“የምንገነባው ሕጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት የሚወሰነው በቅድመ ምርጫ ተሳትፏችን” ዐቢይ አሕመድ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ጠቅላይ ሚኒስትሩ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓልን አስመልክቶ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ በመጪው ግንቦት የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያ ወደ ቀጣይ ብሩህ ዘመኗ የምትሸጋገርበት መሆኑን ገልጸዋል።

ምርጫው ሀገራችን የዴሞክራሲ ድል የምትቀዳጅበት፤ ወደ ቀጣይ ብሩህ ዘመኗ የምትሸጋገርበት በር ነው በማለት ገልጸዋል።

እንደ ሀገር ለዓመታት ዴሞክራሲን ስንናፍቅ ኖረናል፤ ጉዟችን አልጋ በአልጋ አልነበረም ብለዋል።

ከፈተና በኋላ በረከት፣ ከብርታት በኋላ ሐሴት እንዳለ ከረመዳን ጾምና ከዒድ አል ፈጥር በዓል እንማራለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊ ጉዳዮች ውስጥ ዘርና ምርት የተቆራኙ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

የምንገነባው ሕጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት የሚወሰነው በቅድመ ምርጫ ተሳትፏችን ልክ ነው በማለት ገልጸው፤ ተሳትፏችን ከጠየመ ዴሞክራሲያችንም ይጠይማል ነው ያሉት።

በደካማ ተሳትፎ ጠንካራ ዴሞክራሲ ማዋለድ እንደማይቻል ገልጸው፤ ዜጎች በምርጫው ጠንካራ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በባዶ መሬት እንደማይበቅል እና በግጭትና ሥርዓት አልበኝነት እንደማይገነባ ጠቅሰው፤ ስክነትን፣ ለትብብርና ቅንጅት ልብን ክፍት ማድረግን፣ በጨዋታው ሕግ መመራትን ይጠይቃል ብለዋል በመልዕክታቸው።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

አሜሪካና ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ምን እያሰቡ ነው? “አሜሪካ የኢትዮጵያን የባህር ፍላጎት ማሳካት ህልውናዋ ነው”

ኢትዮጵያ የቀጥታ የባህር ዳርቻ ባይኖራትም፣ በወታደራዊ አቅሟ እና የባህር...

“የአሜሪካና ኢትዮጵያ ወዳጅነት አደገኛ ነው፤ ከማን ጋር እንደምንዋጋ አልገባንም፤አሳልፋ ልትሰጠን ትችላለች”

አዲስ ሪፖርተር - በአገር ቤት ሕዝባዊ አመጽ ለማነሳሳት የተደራጀው...

ኤርትራ ለህወሃት መሪዎች የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት የመስጠት ስምምነት አገደች

አዲስ ሪፖርተር - የኤርትራ መንግስት ለህወሃት አመራሮችና ከፈተኛ ወታደራዊ...

አሜሪካ እና ከኢትዮጵያ ጋር “ቋሚ ማዕቀፍ” የተባለ ስምምነት ተፈራረሙ፤

ዲስ ሪፖርተር - የአሜርካና የኢትዮጵያ አዲሱ ስምምነት "ቋሚ ማዕቀፍ"...