አዲስ ሪፖርተር ዜና — የትግራይ ሰላም ኃይሎች ወደ መቀለ መቃረባቸውን ያስታወቁት በስፋት የትግራይ ከተሞችን በመቆጣጠር ላይ መሆናቸውን በማስቀደም ነው። ለውጥ የሚሹ ኃይሎች ከአገር መከላከያ ጋር በመሆን፣ ወደ መቀለ መቃረባቸውን በማስታወቅ ባሰራጩት መግለጫ፣ ለፖሊስ እና ለሚሊሻ እንዲሁም በየሰፈሩ ታጥቀውና ተደራጅተው ላሉ አስቸኳይ ማሳሰቢያ፣ ጥሪና ማስጠንቀቂያ አስተላለፈዋል።
የትግራይ ሰላም ኃይሎች “ትግራይ ሓይሊ ሰላም፣ TIGRAI PEACE FORCE” መቀለ አፋንጫ ስር መድረሳቸውን አስመልክቶ ባስተላለፉት የቅድመ ዝግጅት አስቸኳይ ጥሪ፣ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያም የማይገዙትን ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው አስታውቀዋል።
የሻዕቢያ ኃይሎች ከጽንፈኛው የህወሃት ኃይል ጋር ሲያፈገፍጉ እንደለመዱት ዝርፊያና የጅምላ ጭፍጭፋ እንዳይፈጽሙ ጥብቅ ጥንቃቄ እንዲደረግ የሰላም ኃይሎች አሳስበዋል። በመግለጫቸው መግቢ ላይ ትግራይን ሰላም የማድረግ ኃላፊነትን አንግበው ለውጥ ለማምጣት መነሳታቸውን አመልክተው፣ ይህ ዓላማቸው ፍሬ እያፈራ መሆኑን አስታውቀዋል። ሙሉ መግለጫውን ከትግርኛ ወደ አማርኛ መልሰን አቅርበነዋል።
የትግራይ ሕዝብ ላለፉት ዓመታት ሲታገል ከነበረበት ውስጣዊ ጭቆና፣ ትንኮሳና ጥቃት ለመላቀቅ ዛሬ ለውጥ በሚሹ ጀግኖች አቅም ድል አስመዝግቧል። ይህ ዛሬ ያሰመዘገብነው ድል የሁላችንም አዲስ የለውጥ ፈላጊ ትግራዋያን፣ በተለይም ይህንኑ ታጋዮች፣ አባላትን፣ አመራሮችንና የትግራይ ሰላም ኃይሎች በብቃት፣ በቆራጥነትና በፅናት ያሳዩት የማይበገር ፖለቲካዊ ትግል፣ ዛሬ ላስመዘገብነው ድል ለምላው ሕዝባችን ማድረስ በመቻላችን ክብርና ምስጋና ይገባናል። ስለሆነም ትግላችን ፍሬ አፍርቶ ሠራዊታችን ወደ ትግራይ ከተሞች እየገባ በመሆኑ፣ አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ በዚህ ወቅት የትግራይ ሰላም ኃይሎች እና የሀገር መከላከያ በታላቅ ኃላፊነትና በቁርጠኝነት ሥራቸውን እየተወጡ ባለበት ብዚህ ወቅት የሚከተለውን ጥሪ ጥሪ እናቀርባለን።
ጥሪ ለፖሊስና ሚሊሻ አካላት፡
- በመላው ትግራይ የምትገኙ የፖሊስና ሚሊሻ ኃይሎች፣ በአካባቢያችሁ ተደራጅታችሁ ሙያዊ ኃላፊነታችሁንና ተግባራችሁን እየተወጣችሁ፤ የሕዝብ፣ የመንግሥት፣ የተቋማትና የፌዴራል አካላትን ሀብትና ንብረት ከስርቆትና ከጥፋት እንድትጠብቁ በጥብቅ እናሳስባለን።
- የሕዝቡን ፀጥታና ደህንነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ፣ ጥቃቶችና ዘረፋዎች እንዳይፈጸሙ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር የሰው ሕይወትና ንብረት ሳይጎዳ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በአስቸኳይ ኃላፊነታችሁን ልትወጡ ይገባል።
- በሕዝብ፣ በመንግሥት ተቋማት፣ በግል ንብረቶችና ተቋማት ላይ ጥፋትና ውድመት የሚያደርሱ አካላትን በመለየት፣ ጊዜያዊ ጥበቃዎችን በመፍጠርና ከሕዝቡ ጋር በመተባበር ከወንጀል እንድትከላከሉ እናሳስባለን።
- በዚህ ሂደት የፀጥታ ማስከበር ሙያዊ ኃላፊነታችሁን በገለልተኝነት ካለመወጣት፣ በመንግሥት ተቋማትም ሆነ በግል ንብረቶች፣ እንዲሁም በሕዝብ ላይ ለሚደርስ ችግር ተጠያቂ እንደምትሆኑ እንድታውቁት።
- ከዚያ ቀደም በቡድን የተደራጃችሁ፤ በአካባቢያችሁ የታጠቃቹህ ቡድኖች ያላችሁን መሣሪያ ይዛችሁ ባላችሁበት እንድትቆዩና የትግራይ ሰላም ኃይሎች ሙሉ በሙሉ ወደየ አካባቢያቹህ ሲደርስ መሣሪያችሁን ለሰላም ኃይሎች እንድታስረክቡ በጥብቅ እናሳስባለን።
- መላው ሕዝባችን የትግራይ ሕዝብ፣ በገጠርም ሆነ በከተሞች የምትኖሩ፣ አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ ተደራጅታችሁ የአካባቢያችሁን ሰላምና ደህንነት ከጥፋትና ከወንጀለኞች እንድትጠብቁ ይገባል።
ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮማንድ ትግራይ ሓይሊ ሰላም (TPF) 19 መስከረም 2019 ዓ/ም
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm






