አዲስ ሪፖርተር – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከባንኮች ከፍተኛ ባለአክስዮኖችን ከመቆጣጠር አንስቶ እሰከ ማገድ የሚያስችል ሰልጣን የሚሰጠው ረቂቅ መመርያ መሰናዳቱን የተገለፀ ሲኾን ረቂቅ መመርያው ከባንኮች ከፍተኛ ድርሻ የሚገዙ አካላትን ለመከታተል እንዲያስችለው የሚረዳ መኾኑን ተገልጿል።
ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጀው ረቂቅ መመርያ በዋነኝነት ከባንኮች ከፍተኛ ድርሻ የሚገዙ አካላትና ግለሰቦች የገንዘባቸውን ምንጭ እንዲያሳውቁ የሚያስገድድ ስልጣን የሚሰጥ መኾኑንና የተገለፀ ሲኾን አጠቃላይ የፋይናንስ ዘርፉን ጤና ለመጠበቅ ያለመ ነው ተብሏል።
ባንኩ መመሪያውን ለማውጣት የተገደደበት ምክንያት ሲገልፅም በባንኮች ውስጥ የሚኖሩ የአክሲዮን ዝውውሮች ግልፅና ድርሻቸውን በዓለማቀፍ ደረጃ ያለውን የድርሻ መስፈርቶችን ባሟላ መልኩ መካሄዱን ለማረጋገጥና የባንክ ስራ የመጠበቅ ኃላፊነቱ እንዲወጣ የሚረዳው መኾኑን ገልጿል
በቀጣይም ረቂቅ መመሪያውን ለባለድርሻ አካላት እንዲወያዩበት ባንኩ ግብዣ እንደሚያደርግና አስተያየቶችን መስማት እንደሚፈልግ የተገለፀ ቢሆንም በተዘጋጀው በረቂቅ መምርያ ሐሳባቸውን እንዲሰጡ በሚጋበዙት አካላት ዙርያ ባንኩ ያለው ነገር የለም።
በመጀመሪያ ዙር ረቂቅ መመርያው ላይ የሚሰጡ ጠቃሚ አስተያየቶችን ተቀብሎ ለመመርያው ግብአትነት ለማዋል ዝግጁ መኾኑንና ረቂቅ መመርያው በቅርቡ በምክር ቤት የፀደቀው የባንክ ስራ አዋጅን አቅም የሚሰጡ ነጥቦች የተካተቱበት መኾኑንም ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል ።




