በአርሲ ንጹሃንን የገደሉት የኦነግ/ሸኔና የፋኖ ታጣቂዎች መሆናችው ፍንጭ ተሰጠ፤ የገዳዮቹን ማንነት “አናውቅም” ያሉም አሉ

Date:

ግድያው ሃይማኖትን ወይም አንድ ብሄርን ዒላማ ያደረገ እንዳልሆነ አጣሪ ቡድኑ አስታወቀ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአርሲ የተለያዩ ወረዳዎች የተፈጸወን ግድያ፣ ዘረፋና እገታ ለማጣራት ወደ ስፍራው ያሰማራው የልዑካን ቡድን አባላት ግድያውን የፈጸሙት ኦነግ /ሸኔና የፋኖ ታጣቂዎች መሆናቸውን ከመስክር መስማታቸውን በመጀመሪያው ደረጃ ሪፖርታቸው አስታወቁ። አንዳንዶቹ ማንነታቸውን መናገር አይችሉም። ህጻናት ታግተው ገንዘብ መጠየቂያ መደረጋቸውን፣ ወላጆች ገንዘብ መስጠት ስላልቻሉ ህጻናቱ መገደላቸውን ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል።

የአጣሪ ቡድን ሰብሳቢ መላከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ጥቅምት 12 እን 13 የሆነውን ከዘረዘሩ በሁዋላ፣ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ታጣቂዎቹ ያገቷቸውን ሰዎች እንደገደሏቸው ከምስክሮቹ የሰሙትን ተናግረዋል። ከተጎጂ ቤተሰቦች እና ካነጋገርናቸው ሰዎች በተሰጠ ምላሽ ይህንን ድርጊት የፈጸሙት ራሳቸውን “የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ሸኔ፣ ወይም ፋኖ ” ብለው የሚጠሩት ታጣቂዎች መሆናቸውን አመልክተዋል። አንዳንድ ግለሰቦች ደግሞ በሰጡት ምላሽ የታጣቂዎቹን ማንነታቸውን እንደማያውቁ ነገር ግን በለሊት የሚንቀሳቀሱ ምንም ዓይነት የሃይማኖት መገለጫ የሌላቸው ግለሰቦች መሆናቸውን እንደሆኑ መስክረዋል። ሙስሊሞችም መገደላቸው ተመልክቷል።

በመጀመሪያው ሪፖርት ስለ ገዳዮቹ ማንነት በትክክል አለመገለጽ በአዲስ ሪፖርተር ከቀናት በፊት የዓለም የግራጫ (Gray Zone Warfare) በሚል ርዕስ ጉዳዩን ሰፋ አድርጎ ማየት እንደሚያስፈልኛ የገዳዮቹ ማንነት የሚደበቀው በምክንያት እንደሆነ ከተጠቆመው ጋር ሊቀራረብ የሚችል መስሏል።

ወደ አካባቢው በማቅናት ከስር በተጠቀሱት አካባቢዎች ማጣራት ያከናወኑት አስር የልዑካን አባላት የተውጣጡት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሦስት፣ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከኦሮሚያ እስልምና ከፍተኛ ምክር ቤት ሁለት፣ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሁለት ናቸውው። ልዑክ ቡድኑ ዋና ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እንዲሁም ጸሃፊ መድቦ ነው የተነቀሳቀሰው።

አጣሪ ቡድኑ በቅድመ ወይም በመጀመሪያ ሪፖርቱ፣ ” ግድያው አንድን ሃይማኖት እና ብሄርን ትኩረት ያደረገ አይደለም ” ሲል እማኞቹን ጠቅሶ አመልክቷል። ይህም ግድያ በተፈጸም፣ እገታ በተሰማ ቁጥር ከሐሃይኖት ጋር በማያያዝ ሲቀርብ የነበረውን መረጃ ውድቅ የሚያደርግ ሆኗል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በሚገኙ አንዳንድ ወረዳዎች በሚኖሩ ዜጎች ላይ የተፈጸሙ ግድያ ፣እገታ እና ዝርፊያ በሚመለከት ልዑካኑን በአካባቢው በመላክ በጉዳዩ ላይ ሲያደርግ የቆየውን ጥናት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት በዛሬው ዕለት ይፋ ሲያደርግ ፍንጭ በመስጠት ምርመራውን እስኪያጠናቅቅ ያቆያቸው ጉዳዮች አሉ።

