Monday, December 1, 2025

መንግስት በተደጋጋሚ ጥቃት፣ እገታ፣ የንብረት ዘረፋና እና ውድመት በሚፈጽሙና የሰዎችን የመዘዋወር መብት በሚገድቡ ላይ በቂ የፀጥታ ኃይል እንዲያሰማራ ተጠየቀ

Date:

ኮሚሽኑ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡ የሰዎችን የመዘዋወር መብት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራትን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውንና እነዚህ ተግባራት ለመከላከል በአስቸኳይ እልባት ለመስጠት መንግስት በተደጋጋሚ ጥቃት፣ እገታ፣ የንብረት ዘረፋና እና ውድመት የሚፈፀምባቸው መንገዶች ላይ በቂ የፀጥታ ኃይል እንዲያሰማራ ባወጣው የሪፖርት ግኝት አስታውቋል ።

አዲስ ሪፖርተር – መንግስት የዜጎችን ጥቃት፣ እገታ፣ ዘረፋ፣ ወድመትና የመንገዶች መዘጋት እንዲከላከል ተጠየቀ፡፡ ኢሰማኮ ባወጣው ሪፖርት እንዳለው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡ እነዚህ ተግባራት የሰዎችን በነጻነት የመዘዋወር መብት አደጋ ላይ ጥለዋል።

ዜጎች የሚደርስባቸውን ጉዳት ዘርዝሮ ኮሚሽኑ መንግስትን ሲወቅስ ያነሳው ጉዳይ ቢኖር ትርጎጂዎች በደረሰባቸውና እየደረሰባቸው በደል ልክ አጥፊዎችን ለህግ ከማቅረብ አንጻር ክፍተት መኖሩን ነው። ይህ የኮሚሽኑ ግምገማ በርካታ ተጎጂዎች ከሚሰጡት የ”ተበደልን” አቤቱታ ጋር የሚገጥም ሆኗል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የጥናት ግኝቶችን ስፍራና በጥናት የለያቸውን ፈታኝ ችግሮች በመዘርዘር ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ይፋ አድርጓል። ተጎጂዎች የሕግ ምላሽ ሳያገኙ መቅረታቸውን ደግሞ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች መሆናቸውን ገልጿል።

መንግስት በተደጋጋሚ ጥቃት፣ እገታ፣ የንብረት ዘረፋና እና ውድመት የሚፈፀምባቸው መንገዶች ላይ በቂ የፀጥታ ኃይል እንዲያሰማራ ኢሰመኮ ባወጣው የሪፖርት ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የዜጎች በነፃነት የመንቀሳቀስ እና የመዘዋወር ነፃነት መብት አደጋ ላይ መውደቁ ያስታወቀው በአራት የተመረጡ ክልሎች ላይ ባደረገው ምርመራ ማረጋጡን በማስታወቅ ነው።

ወንጀሎች የተሳተፉ ግለሰቦችንና ቡድኖች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ክፍተት የተስተዋለበት በመሆኑን የገለፀው የኮሚሽኑ መግለጫ፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ተገቢና ተመጣጣኝ የሆኑ እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚገባ በሪፖርቱ አሳስቧል

ኮሚሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የዜጎች የመዘዋወር ነፃነት መብት አደጋ ላይ መውደቁ የገለፀውም በዚሁ መነሻ ነው። ኮሚሽኑ ሪፖርቱን ከማውጣቱ በፊት ዜጎች በተዘረዘሩት ቸግሮች ምክንያት የደረሰባቸውን ጉዳት ስቃይ በተለያዩ አግባቦቦች ከማስታወቅ ተቆጥበው አያውቁም።

ኮሚሽኑ አደረኩት ባለው የምርመራ ግኝት መሰረት በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በጋምቤላ ክልሎች በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች የሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት መብት በተለያዩ ደረጃዎች መታቀቡን ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ነው ያስታወቀው።

የኮሚሽኑ በመግለጫው እንዳስታወቀው ከሆነም በተጠቀሱት አራት ክልሎች በየጊዜው በሚጣሉ ኬላዎችን ጨምሮ የመንገድ መዘጋት እርምጃዎች፣ የሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲኹም በመንገዶች ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ሳቢያ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች “አሳሳቢ” በሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን በሪፖርቱ ላይ አመላክቷል። ይሁን እንጂ በዝርዝር ስም ጠቅሶ ሕዝብን ለስቃይ የዳረጉትን ክፍሎች አላጋለጠም።

በኮሚሽኑ ሪፖርት መሰረት በአራት ክልሎች በተደረገው ክትትል እና ምርመራ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አስከፊ በሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን ማረጋገጥ እንደተቻለ ጠቅሶ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ የዓይን ምስክሮችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን እና ጉዳዮ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትን በማነጋገር እንዲሁም መረጃዎችን ማጠናከር እንደተቻለ ተገልጿል።

የኮሚሽኑ መግለጫው፣ የሰብአዊ መብቶች ክትትል እና ምርመራ ግኝት የተደረገባቸው አከባቢዎች በግጭት ዐውድ ውስጥ እና ከግጭት ዐውድ ውጪ የሚገኙ ሁኔታዎችን ማካተቱን የገለፀ ሲኾን ምርመራው የተከናወነው ከሚያዝያ 2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 2018 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ መሆኑን አስታውቋል ።

