ምርጫ ቦርድ በሚያስገድዱ ላይ የእግድ ዕርምጃ እወስዳለሁ አለ፤ ምዝገባ ሊጠናቅቅ ነው

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት፣ የመራጮች ምዝገባ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ይቆያል። የምዝገባው ሂደት ሊጠናቀቅ 3 ቀናት ብቻ ስለቀሩት፣ እስካሁን የምርጫ ካርድ ያልወሰዳችሁ ዜጎች ቀሪዎቹን ቀናት እንዲጠቀሙ አሳቧል።

“ምርጫ ካርድ አለመውሰድ የራስዎን እና የቤተሰብዎን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሌላ አካል እንዲወስን በራስዎ ፈቃድ ዕድሉን አሳልፎ መስጠት ነው።በሀገርዎ የዴሞክራሲ ልምምድ ውስጥ ለመወሰን እና የዜግነት ግዴታዎን ለመወጣት የድምፅ መስጫ ካርድዎን ይያዙ” ሲል ቦርዱ ጥሪውን አስተላልፏል።

ድምፅ መስጠት መብትዎ= ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲ ተሳትፎዎ መገለጫ መሆኑን ያሳሰበው ቦርዱ፣ በአቅራቢያ በሚገኝ የምርጫ ጣቢያ በአካል በመገኘት ወይም በምርጫዬ መተግበሪያ በዲጂታል አማራጭ መመዝገብ እንደሚቻልም አመልክቷል።

በተመሳሳይ ዜና ምርጫ ቦርድ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ የሚፈጸሙ “ሕገ-ወጥ ማስገደዶች” ካልቆሙ ምርጫን እስከማሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ እየተስተዋሉ ያሉ የሕግ ጥሰቶችን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤ ዜጎች ካርድ እንዲወስዱ የሚደረግ ማንኛውም አይነት የግዴታ ተጽዕኖ በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስቧል።

ቦርዱ እንደሚለው፣ ቤት ለቤት በመዘዋወር “ካርድ ውሰዱ” ከሚል ሕግን ከሚተላለፍ ተግባር ጀምሮ፣ መመዝገብን ከማኅበራዊ አገልግሎቶች ማግኘት እና ከደሞዝ መቁረጥ ጋር በማያያዝ በዜጎች ላይ ያልተገባ ተጽዕኖ እየተፈጸመ መሆኑን የሚጠቁሙ ሪፖርቶች ደርሰውታል።

ምርጫ ቦርድ በመግለጫው ባስተላለፈው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ፦ “ይህ የዕርምት ዕርምጃ ካልተወሰደ፣ ያልተገባ ቅስቀሳ የሚደረግባቸውን የምርጫ ክልሎች እና ምርጫ ጣቢያዎችን በመለየት ምርጫ እንዳይካሄድ የሚያደርግ ዕርምጃ ለመውሰድ እገደዳለሁ” ብሏል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱን አባረር፤ በግምገማ “የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ሚዲያዎች ሸሽተውናል” ተባለ

በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ይካሄዳል የተባለው 'ምድር አንቀጥቅጥ' ሰላማዊ...

የሱኒ ሃገራት ዓለም ፤ በስሜትና በተጨባጭ እውነታ መካከል ያለው ልዩነት፤ የአህመዲን ጀበል የግሉ ጂኦ-ፖለቲካ

በዘመናዊው ጂኦ-ፖለቲካ ውስጥ ትክክለኛው ሃይል የሚለካው በቴክኖሎጂ ልዕልና፣ በኢኮኖሚ...