውም፣ የትግራይን ይረሃብ አደጋ አንስተው በሱዳን ያሉ ተፈናቃዮች በሁለት ሳምንት ያገኙ የነበረው 14 ኪሎ እህል ወደ 2.5 ኪሎ ዝቅ ማለቱን በመግለጽ የችግሩን አሳሳቢነት አነሱ። አክለውም ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ መሆኗን ገለጹ። እናም ተቃውሞ በማቀጣጣጠል ለውጥ ማምጣት ላይ መረባረብ እንደሚያስፈልግ አከሉ።

በዚህ መካከል አቶ ልደቱ ስብሰባውን መቀጠል እንደሚሻል አሳስበው በትውውቅ ተጀመረ። ከትውውቁ ጀምሮ ትርምስ፣ ጋባዥ ድርጅትና ውክልና የሰጠ አካል ላይ ስምምነት የሌለው የሚመስለው የግብረኃይሉ ውይይት ከነ ውጥንቅጡ ተጀመረ። የመጡት ዘጠኙ ራሳቸውን ገለጡ። ቪዲዮም ከፍተው እጅ አውለበለቡ። የአምስተርዳሟ ሲስተር ሐርግ “ይህን ከመሰለ ስብስብ ጋር በአቶ ልደቱ ጋባዥነት በመቀላቀሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ። አንድነት ብላችኋል እግዚአብሄር አይለያችሁ” ብለው ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች የወላይታ ነጻ አውጪ ግንባር መስራች መሆናቸውን ተናገሩ። “አንድ ስለሆናችሁ” ያሉት ሲስተር ሐረግ ያዕቆብ “ነጻ አውጪ ነኝ” ብለው ጨረሱ። የወከላቸው ድርጅት እንደሌለ ሲናገሩ፣ አቶ ልደቱ መሃል ገብተው “ከደቡብ ህዝቦች ተወክለዋል” ሲሉ “የለም የለም። ኋላ ላይ እነነጋገርበታለን” አሉና ታለፈ።

በትውውቁ ወቅት ከአቶ ልደቱ በስተቀር ስምንቱ ማንነታቸውን ሲገልጹ የመጡብትን ብሄር ይፋ አድርገዋል፣ አቶ ነዓምን ግን በኢትዮጵያ ስም የመሰረቱዋቸን ድርጅቶች ከማስታውቀ በቀር ስለ ትውልዳቸው ያሉት ነገር የለም። ግብረ ኃይሉን የተቀላቀሉት በግላቸው መሆኑን አመልክተው፣ የኢትዮጵያን አድን ስብስብ መስራች፣ ስምንት ስብስቦች ያሉበት የኢትዮጵያ የትብብር ንቅናቄ ምስራች መሆናቸውን ጠቅሰው አቶ ልደቱ ስለጋበዟቸው እንደመጡ ተናገሩ። ትብብር አገር ለማዳን ንቅናቄ / እሳቸው የሚመሩት ነው/ ይህ ግብረኃይል ድጋፍ ከመሰጠቱ በፊት እንዲመረመር መወሰኑን አስታወቁ።

ስብሰቡ ምርመራ የሚደርገበት ጉዳይ ምን እንደሆነ ለማጣራት የአዲስ ሪፖርተር የዲሲ ተባባሪ ዘጋቢ ያነጋገራቸው እንዳሉት አቶ ነዓምን ከኤርትራ መንግስት ጋር በገሃድ ስለሚሰሩ ስብስቡ ከሻዕቢያ የሚወርድለትን መመሪያ በአግባቡ እንደሚተገብር ሳይረጋገጥ እውቅና መስጠት ስለማይችሉ እንደሆነ አስረድተዋል። አክለውም ሻዕቢያ የሚነዳቸው ሚዲያዎችም ለዚህ ንቅናቄ ሙሉ ሽፋን የሚሰጡት አካሄዳቸው ከተገመገመ በሁዋላ እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ነዓምን ትውውቁ ካለቀ በሁዋላ የመጀመሪያ አቅጣጫ ሰጪ ሆነው ባቀረቡት አስተያየት ሕዝባዊ እንቢተኛነት እንዲቀጣጠል ከአቶ ልደቱ ጋር በጥንቃቄ ሲሰራበት እንደነበር አመልክተው፣ እንቅስቅሴው ትልቅ ውጤት ያመጣል ብለው እንደሚያምኑ አስረድተዋል።

በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት የኤርትራ አምባሳደር በግል የቲውተር ገጻቸው አድናቆትና የቅርብ ወዳጅነትን በሚያሳዩ ቃላቶች ተሞካሽተው ለአዲስ ዓመት እንኳን አደረስዎ የተባሉትና መልክም ምኞት የተቸራቸው አቶ ነዓምን፣ “ሕዝባዊ እንቢተኛነቱ ሲቀሰቀስ በደንብ የተደራጀና ፍኖተ ካርታ የተዘጋጀለት መሆን አለበት” ብለዋል። ግልጽ ባያደርጉትም ፍኖተ ካርታው እሳቸው በተለይም ከመሳይ ጋር በተደጋጋሚ ሲያስተዋውቁት የነበረው ተዘጋጅቶ የቀረበላቸው ዕቅድ እንደሆነ ከተሳታፊዎቹ መካከል ተናግረዋል።

