ብልጽግናን በአዲስ አበባ ከ60 በመቶ በላይ ነባር ወኪሎቹን አራግፎ በአዲስ ተካ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – በ2013 ዓ.ም. በተደረገው አጠቃላይ ምርጫ ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው በአዲስ አበባ ከተመረጡት የፓርላማ እና የከተማ ምክር ቤት ተመራጮች ውስጥ 62 በመቶው በአዲስ ተተኩ። በመጪው ምርጫ በአዲስ አበባ ዕጩ ሆነው ካልቀረቡት ተመራጮች መካከል ምክትል ከንቲባው ጃንጥራር አባይ ይገኙበታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስን ጨምሮ በርካታ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ደግሞ በተወካዮች ምክር ቤት አዲስ አበባን እንዲወክሉ እንዲወዳደሩ በዕጩነት ቀርበዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ግንቦት ላይ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ ለአዲስ አበባ ከተማ ካቀረባቸው 154 ዕጩዎች ውስጥ 96 ያህሉ በባለፈው ምርጫ በመዲናዋ ያልተወዳደሩ እንደሆኑ ቢቢሲ የምርጫውን ሰነድ አመሳከሮ ይፋ አድርጓል።

በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ከተመረጡ 160 ግለሰቦች ውስጥ በዚህኛውም ምርጫ ዕጩ ሆነው የቀረቡት 58 ያህሉ ብቻ ናቸው።

የዕጩዎች ዝርዝር እንደሚያመለክተው ገዢው ፓርቲ በአዲስ አበባ ከተማ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲወዳደሩ ያቀረባቸው ዕጩዎች 20 ናቸው። ከዚህ ውስጥ በድጋሚ ለዚህ ስፍራ ዕጩ የሆኑት አራቱ ብቻ ናቸው።

ፓርቲው ባለፈው ምርጫ ለፓርላማ ዕጩ ያላቀረበው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር የሆኑት ዳንኤል ክብረት በግል በተወዳደሩበት “ምርጫ ክልል 28” ነበር።

በዘንድሮው የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ ዳንኤል ክብረት አልተካተቱም። ብልጽግና ፓርቲም የፌደራል የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን ዶ/ር ሌሊሴ ነሜን በምርጫ ክልሉ ዕጩ አድርጎ አቅርቧል።

ፓርቲው ዕጩ ካላስመዘገበባቸው ሦስት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምርጫ ክልሎች ውስጥ በሁለቱ የሚወዳደሩት የተቃዋሚው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) አመራሮች ናቸው።

በየካቲት መጨረሻ በተካሄደው የኢዜማ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲው መሪ ሆነው የተመረጡት ኢዮብ መሣፍንት ብልጽግና ዕጩ ባላቀረበበት “ምርጫ ክልል 18″ ይወዳደራሉ። በዚሁ ጉባኤ ምክትል መሪ የሆኑት ንጋቱ ወልዴ ደግሞ በ”ምርጫ ክልል 23” የተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።

ብልጽግና ፓርቲ ዕጩ ባላስመዘገበበት ሌላኛው “ምርጫ ክልል 11” ከሚወዳደሩ ፖለቲከኞች መካከል ደግሞ በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) ወክለው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት የተመረጡት አበባው ደሳለው ይገኙበታል።

በባለፈው ምርጫ በአማራ ክልል የወከሉትን ፓርቲ የለቀቁት አበባው፤ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲን (ኢሕአፓ) ተቀላቅለዋል። አሁን ዕጩ ሆነው የቀረቡትም ኢሕአፓ የሚገኝበትን “ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት” የተሰኘ ቅንጅትን በመወከል ነው።

ፎቶ ቢቢሲ

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱን አባረር፤ በግምገማ “የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ሚዲያዎች ሸሽተውናል” ተባለ

በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ይካሄዳል የተባለው 'ምድር አንቀጥቅጥ' ሰላማዊ...

የሱኒ ሃገራት ዓለም ፤ በስሜትና በተጨባጭ እውነታ መካከል ያለው ልዩነት፤ የአህመዲን ጀበል የግሉ ጂኦ-ፖለቲካ

በዘመናዊው ጂኦ-ፖለቲካ ውስጥ ትክክለኛው ሃይል የሚለካው በቴክኖሎጂ ልዕልና፣ በኢኮኖሚ...