በቅርቡ ልዩ ኮማንዶ ማስመረቁን ይፋ ያደረገው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር /ትህነግ አንድ ክፋይ የብልጽግና መንግስት “ለጦርነት ተዘጋጅቷል፤ ሊያጠፋን ነው” በሚል ያዘጋጀው የፕሮፓጋንዳ ሰነድ ይፋ ሆነበት። ሻለቃ ሃጎስ ስድስት መቶ ተዋጊዎቹ በሚቀጥለው ሳምንት እጅ እንደሚሰጡ አስታወቀ። ለሻዕቢያ እያገለገለ ያለውን የትህነግ ቡድን ለማስወገድ ከትግራይ ሰላም ኃይሎች ጋር እንደሚቀላቀል አስታወቀ።
የአገር መከላከያን “ብልጽግና” እያለ የሚጠራው የትህነግ ሰነድ፣ መንግስት “የፕሪቶሪያውን የሰላም አማራጭ ሰነድ ከአቶ ጌታቸው ረዳ፣ ሌተናል ጄነራል ጻድቃንና አሰፋ አብርሃ ጋር ነው የፈረምኩት” በማለት ስምምነቱን ባለቤት አልባ በማድረግ ሊወጋቸው እንደተዘጋጀ ቃል በቃል በሰነዱ ላይ ተቀምጧል።
ስምረት የሚባለውና አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ፓርቲ ትግራይን ለብልጽግና ለመስጠት እየሰራ እንደሆነ ተደርጎ መገለጹን ለአዲስ ሪፖርተር የደረሳት ሰነድ ያስረዳል።
ስምረት ከትናት በስቲያ በሰጠው መግለጫ ህጋዊ መስፈርቱን አሟልቶ ወደ ምርጫ እየሄደ መሆኑን ሲያስታውቅ፣ እግረ መንገዱን ከብልጽግና ጋር ግንኙነት እንዳለው ተጠይቆ ” በፍጹም” ሲል መናገሩና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ተጣምሮ ለመስራት የሚያስኬድ መንገድ ካለ ሊያየው እንደሚችል አመልክቷል።
ትህነግ ለምርጫ ወደ ትግራይ እናቀናለን የሚሉ ወኪሎችም ሆነ ፓርቲ ካለ በይፋ እንደሚያስራቸው ማስታወቁ አይዘነጋም። ስምረትን ጨምሮ አሁን የተቋቋሙ ፓርቲዎች ምርጫ እንዲካሄድ መንግስት ህግ እንዲያስከብርም እየጠየቁ ነው። ትህነግ በምርጫ ቦርድ የተነጠቀውን ህልውናውን መልሶ ለማግኘት ዳግም ጥያቄ ማቅረቡም አይዘነጋም።
ሰነዱ መንግስት ለጦርነት እየተዘጋጀ፣ መሳሪያ እየገዛ እንደሆነ አመልክቶ እነሱም በዚያው መጠን መዘጋጀት እንዳለባቸው ያሳስባል። ለሰራዊቱ መወያያ እንዲሆን የተዘጋጀው ሰነድ አክሎም ትህነግ ፋኖን እያደራጀና እያስታጠቀ እንደሆነ፣ ከሻዕቢያ ጋር ጽምዶ ፈጥሮ ኢትዮጵያን ለማጥቃት እንደሚሰራና ከሱዳን ጋር በማበር ኢትዮጵያን ከቦ የመውረር ዕቅድ እንዳለው በመግለጽ እየከሰሰ መሆኑንም አመልክቷል ይሁን እንጂ ከተጠቀሱት አካላት ጋር እንደሚሰራ በሰነዱ ላይ ቃል በቃል አልተቀመጠም።
ሰሞኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር “ተወሯል” በሚለው ወልቃይትና ጠገዴ ምንም ዓይነት ድርድር እንደሌለ ገልጾ ባወጣው መግለጫ የፕሪቶሪያውን ስምምነት እንደሚከተል ማስታወቁ አይዘነጋም።
ሰነዱ መንግስት ጦርነት ሊያነሳ በዘግጅት ላይ መሆኑን ለሰራዊቱ ለማስረዳት ባዘጋጀው ሰነድ ላይ መንግስት ትግራይ ላይ ለማስተኮስ ሐራ መሬት ላይ ታጣቂዎችን እያደራጀ መሆኑን፣ ትግራይ እንድትታወክን ነዳጅ ማሳነሱን፣ በጀት ዝቅ ማድረጉንና የኢኮኖሚ ችግር እንዲባባስ እያደረገ እንደሆነ በመግለጽ ይከሳል።
ትህነግ በቀርቡ ለሰራዊቱ የደሞዝ ጭማሪ ማድረጉ ይፋ ሆኗል። በዚሁ መሰረት 6000 ብር በወር ይከፍላል። 2400 ብር በካሽ የሚሰጥ የቀለብ ተጨማሪ ይታከልበታል። በዚሁ ስሌት መሰረት ተጨማሪ ብር ያስፈለገው ትህነግ የሚሰጠውን በጀት ለሰራዊት እያዋለ ሕዝብ እንደሚጎዳ መንግስት ማስታወቁ አይዘነጋም።
የንዳጅና የሸቀጥ እጥረትን በተመለከተ ነዋሪዎችን ዋቢ ያደረጉ የትግራይ አክቲቪስቶችና ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ሸቀጡም ቤኒዚኑም ወደ ኤርትራ እንደሚጋዝ ማመልከታቸው፣ ይህንኑ ዜና በምስልም አስደግፈው እንዳሰራጩ አይዘነጋም። ስለዚህ ጉዳይ ሰነዱ ያለው ነገር የለም።
