የማርበርግ ቫይረስ ምልክት ያሳዩ 6 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ በአሁኑ ሰዓት በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች የሉም

Date:

  • አዲስ ሪፖርተር -የማርበርግ ቫይረስ ምልክት ያሳዩ ስደስት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። ይሁን እንጂ በላብራቶሪ ማረጋገጥ የተቻለው የሦስቱ ብቻ መሆኑንን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በአሁኑ ሰዓት በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች አለመኖራቸው ተመልክቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተከሰተው እና ምንነቱ ለማረጋገጥ የዘረመል ምርመራ ሲካሄድበት የቆየው ሄሞራጂክ ፊቨር በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) ስለመሆኑ መረጋገጡን፤ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ በሰጡት መግለጫ ማሳወቃቸው ይታወቃል።

በወቅታዊ የጤና አስመልክቶ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ዛሬ ሕዳር 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል። በዚሁ መግለጫቸው እንዳሉት ሕዳር 3 ቀን በሽታው ይፉ ከተደረገ በኋላ በ17 ሰዎች ላይ ናሙና ተወስዶ ምርመራ ተደርጓል። በተረጋገጠ ምርመራ መሰረት በማርበርግ ቫይረስ የሞቱት ሶስት ሰዎች ናቸው። እንዲሁም በማርበርግ የተጠረጠሩና በላብራቶሪ ያልተረጋገጠ ሶስት ሰዎች፤ በአጠቃላይ ስድስት ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ አመልክተዋል። ምርመራው ከተደረገላቸው ቀሪዎቹ ሰዎች ነፃ ሆነው መገኘታቸውን ተናግረዋል።

በጤና ሚኒስቴር በኩሉ “ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከፍተኛ የዝግጅት እና የቅንጅት ሥራዎችን እየሰራን ነው” ያሉት ሚንስትሯ፤ ወደ ክልሎች ድጋፍ የመላክና ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች የተገናኟቸው ሰዎች የመለየት ሥራ እንደተሰራ አንስተዋል።

ሕብረተሰቡ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግና ከሌሎች ሕመሞች የሚለይበትን መንገድ ማወቅ ይገባል ያሉም ሲሆን፤ ምልክቱ ከታየባቸው ሰዎች ጋር የሚደረግ ንክኪ መተላለፊያ መንገዱ ነው ብለዋል። ማርበርግ ቫይረስ በትንፋሽ የሚተላለፍ አለመሆኑና ለመከላከል ንክኪን መቀነስ እጅን መታጠብ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ሰዓት በዚህ በሽታ የተያዙ ታማሚዎች አለመኖራቸውን የገለጹት ዶ/ር መቅደስ፤ ይህ ማለት የሚያዘናጋ አለመሆኑንና የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል እና ባለበት እንዲቆም ለማድረግ በርካታ ሥራዎች መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የማርበርግ ቫይረስን ለመቆጣጠር የመጀመሪያው መንገድ መከላከል ሲሆን፤ ምልክቶች የታዩባቸውን ሰዎች ሕክምና ለመስጠት ፈሳሽን የመተካት እና እንደ ሕመሙ ድጋፍ እንደሚደረግ ጠቁመዋል። ነገር ግን ለዚህ ይሆናል ተብሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጠለት መድሃኒት አለመኖሩን ተናግረዋል።

በተለያዩ ሀገራት በሙከራ ደረጃ ላይ ያሉ መድሃኒቶችና ክትባቶች መኖራቸውና ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ማለፍ ያለባቸው ሂደቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል። የማርበርግ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ በጀርመን ሀገር በአውሮፓውያኑ 1967 መታየቱን አስታውሰዋል።

ከዛ በኋላ በ12 ሀገራት ላይ የታየ ሲሆን፤ በአፍሪካ ከኮቪድ ወረርሽኝ በኋላ ጋና፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ታንዛኒያና ሩዋንዳ ላይ መታየቱን ጠቁመዋል። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰቱንም ሚኒስትሯ ጨምረው ገልጸዋል። ሕብረሰተቡ መረጃዎችን እና የጥንቃቄ መንገዶችን ከጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መከታተል እንዳለበትም አሳስበዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኃይሌ ገብረስላሴ “አረቄን እጠቀም ነበር” በማለቱ ዕግድ ተጣለበት፤ እግዱ ለዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ማህበራት ተበትኗል

አዲስ ሪፖርተር - አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ አረቄን ከዶፒንግ ጋር...

“የኢትዮጵያዊያ መከራ የሆነውን ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያና ትግራይ ምድር መንቀል ዋና ዓላማችን ነው”

አዲስ ሪፖርተር - እስካሁን በመላው ኢትዮጵያ ለተፈጠሩ ምስቅልቅሎች፣ በትግራይ...

የአማራ ክልል የወሲባዊ ጥቃት አሳስቧል፤ “በማንና እንዴት ይፈጸማል? ለሚለው በጥናት የተረጋገጠ መረጃ የለም” ጤና ቢሮ  

አዲስ ሪፖርተር - በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ጦርነትና...

በሻዕቢያና ህወሃት መካከል አለመተማመኑ ሰፍቷል፤ የሚታወቁ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ከእነ ሞንጆሪኖ ቡድን እየወጡ ነው

ስጋት ትልቁ ምክንያት ነው። ሻዕቢያ በተግባር የተፈተሸ ከሃጂ በመሆኑ...