አዲስ ሪፖርተር – አቶ ነዓምንና ዘለቀና ጃዋር መሐመድ አዲስ “ጽምዶ” ከፈጠሩ በኋላ ግምገማ አካሂደዋል። የአዲስ ሪፖርተር የዋሽንግቶን ተባባሪ ባሰባሰበው መረጃ አቶ ነዓምንና ጃዋር በሚመሩት ቡድን ውስጥ የተገመገመው የተካሄደው ጃዋር ግብጽ ደርሶ ከመጣ በሁዋላ ነው። በዚሁ የዙም ስብሰባቸው ሕዝብ እንዲነሳ የሚያደርጉ ምክንያቶች በበቂ ደረጃ አልተፈጸሙም።
ጃዋር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወለጋ ገጠር ድረስ ገብተው የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውን፣ ፋብሪካ መመረቃቸውንና ከሕዝብ ጋር መገናኘታቸውን ተከትሎ “በቅርቡ የእርስ በእርስ የብሄር መተላለቅ ይነሳል” በማለት መናገሩ ይታወሳል። ይህንኑ ንግግሩን ተከትሎ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወለጋ በመሄዳቸው ለምን የብሄር የእርስ በእርስ መተላለቅ ይነሳል? የምታውቀው፣ ወይም የተዘጋጀህበት ጉዳይ ካለ አስረዳ” በሚል አዲስ ሪፖርተርን ጨምሮ በርካታ ጸሐፊዎች ጥያቄ አቅርበው ነበር።
ጠበቃ ወንድሙ ኢብሳ ከአዲስ ሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ “ጃዋር ባደገበትና በኖረበት መንደሩ አንድም ክርስቲያን ቀና ብሎ አይሄደም። ከሄደም አንገቱን በሜንጫ ይቆረጣል ብሎ ነበር። አሁንም አርሲ ውስጥ ይህንን የሚፈጽሙትን ያውቃቸዋል። ተው ይበላቸው” ሲሉ ጃዋር ሳያውቀው የሚሆን ነገር እንደሌለ ተናግረው ነበር።
ጃዋር አስቀድሞ በተናገረው መሰረት በወለጋ የፋኖ ታጣቂዎች ንጹሃንን እንደገደሉና በሺህ የሚቆጠሩ መፈናቀላቸው ይፋ ሆኗል። የሸኔ ታጣቂዎችም በአርሲ ግድያ መፈጸማቸው በኢትዮጵያ ሰብአዊ መበቶች በኩል ይፋ ሆኗል። በዚህ መካከል የአመጽ ጥሪ ለማስተላለፍ የያዘውን ቀጠሮ ሰርዞ ግብጽ ደርሶ የመጣው ጃዋርና አቶ ነዓምን የሚመሩት ቡድን ተሰብስቧል።
ከአራት ቀን በፊት ስብሰባውን ያደረገው ይህ ቡድን “ሕዝብ እንዲቆጣ የሚያደርጉ ተግባራት አልተፈጸሙም” ሲል በየስፍራው የተሰማራውን አስፈጻሚ ሴል ወቅሷል።
የአዲስ ሪፖርተር የዲሲ ተባባሪ የቡድኑ አባል የሆኑ የአብሮነት አባላትን በመጥቀስ እንዳሉት፣ ኃይማኖትን ተንተርሶ የተጀመረውን ልዩነት ማጋጋሉ ከሁሉም በላይ ውጤታማ እንደሚያደርግ ጃዋርና አቶ ነዓምን ባሉበት ስብሰባ በስፋት ተነስቷል። በዚሁ መሰረት “ብልጽግና ጸረ ኦርቶዶክስ ነው” በማለት እንደ አዲስ የተነሳውን ቅስቀሳ ለማስፋት መነሻ ምክንያቶች ከአርሲ ውጭ በሌሎች አካባቢዎችም እንዲፈጸሙ ተብሏል።