በአራት ክልሎች በተደረገው ክትትል እና ምርመራ በየአካባቢዎቹ የሚገኙ ነዋሪዎችን በግንባር ቀርቦ ማነጋገር እንደተቻለ እና ሪፖርቱን ለማጠናከርም የሚመለከታቸው የፀጥታ ሐይሎች እንዲኹም የተጎጂ ቤተሰቦችን በማነጋገር መረጃ እና ማስረጃዎች ማሰባሰብ መቻሉን በኮሚሽኑ ያወጣው መግለጫ ያስረዳል ።

በዚህ መሰረት ኮሚሽኑ የመዘዋወር መብት አፈፃፀምን የሚሸረሽሩ ናቸው ያላቸውን ጥሰቶች የዘረዘረ ሲኾን በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በተደጋጋሚ በሚጣሉ የሰዓት እላፊ የእንቅስቃሴ ገደቦችን ጨምሮ በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች እና በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች በመንገዶች ላይ በሚጣሉ ኬላዎች የመንገድ መዝጋት ትዕዛዞች አሳሳቢ ሲል ካስቀመጣቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል ይገኙበታል።

መግለጫው አክሎም፣ በተጠቀሱት አራት ክልሎች በመንገዶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እንዲኹም ውድመቶችም የተፈፀሙ መኾናቸውን እነዚህ ተግባራት ዜጎች በነፃነት የመዘዋወር መብት ላይ አደጋ መፍጠራቸውን ተናግሯል።

ስለዚህም እነኚህ መብት የሚጥሱ እንቅቃሴዎች በኢትዮጵያ ሕገመንግሥት እና ኢትዮጵያ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተቀበለቻቸውን የሰብዓዊ መርሆች የሚጥሱ ከመሆናቸው ባሻገር ዜጎች በሕግ አስፈፃሚው አካል ያላቸውን እምነት የሚሸረሽሩ ተግባራት ናቸው ብሏል። በተለይም ተጎጂዎች የሕግ ምላሽ ሳያገኙ መቅረታቸውን ደግሞ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመላካች መሆናቸውን ገልጿል ። ኮሚሽኑ የህግ ምላሽ አላገኙም ያላቸውን ጉዳዮች አልዘረዘረም። ይሁን እንጂ መንግስት ወንጀለኞቹን ለህግ ማቅረብ እንዳለበት አመልክቷል።

መንግስት በእነዚህ ወንጀሎች የተሳተፉ ግለሰቦችንና ቡድኖች በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ ክፍተት የተስተዋለበት በመሆኑን የገለፀው የኮሚሽኑ መግለጫ፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ተገቢና ተመጣጣኝ የሆኑ እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚገባ በሪፖርቱ አሳስቧል።

የሚመለከተው የመንግስት አካል ማናቸውም ህግና ስርዓትን የማስከበር፣ ወንጀል የመከላከል እና አጥፊዎችን ተጠያቂ የማድረግ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ህግና ስርዓትን በተከተለ መልኩ እንዲያስፈፀሙና የሚወሰዱት እርምጃዎችም ሰብአዊ መብቶችን ባከበረ መልኩ እንዲፈፀሙ ጠይቋል።

መንግስት በብርቱ ሊሰራባቸው ይገባል ካላቸው ጉዳዮች መካከል በመንገዶች ላይ በታጠቁ ኃይሎች ለሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንዳለበትና በዜጎች ላይ ያንዣበበው የመንቀሳቀስ ነፃነት አደጋ እንዲከላከል

በተለይም መንግስት በብርቱ ሊሰራባቸው ይገባል ካላቸው ጉዳዮች መካከል በመንገዶች ላይ በታጠቁ ኃይሎች ለሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች ተገቢውን ትኩረት መስጠት እንዳለበትና በዜጎች ላይ ያንዣበበው የመንቀሳቀስ ነፃነት አደጋ እንዲከላከል ምክረ ሐሳብ መስጠቱን ከኮሚሽኑ መግለጫ ተመልክተናል።

በእነዚህ ድርጊቶች ተጎጂ በሆኑ ሰዎች ላይ በቀጥታ ከሚደርሱት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ባሻገር በተጎጂ ቤተሰቦች ላይ የሚደርሰውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት እና የስነ ልቦና ጫና እንዲከላከል መንግስትን የጠየቀ ሲኾን በተለይም ዜጎች በሕግ ያላቸው አመኔታ እንዳይሻር የመጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ በአፅንኦት ተማፅኗል ።

ኮሚሽኑ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የመጡ የሰዎችን የመዘዋወር መብት አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራትን አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውንና እነዚህ ተግባራት ለመከላከል በአስቸኳይ እልባት ለመስጠት መንግስት በተደጋጋሚ ጥቃት፣ እገታ፣ የንብረት ዘረፋና እና ውድመት የሚፈፀምባቸው መንገዶች ላይ በቂ የፀጥታ ኃይል እንዲያሰማራ ባወጣው የሪፖርት ግኝት አስታውቋል ።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related