በቀረበው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ውጤት መሰረትም ገባኤው ጥቃቱ አንድን ሃይማኖት እና ብሄርን ትኩረት ያደረገ ግድያ ተፈጽሟል በማለት ሲዘዋወር የነበረውን መረጃ መሰረት የሌለው መሆኑ አመልክቶ ሙስሊሞችም መገደላቸውን ይፋ አድርጓል።

አጣሪ ቡድኑ ሪፖርቱን የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ያቀረበበት ምክንያት ሪፖርቱ ያላለቀ በመሆኑ ፣የተጠቀሱት ወረዳዎች የተራራቁ በመሆናቸው እንዲሁም መሰረተ ልማት ውስንነት ያለበት ከመሆኑ አንጻር ሁሉም ቦታ ላይ ደርሶ የመጨረሻ ሪፖርት ለማውጣት ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ ነው።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ከጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ አርሲ ዞን በተለይም በአምስት ወረዳዎች ተፈጠሩ የተባሉትን ሲዘረዝሩ “የሰው ህይወት ጠፍቷል፣ አካል ጎድሏል ፣የተፈናቀሉ እና የጠፉ አሉ፣ ንብረት ወድሟል” ብለዋል። ይህም የተሰማው በአካባቢው ከሚኖሩ፣ ታግተው ከተለቀቁ፣ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ወዘተ ነው።

ቀሲስ ታጋይ ” ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ምልከታ እና የማጣራት ሪፖርት ነው፣ ቀጣይ ተጨማሪ ማጣራት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ካሉ ቦታው ድረስ እየሄዱ የማጣራት ስራ ጊዜ የሚፈልግ ነው ። በሦስት እና በአራት ቀናት ብቻ የሚያልቅ አይደለም። ወራትም ሊወስድ ይችላል” ሲሉ ማጣራቱ ቀላል እንደማይሆን ገልጸዋል።

የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሰቢ መላከ ሰላም ዳዊት ያሬድ የመጀመሪያ ደረጃ የጥናት ሪፖርቱን ውጤት በሚመለከት ዝርዝር ሃሳቡ በዋናው ማጠቃለያ ሪፖርት ላይ የሚገልጽ ሆኖ ጥናቱ የተደረገው ጉና፣ ሽርካ ፣ሆንኩሎ አቤ፣ መርቲ ወረዳዎች መሆኑን አስታውቀዋል። ሲያብራሩም አንደኛ በጉና ወረዳ ናኖ ጃዊ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የሰው ህይወት መጥፋት፣ የንብረት መውደም ፣ዝርፊያ እንዲሁም እገታ መፈጸሙን ገልጸዋል።

የክስተቱ ሁኔታ 12/02/18 ዓም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ታጣቂዎች አስገድደው ከማህበረሰቡ ጋር ምሳ በሉ። በመጨረሻም የመንግስት ታጣቂ ሃይል መምጣቱን ሲያውቁ የተወሰኑ ሰዎችን አግተው እና ንብረት ይዘው ወደ ጫካ ሸሹ። በበነጋታው ማለትም ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓም ምሽት ተመልሰው ተጨማሪ ሰው አግተው ወስደዋል።

ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓም ያገቷቸውን ሰዎች ገደሏቸው። ከተጎጂ ቤተሰቦች እና ካነጋገርናቸው ሰዎች በተሰጠ ምላሽ ይህንን ድርጊት የፈጸሙት ራሳቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ሸኔ፣ ወይም ፋኖ ናቸው የሚል ምላሽ ነው

አንዳንድ ግለሰቦች ደግሞ በሰጡት ምላሽ ማንነታቸውን እንደማያውቁ ነገር ግን በለሊት የሚንቀሳቀሱ ምንም አይነት የሃይማኖት መገለጫ የሌላቸው ግለሰቦች መሆናቸውን ነው።

