የ9 ቢሊዮን ዶላር የሙስና ቅሌት ተከትሎ የኢልሃን ኦማር ሃብት ማሻቀቡ ከፍተኛ ጥርጣሬን ቀሰቀሰ

Date:

አዲስ ሪፓርተር – በአሜሪካ የሚኒሶታ ግዛት የፌዴራል የምክርቤት አባል ትውልደ ሶማሌያዊቷ ኢልሃን ኦማር እና ባለቤታቸው ያስመዘገቡት ያልተጠበቀ የሀብት እድገት የአገሪቱን የፖለቲካ ማህበረሰብ እያነጋገረ እንደሚገኝ ፎክስኒውስ ዘግቧል። ለዓመታት “ሚሊየነር አይደለሁም” ስትል የቆየችው ኢልሃን ኦማር አሁን ይፋ የሆኑ የፋይናንስ መግለጫዎች ግን የሀብትመጠኗ በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በ3,500 በመቶ ማደጉን ያመለክታሉ። ይህ ያልተጠበቀ “የሀብት እድገት” በሚኒሶታው የ9 ቢሊዮን ዶላር የሙስና ቅሌት ማግስት መከሰቱ ጉዳዩን በብዙዎች ዘንድ አጠራጣሪ አድርጎታል።

የሀብት ምንጩ እንቆቅልሽ

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ መጠነኛ ገቢ እንዳላቸው ሲገለጽ የነበሩትኢልሃን ኦማር፣ በቅርቡ ይፋ በሆነው የሀብት ምዝገባ ሰነድ ላይያላቸው የሀብት መጠን እስከ 30 ሚሊዮን ዶላር እንደሚደርስተመልክቷል። ለዚህ ድንገተኛ ብልጽግና እንደ ምክንያትየቀረበው የባለቤታቸው ቲም ማይኔት የንግድ ድርጅቶች ትርፍ ቢሆንም፣ የኩባንያዎቹ ዋጋ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ያሳየው እድገት “ተፈጥሯዊ አይደለም” የሚል ትችት አስከትሏል። በተለይም በ2023 ሪፖርት ላይ 1,000 ዶላር ብቻዋጋ የነበረው “Rose Lake Capital” የተሰኘው ድርጅት፣ በአሁኑወቅት እስከ 25 ሚሊዮን ዶላር ማውጣቱ ትልቅ ጥያቄፈጥሯል።

መረጃዎችን የማጥፋት ሙከራ

የፌዴራል ምርመራ ቢሮ (FBI) በሚኒሶታ በሚገኙ የሕፃናትመዋያ ማዕከላት ላይ የሚካሄደውን የቢሊዮን ዶላር የምዝበራምርመራ ማፋጠኑን ተከትሎ፣ የኢልሃን ኦማር ባለቤት የኩባንያቸውን ድረ-ገጽ መረጃዎች ማጥፋታቸው ተረጋግጧል። ከድረ-ገጹ ላይ የከፍተኛ አመራሮች ስም እናየኩባንያው ዝርዝር ስራዎች እንዲሰረዙ መደረጉ፣ የምርመራአካላት በትኩረት እንዲከታተሏቸው ምክንያት ሆኗል።ሪፐብሊካን የምክር ቤት አባላት ይህንን ድርጊት “የወንጀልማስረጃን የመደበቅ ሙከራ” ሲሉ ጠርተውታል።

የሚኒሶታው የምዝበራ ቅሌት እና የፖለቲካ ትስስሩ

በሚኒሶታ ግዛት በሶማሊያ ተወላጆች የሚመሩ የሕፃናት መዋያማዕከላት፣ ምንም ዓይነት ሕፃናት ሳይንከባከቡ በሚሊዮን የሚቆጠር የመንግስት ገንዘብ ሲቀበሉ መቆየታቸው በቅርቡ መጋለጡ ይታወሳል። ይህ የምዝበራ ተግባር “እንደ ፈቃድያለው የገንዘብ ማተሚያ ማሽን” ተብሎ የተገለጸ ሲሆን፣ በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል የተወሰኑት ለኢልሃን ኦማር የምርጫ ዘመቻ ከፍተኛ ገንዘብ የለገሱ መሆናቸው በኦማር እና በምዝበራው መረብ መካከል ያለውን ግንኙነት አጠራጣሪ አድርጎታል።

የቴክሳሱ ተወካይ ቺፕ ሮይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣“አንድ የኮንግረስ አባል በስልጣን ላይ እያለ በዚህ ደረጃ ሀብታም መሆኑ አሳሳቢ ነው። ኢልሃን ኦማር በሕግ ከተደነገገው ውጪ በሙስና መሳተፏ ከተረጋገጠ፣ ከስልጣን መወገድ ብቻ ሳይሆን ዜግነቷ ተሰርዞ ከአገር መባረር አለባት” ብለዋል።

ቀጣይ እርምጃዎች

የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር እና የምርመራ ቢሮ የገንዘብ ፍሰቱንና የንብረት ዝውውሩን በጥብቅ እየተከታተሉ ሲሆን፣ በግዛቱ አስተዳደር በኩልም የገዥው ቲም ዋልዝ አስተዳደር በጉዳዩ ላይ የነበረው ተሳትፎ ወይም ቸልተኝነት እየተመረመረ ይገኛል። የኢልሃን ኦማር ወገኖች በበኩላቸው የቀረበው ክስ“ፖለቲካዊ ጥቃት ነው” በማለት እያጣጣሉት ቢሆንም፣ በየቀኑ የሚወጡ አዳዲስ የሰነድ ማስረጃዎች ግን ጫናውን እያበረቱት ነው።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የአዲስ አበባ ሕዝብ የእናት ሀገር ጥሪ ተሳትፎና ኮሎኔል መንግሥቱ

የእናት አገር ጥሪ ከተደረገ በኋላ መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ...

ቢሾፍቱ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ፤ ኢትዮጵያን ወደ መፃኤ ዘመን የሚያሻግር የሎጂስቲክስ አብዮት

ኢትዮጵያ ከቢሾፍቱ ሰማይ ስር የኢኮኖሚና የሎጂስቲክስ ካርታዋን እንደገና ለመሳል...

“ጥርስ የሌለው ውሻ” የሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የዓለም መፃኢ እጣፈንታ

አዲስ ሪፖርተር - ፕሬዛዳንት ትራምፕ አሜሪካን ከተባበሩት መንግስታት ደርጅት...

በዘመነ ትራምፕ ጫና ውስጥ የወደቀችው ሶማሊያ እና ለሶማሌ ላንድ ተስፋን ያለመለመው አዋጅ

አዲስ ሪፓርተር - ከሶማሌላንድ የሉዓላዊነት ጥያቄ እና ከእስራኤል እውቅና...