የደም አይነት እና የአመጋገብ ስርአት

Date:

አዲስ ሪፖርተር – የሰው ልጅ ደም በቀይ የደም ሕዋሳት ላይ ያሉትን ንጥረ ነገሮች መሠረት በማድረግ ኤ (A) ፣ ቢ (B) ፣ ኤቢ (AB) እና ኦ (O) ተብሎ በአራት ይከፈላል፡፡ የተመገብነው ምግብ በአንጀታች ውስጥ ከተፈጨ በኋላ በደማችን አማካኝነት ወደተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ይሠራጫል፡፡ በዚህም ሂደት ውስጥ ምግባችን ውስጥ ያሉ የተለያዩ ንጥረ ነገሮች ከደማችን ጋር ኬሚካላዊ ግንኙነትና ውሕድ ይፈጥራሉ፡፡ ይህንንም ተከትሎ ከደማችን ዓይነት ጋር የሚስማማ ምግብ ከተመገብን የምግብ የመላም ሂደት ሊፋጠን፣ አላስፈላጊ ክብደት ልንቀንስ፣ የላቀ ጉልበት ሊኖረን እንዲሁም የበሽታ የመከላከል ዓቅማችንም ሊዳብር ይችላል፡፡ከዚህ በመቀጠልም ከእያንዳንዱ የደም ዓይነቶች ጋር የሚጣጣሙ የምግብ ዓይነቶችን እንጠቅሳለን፡፡

1) የ ኦ (O)ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት

ይህ የደም ዓይነት ከሌሎች ቀድሞ የነበረ ጥንታዊ ሲሆን ከእንስሳት አዳኞች የተወረሰ የደም ዓይነት ነው፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ዓሣ፣ የባህር ምግብ፣ ቀይ ስጋ፣ ጨው፣ ዶሮ፣ ሲኳር ድንችና የመሳሰሉትን ምግቦች እንዲያዘወትሩ ይመከራል፡፡በዚያውም ልክ እንቁላል፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣ ስንዴና ባቄላን ከገበታቸው ማራቅ አለባቸው፡፡

2) የ ኤ (A) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት

ይህ የሰው ልጆች ወደ እርሻ ሲገቡ በተፈጠረው የአመጋገብ ለውጥ ምክንያት የተከሰተ የደም ዓይነት ነው፡፡ በዚያ ዘመንም የሰው ልጆች ለመኖነት ፊታቸውን ወደ አትክልቶች በማዞራቸው ምክንያት በጊዜ ሂደት እጅግ የዳበረ የምግብ ማላም ስርዓትን አዳበሩ፡፡ በአንጀታችው ውስጥ የሚገኙት የባክቴሪያዎች ዓይነትና ቁጥርም እጅግ ተበራከተ፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ፖም፣ አቮካዶ፣ ሰላጣ፣ ካሮት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ባቄላ፣ እርጎ፣ የስንዴ ዳቦና ፓስታ እንዲመገቡ ይመከራል፡፡ ነገር ግን እንቁላል፣ ስጋ እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን በተገቢው መንገድ ለማብላላት አንጀታቸው አልዳበረም፡፡

3) የ ቢ (B) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት

የጥንቶቹ አዳኞች ወደ ሒማሊያስ ተራሮች በመሰደድ እንስሳትንም በማላመድ የአርብቶ አደር ሕይወትን መምራት ሲጀምሩ የተፈጠረ የደም ዓይነት ነው፡፡ ቀይ ስጋ፣ ዓሣ፣ እርጎ፣ ዓይብ፣ ወተት፣ ሙዝ፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ወይንና አናናስ ተስማሚ ከሚባሉት ምግቦች መካከል ሲጠቀሱ ዶሮ፣ ስንዴ፣ ቲማቲም እንዲሁም ለውዝ እንዳይመገቡ ይመከራል፡፡

4) የ ኤቢ (AB) ደም ዓይነት የአመጋገብ ስርዓት

ኤቢ የደም ዓይነት በቅርብ ጊዜ የተከሰተ ሲሆን ከዓለም ህዝብም በአምስት ፐርሰንቱ ውስጥ ብቻ ይገኛል፡፡ የዚህ ደም ባለቤቶች ስጋንና ሌሎች የእንስሳት ተዋጽኦዎችን መፍጨት ቢችሉም የጨጓራቸው አሲድ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ ምክንያት የተመገቡት ምግብ በስብ መልክ ይከማቻል፡፡ ፍራፍሬዎችና አረንጓዴ አትክልቶች፣ ሀብሀብ እና ወይን፣ እንደ ቱና እና ሰርዲን ያሉ የባህር ምግቦችን ማዘውተር ተገቢ ሲሆን ከበቆሎ፣ የበሬና አሳማ ስጋ እነዲሁም ከአልኮሆልና ቡና መራቅ ያስፈልጋቸዋል፡፡

ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

Egypt’s Red Sea Signal: Opening the Door to a Historic Nile Agreement with Ethiopia

"sources like The National indicating Egypt's conditional openness to...

አብን በሁመራ፣ አዲረመጥ፣ ኮረም ኦፍላ፣ ጠለምት ራያና አላማጣ ሕዝቡ ለክልልም ምርጫም መሳተፍ አለበት አለ

አዲስ ሪፖርተር - "ህዝባችን ለክልሉ ምክርቤት ጭምር ምርጫ መካሄድ...

“ለዓመታት የፖለቲካ መብታቸው ተገፎ ለኖሩ ዜጎች የዲሞክራሲ ጭላንጭል የፈነጠቀ ታሪካዊ እርምጃ” ወልቃይት

አዲስ ሪፖርተር - የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና ወሰን ኮሚቴ...

“ለአራተኛ ጊዜ ተወረናል” ከወሎ ራያ አማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ከሚቴ የተሰጠ መግለጫ

አዲስ ሪፖርተር - "መንግሥትም የህዝቡን የማንነት እና የራስ አስተዳደር...