“በሸርካ ወረዳ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓም የሰው ህይወት ጠፍቷል እገታም ተፈጽሟል በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ ዜጎች ላይ በተለያየ ጊዜ ዘር ፣እምነት እንዲሁም እድሜ እና ጾታ ሳይለዩ ግድያዎች ተፈጽመዋል” ብለዋል። ህጻናት ታግተው ገንዘብ መጠየቂያ ተደርገዋል፣ ወላጆች ገንዘብ መስጠት ስላልቻሉ ህጻናቱ ተገድለዋል።  አንዳንድ ቦታዎች ላይ ህጻናቱ ተለቀው ወላጆች ከነገንዘባቸው ተወስደው ተሰቃይተዋል። የተቀሩት ወረዳዎችም ተመሳሳይ ድርጊቶች መከናወናቸው ምላሽ ተሰጥቶናል።

ከመንግስት በኩል የተገኘው ምላሽ ወታደራዊ እርምጃ መወሰዱን እና ከመንግስት የታች መዋቅር ጭምር መስዋዕትነት እየተከፈለ መሆኑን ነው።

በችግሩ ተጋላጮች ወይም ሰላባ የሆኑ ቤተሰቦች ወይም የቅርብ ምስክሮች ክስተቱ አንድ ወገንን ወይም ብሔር እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ አለመሆኑን እና ሁሉንም የጎዳ እንደሆነ በአታሪ ቡድኑ ሪፖርት ለምስክሮች እንደተገለጸ ሰብሳቢው አመልክተዋል።

አጥኚ ቡድኑ በአራት ወረዳዎች በመንቀሳቀስ እና እውነታውን ለባለድርሻ አካላት ለማቅረብ ስራውን የጀመረ ሲሆን በአራት ወረዳዎች ባስቀመጠው የጥናት እቅድ መሰረት ተግባራዊ ስራውን ያከናወነ በመሆኑ ጥቅል ዝርዝር ሁኔታዎች ማለትም የሟች ማንነት ፣የአሟሟት ሁኔታ፣ ብዛት ፣የሃይማኖት ስብጥር በቀጣይ በጥናት የሚካተቱ እና የቀሩትን ወረዳዎች ባማከለ መልኩ የሚያቀርብ ይሆናል ” ብለዋል።

ምክትል ሰብሳቢ ሃጂ አብድልሃኪም ሁሴን በሰጡት ቃል አንድ ወገን ላይ ያተኮረ ግድያ ተፈጽሟል መባሉ ስህተት መሆኑን ገልጸው ” አጥቂዎቹ አንድን ሃይማኖት እንደማይለዩ ፣እንዲሁም ታጣቂዎቹ የሁሉም ሃይማኖት ስብጥር እንደሆኑ በአንዳንድ ወቅት በአጋቾቱ ታግተው ከተለቀቁ ሰዎች በተገኘ መረጃ ተገልጾልናል ” ብለዋል።

ሪፖርቱ ወደፊት በስፋትና በዝርዝር የሚያቀርባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው፣ የዜጎች ግድያና እገታ በአንድ ኃይማኖትና ብሄር ላይ እንደሚፈጸም አድርገው የሚገልጹና ሲገልጹ የነበሩ የኢትዮጵያ ኃይማኖቶች ጉባኤ ከተለያዩ አካላት የተውጣጣ አጣሪ ኮሚቴ ወደ ስፍራው መላኩን ተቃውመው እንደ ነበር የሚታወስ ነው።

አዲስ ሪፖርተር የተለያዩ አካላትን በማነጋገር ጉዳዩን አስመልክቶ ሲዘግብ፣ ስማቸውን ያልጠቀሱ ከፍተኛ የኃይማኖት መሪ “ ገዳዮቹን ለማጋለጥ ትንሽ ፍንጭ ሲታይ ተቃውሞ ይነሳል። ይህ አስገራሚ ነው” በማለት አስተያየት ሰጥተው ነበር።

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

የፕሮፌሰሩ እይታ “ጠንቋይ የሰዉን እንጂ የራሱን አያዉቅም” አብይ አሕመድ ነጥብ አስጥለዋል

ሀገር የምትገነባው መንግስት ያድርግ በሚሉ ጥያቄዎች ሳይሆን እኔ ይሄን...