ኢትዮጵያ በዓለም ሁለተኛ የተባለውን የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ በስድስት ወር ትከፍታለች

Date:

“የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ እንከፍታለንእንከፍታለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ። ዩኒቨርስቲው ዕውን ሲሆን ከዓለም ኢትዮጵያን በዘርፉ ዩኒቨርስቲ ካላቸው አገራት ሁለተኛ ያደርጋታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ የመሰናዶ ሥራዎች በቀጣዮቹ ስድስት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ በማመልከት የተናገሩት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ 75ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲው ተገኝተው የውይይት መነሻ ጽሑፍ ባቀረቡበት ወቅት ነው፡፡

ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዩኒቨርሲቲ ለማቋቋም እየሰራች መሆኗንና ይህም በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚተገበር ያስታወቁት አብይ አሕመድ “እንፍጠን” በማለት ኢትዮጵያን ከቴክኖሎጂ ጋር ባያያዝ ቁልፍ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ የኤአይ (AI) ዩኒቨርሲቲ ለመገንባት ዝግጅቷን ማጠናቀቋን እና በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ ሥራው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ ሲያደርጉ ታዳሚዎች ሲያደንቁ ታይተዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የተቋቋመ አንድ ዩኒቨርሲቲ ብቻ መኖሩን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያው ከስድስት ወር በሁዋላ ይፋ የምታደርገው ዩኒቨርስቲ ተቋም ሁለተኛው እንደሚሆን አስታውቀዋል። ለዚህም መፍጠን እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ዩኒቨርሲቲው አንድ ሺህ የሚደርሱ ብቁ ተማሪዎችን የማስመረቅ አቅም እንዲኖረው መታቀዱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሐመድ፣ ከእነዚህም መካከል 100 የሚሆኑት ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን የምትሰጠው የነፃ ትምህርት ዕድል (Scholarship) ተጠቃሚዎች እንደሚሆን ይፋ አድርገዋል። ለአኅጉራዊ ትስስር ሲባል፣ ለእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ሁለት ተማሪዎች ኮታ እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው በጥራት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ከኢትዮጵያ ተማሪዎች መካከል በውድድር ከፍተኛ ውጤት የሚያመጡ ብቻ ተመርጠው እንደሚገቡ አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በዋናነት በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)፣ በማሽን ለርኒንግ፣ በሮቦቲክስ፣ በዴታ ማይኒንግ እና በኮምፒውቲንግ ዘርፎች ላይ ብቻ ትኩረቱን አድርጎ በተግባር የተደገፈ ትምህርት ይሰጣል ብለዋል።

በዩኒቨርሲቲው የትምህርትና ምርምር ሥራዎች ላይ ከሀገር ውስጥ ባለሙያዎች በተጨማሪ የዳያስፖራ አባላት እና ዓለም አቀፍ ምሁራን ተሳታፊ እንደሚሆኑም ገልጸዋል።

ይህ ተቋም መቋቋሙ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ተወዳዳሪነት ከፍ እንደሚያደርገው እና አዲሱን ትውልድ ለዘመኑ የዕውቀት ሽግግር ዝግጁ እንደሚያደርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመላክተዋል።

የዩኒቨርስቲው መከፈት በዘመናዊው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ሥነ-ምሕዳር ውስጥ የኢትዮጵያን ደረጃ ከፍ የሚያደርግ፣ ተግባራዊና የዘመኑን እውቀት የታጠቀ የሰው ኃይል ለመፍጠር ያለመ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው አመልክተዋል።

ፌስቡክ፡ https://web.facebook.com/addisreporternews/
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

የኤርትራ አፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች ግንባር ፈጠሩ፤ “ስምምነቱ ለሻዕቢያ አስደንጋጭ መርዶ ነው” አቶ አብዲ ሼኽ መሐመድ

አዲስ ሪፓርተር - በኤርትራ የሚንቀሳቀሱት ሁለት የአፋር ተቃዋሚ ድርጅቶች...

ለኢትዮጲያ ሲሉ ቀይ ባሕር ላይ የወደቁት ጀግኖች አደራ ተቀባይ

ኢትዮጵያ ቀይ ባሕር የትናንትና ታሪኬ ኾኖ አይቀርም የሚል አጀንዳዋን...

ሀሰን ሼኽ በመጨረሻ “እኔም የቬንዙዌላ ፕሬዚዳንት ዕጣ ይደርሰኛል” በሚል ጭነቀት ውስጥ መሆናቸው ተሰማ

አዲስ ሪፖርተር - እስራኤልን ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከሶማሊላንድ ጠራርገው...