ቀደም ሲል ይፋ በሆነው ለጦርነት ዝግጅት ትህነግ ያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ዕቅድ ልዩ ሰነድ እንደሚያመለክተው፣በአጠቃላይ 6,770,200,000.00 (ስድስት ቢሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ብር ለመሰብሰብ ያለማል። ይህ ገንዘብ በዋነኛነት የሚሰበሰበው በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና የንግድ ተቋማት ላይ ጫና በማድረግና አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በመጠቀም እንደሆነም እያንዳንዱን ዘርፍና ለዚሁ ስራ በየዘርፉ የተመረጡትን የኮሚቴ ሰብሳቢዎች ስም ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም።
ሰነዱ የውጭ አገር ዜጎች ወደ ትግራይ እንዳይሄዱ መንግስት ገደብ እንደሚያደርግ፣ በመግለጽ ሰራዊታቸው ይህን ሁሉ እንዲመክት ያበረታታል። ሰነዱን የተለመደ ፐሮፓጋንዳ እንደሆነ የሚገልጹና በትግራይ አሁን ላይ ለመዋጋት ፍላጎት ያለው የበታች ሰራዊት እንደሌለ ይናገራሉ።
ከፍተኛ የጦር መኮንኖቹን አቶ ስብሃት አስቀድመው በአቻ ጋብቻ የተዛመዷቸው በመሆናቸው እሳቸውን ተክታ የትህነኝ የአደዋ ርስትነት እንድታስጠብቅ በምትሰራዋ እህታቸው ሞንጆሪኖ እንደሚመሩ የሚናገሩ “እነዚህ ወገኖች አስቀድመው እንዳስጨረሱት የሚያልቅላቸው ሰው የለም”
አንድ አዲስ አበባ የሚኖሩ ጄነራል የትግራይ ሕዝብ አሁን ላይ ስለ ጦርነት መስማት እነድማይፍለግ ሲያስታውቁ ” የትግራይ ሕዝብ እንኳን በመሳሪያ በቲማቲም መፈናከት አይፈልግም” ማለታቸውን ገልጸን መዘገባችን የሚታወስ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን በማይጸብሪ ላለው የአገር መከላከያ ሰራዊት እጁን የሰጠው ሻለቃ ሃጎስ ትህነግ የትግራይን ሕዝብ አነሳስቶ ለማዋጋት ምክንያት እንደሌለው በማስታወቅ በቀርቡ ከትግራይ ሰላም ኃይሎች ጋር ተቀላቅሎ እስከወዲያኛው የማስወገዱ ዘመቻ አካል እንደሚሆን አመልክቷል።
ትግራይ ቱዴይ ከሚባል የዩቲዩብ ቻናል ጋር ከማይጸብሪ አጭር ቃለ ምልልስ ያደረገው ሻለቃ ሃጎስ እንዳለው ለመዋጋት ምክንያትና ዓላማ ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው። ትህነግ ሁለቱም የሉትም ብሏል።
ከሻዕቢያ ጋር የተፈጸመውን ቅንጅት “ክህደት” ያለው ሻለቃ ሃጎስ፣ እጁን ለአገር መከላከያ እንዲሰጥ ያደረገው ዋና ምክንያትም ይህ የትግራይ ሕዝብን ሳይመርጥ የጨፈጨፈና ግፍ የሰራ ኃይል ጋር የተፈጸመው ጽምዶ እንደሆነ አመክቷል።
“400 ኃይል ይዤ ገብቻለሁ፤ 600 የሚሆኑት በሚቀጥለው ሳምንት ይገባሉ፤ አንድ ላይ ከትግራይ ሰላም ኃይሎች ጋር ሆነን ትግሉን እናስቀጥላለን” ሲል ይፋ የተናገረው ሻለቃ ሃጎስ በጥቅሉ 1200 በላይ የራሱ ጭፍራ እንዳለው አስታውቋል።
ሻለቃ ሃጎስ በ23/03/2017 ከሸፈተ በኋላ አሁን ለመከላከያ እጁን ሲሰጥ ” ኢትዮጵያን ለማዋረድ ቆርጦ ከተነሳ ኃይል ጋር መቀጠል አይቻልም። ይህ ኃይል መወገድ አለበት” ብሏል። በዚህ ሚዲያ ቃለ ምልልሱ የሃገር መከላከያ ላደረገለት አቀባበል አመስግኗል።
በ1992 ሻዕቢያ ባድመን በድንገት በወረረ ወቅት ኢሃዴግ የኢትዮጵያን መከላከያ “የመንግስቱ ኃይለማሪያም ሰራዊት” በማለት አፍርሶ ስለነበር፣ የባህር ኃይልና የአየር ኃይሉን በትኖ ስለነበር መመከት አልተቻለም ነበር።
ዳግም ጥሪ ተደርጎ ” የደርግ” የተባለውና መንገድ ላይ ቆሞ እንዲለምን የተደረገው የቀድሞ የኢትዮጵያ አለኝታ ጥሪውን ተቀብሎ ተመለስ እስኪባል ድረስ ሻዕቢያን እያራወጠ አስመራ ጫፍ በደረሰበት ጦርነት ወቅት፣ ሻለቃ ሃጎስ ጦሩ መልሶ እስኪደራጅ የራሱን ሚሊሻ አደራጅቶ ሻዕቢያን በሽራሮ አቅጣጫ ሲዋጋ እንደነበር የሚያውቁት ይመስክራሉ።
Website፡ https://addisreporter.com/
Email፡ info@addisreporter.com
Telegram፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
Phone no ፡ +251981866434 / +251116393393