ሕዝብ እንዲያምጽ በኦሮሚያ፣ ትግራይ፣ደቡብ፣ አዲስ አበባ ሕዝብ ብዙ መሰራቱን እንደሚያውቁና የተዘረጋ መዋቅር እንዳለ አድበስብሰው ካሳወቁ በሁዋላ ተመልሰው እልፍ ያለ ነገር እንደሌለ ሲገልጹ ይደመጣል። አቶ ነዓምን በዚህ መንደርደሪያ ጀምረው ግምገማቸው አኖሩ።

“አሁን ባለው መበታተን፣ ለመረዳት በሚያስቸግሩ ምክንያቶች፣ በወቅታዊ ሁኔታዎች ህዝቡ ለተቃውሞ አይወጣም” አሉ። አቶ ነዓምን፣ ዋሽንግቶን እና ሎንዶን ሰልፍ ቢጠራ ህዝቡ የማይወጣበትን ምክንያት ሲያነሱ አማራውን ነው ቅድሚያ የጠቀሱት።

“በአማራ አደረጃጀት እንኳን ሕዝቡ አብሮ ለተቃውሞ የማይወጣበት እውነታ ነው ያለው። ስለዚህ በየአድረጃጀቱ ሰዎች ተለይተው እንዲያምኑ ሎቢ መደረግ አለባቸው” የሚል አቅጣጫ አስቀመጡ። አክለውም “በጥቅሉ ዋሽንግቶንና ሎንዶን አስቻይ ሁኔታ የለም” ብለዋል። የማሳመኑ ስራና የሎቢው ተግባር ቅደም ተከተል እንደሚያስፈልገው አስታውቀው “ጓድ ልደቱ” በማለት ከስብሰባው መጀመርና አጀንዳ ይፋ ከመሆኑ በፊት የጥንስሱ መሪ መሆናቸውን የሚያሳይ መመሪያ አዘል አቅጣጫ አስቀምጠው ጨረሱ።

አቶ ልደቱ ጓዳዊ ምስጋና አቅርበው “ስራው የሚሰራው በጋራ ነው። የሚቋቋም ኮሚቴ አለ አቅጣጫ ያስቀምጣል” በማለት አቶ ነዓምንን “እዚህ የሚወሰን ነገር የለም” ሲሉ በተደጋጋሚ “እኔ የለሁበትም ስብሰባውን አመቻች ነኝ” የሚሉትን ኢንጂነር ሙሉጌታን ስብሰባውን እንዲያስቀጥሉ አመላከቱዋቸው። አቶ ልደቱ “መመሪያ አልቀበልም” የሚል እንደምታ ያለው ስልታዊ ምላሽ ለሰጡ በሁዋላ አቶ ነዓም “ቺርስ” አሉዋቸው።

በትውውቁ ወቅት ጠንከር ያለ መልዕክት ያስተላለፉት ዶክተር ኢስማኤል ጎርሴ ናቸው። ምንም እንኳን የሶማሌ ክልል ተወላጅ ቢሆኑም ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ “በዚህ በ21ኛ ክፍለ ዘመን፣ ከዚህ ብሄር ነው የመጣሁት በማለት መናገር አሳፋሪ ነው እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ” በማለት ሲናገሩ ተሰምቷል።

ከዚህ ሁሉ ወጣ ገባ የበዛው ውይይት በሁዋላ፣ መንግስትን የሚቃወም የጋራ የበይነ-መረብ ትይዕንተ-ህዝብ እና ሰላማዊ ሰልፎች ለማዘጋጀት የተቋቋመው ግብረ-ሀይል አባላት፤ ከአስራ ሰባቱ ዘጠኙ በመገኘታቸው፣ ውሳኔ ማሳለፉን የሚገልጽ ማስታወሻ ተበተነ።

የሚቀጥለው የግብረ ሀይሉ ስብሰባ 01/17/2026 በአሜሪካን ሰዓት አቆታተር 12:00 p.m እንዲካሄድ ወቀተሮ የተያዘ ሲሆን፣ በዕለቱ ህዝባዊ አመጽ የሚቀታተልበትን ስራ የሚሰራ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ (technical team) ይመረጣል።

ከስብሰባው ተሳታፊዎች፣ ካልተገኙትና ከሚቃወሙዋቸው ጋር ሲዳመር በኢትዮጵያ ስም የተቋቋሙት ድርጅቶች፣ ስብስቦች፣ የጋራ ግብረኃይሎች፣ ጥምረቶች፣ መድረኮች፣ ፎረሞች፣ በህቡዕ ከሚነቀሳቀሱት ውጪ ከሰላሳ በላይ ናቸው። አንዳንዶቹ የሁለትና የሶስት ስብስብ መሪ ናቸው። እነዚህ አላካት አንድ መሆን አቅቷቸው አራት አስርት ዓመታት ወይም ከያኔው ትውልድ ጀምሮ ውይይትና ሰላማዊ ንግግርን ረግጠው በትርምስና በደም ፖለቲካ የሚያምኑ እንደሆኑ በስፋት ይተቻሉ። አንዳንዶቹም በተፈጥሮ አርጅተው የማስታወስ ችሎታቸውን ያጡና በትክክል ኢትዮጵያ ውስጥ ምን እየተደረግ እንደሆነ የማያውቁ ወይም መረጃ የሌላቸው እንደሆኑ የሚቃወሟቸውና “ተውን”የሚሉት ወገኖች ይናገራሉ።

ፎቶ / አቶ ነዓምን ከኤርትራ የተባበሩት መንግስታት አምባሳደር ጋር በገና ዋዜማ የተነሱትና ሴትየዋ በግል የቲውተር ገጻቸው አድንቀውና መልካም ምኞት ተመንተው የለተፉት ምስል

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...