በህጋዊ የምርጫ ቦርድ ምዘገባ አድርገው ዕውቅና ከተሰጣቸው ፓርቲዎች መካከል ከዚህ ቡድን ጋር የሚሰሩ፣ በኃይማኖትና በብሄር ልዩነት ሰበብ የሚከሰቱ ማናቸውንም ተግባራት በመቃወም፣ በተከታታይ በተለያዩ አውዶች ለሕዝብ ቁጣን በሚቀሰቅስ መልኩ ፕሮፓጋንዳ መስራት ላይ መፋዘዛቸው በስብሰባው ተመልክቷል። ይልቁኑም ምርጫውን በሞቀ ክርክር እያጀቡት እንደሆነ አመልክተዋል። ይሁን እንጂ በግል ደረጃ አንዳንድ የፓርቲዎቹ አባላት መንግስትን በማሳጣት በኩል ያልተጠበቀ ስራ እየሰሩ መሆናቸውም ተነስቷል።
ከዚህ ስብሰባ በሁውላ በቀጣይ የተነደፉ ስልቶችን ያካተተ ሰነድና፣ ተሳታፊዎች ሰነዱን ዓይተው ስብሰባ እንዲገኙ የሚጋብዝ ደብዳቤ ተዘገጅቶ ተበትኗል። ደብዳቤው ምርጫውን መቀደም፣ መንግስትን ጦርነት ጠማቂ፣ ሰላም የማይወድ፣ ሕዝብ ሊያስጨርስ ሌት ተቀን የሚሰራ፣ አድርጎ የሚስል ነው።
ራሱን “የህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል እንቅስቃሴ አመቻች ጊዚያዊ ኮሜቴ” በሚል ስያሜ የሚጠራውን ስብስብ ወክለው ደብዳቤውን በርዕስ ለቀድሞ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ገደይ ዘርዓጺዮን የጻፉት አቶ ነዓለም ዘለቀ ናቸው። የካቲት22 ቀን 2018 ዓ.ም የተጻፈውን ደብዳቤ ያዘጋጁት አቶ ነዓምን ዘለቀ ደግሞ የሻዕቢያ ወኪል ሆነው በሰሜን አሜሪካ ያሉ “ኢትዮጵያዊ” ነን የሚሉትን ተቃዋሚዎች የሚመሩ፣ የሚያሰባስቡ፣ ድጎማ የሚያመቻቹ፣ አጀንዳ እየተቀበሉ የሚያሰራጩ እንደሆኑ የአብሮነት አባላት በተደጋጋሚ ይመሰክሩባቸዋል።
አቶ ነዓምን በአብሮነት ስብሰባ ላይ ከግብጽና ሻዕቢያ ጋር የሚፈጠረው ሕብረት ከብሄራዊ ጥቅም አንጻር እንዴት ይታያል? ሻዕቢያም ሆነ ግብጽ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ናቸው በሚል ለተነሳ አስተያየት “ይህንን አሁን አታንሱ። ይህ ጉዳይ አይነሳም” በማለት ሲመልሱ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው “እኔም ከነዓምን ጋር እስማማለሁ” ሲሉ የዚሁ እንደ ጃዋር ያሉበት ቡድን አባል የሆኑትና ራሳቸውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሚሉት አቶ ታሬድ ኃይለማሪያም “ይህን መንግስት ለማውረድ ከሴታንም ጋር ቢሆን እንሰራለን” በማለት ለላካቸው ቡድን ታማኝነታቸውን መግለጻቸውን ስብሰባው ላይ የነበሩ ለአዲስ ሪፖርተር ማስታወቃቸውን ገልጸን መዘገባችን አይዘነጋም።
አቶ ልደቱ በመሰረቱት አብሮነት ውስጥ የተዋለደው ይህ ቡድን ስብሰባ ላይ እንደ ማሟያ ከተለያዩ ብሄረሰቦች የተካተቱት “እኛ እንደ እናንተ ከግብጽና ኤርትራ ገንዘብ አይከፈልንም፤ እኛን እንደመጠቀሚያ ለማድረግ አታስቡ” በማለት የተሰማቸውን ቅሬታ በቁጣ ገልጸው እንደነበርም ይታወሳል። ከግብጽና ሻዕቢያ ገንዘብ እንደሚከፈላቸው ተጠቅሶ ወቀሳ የተሰነዘረባቸው አቶ ነዓምንም ሆነ ሰብሳቢው አልደቱ በወቅቱ ዝምታ መምረጣቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው። ስብሰባው ካለቀ በኋላ ግን በግል ሰዎቹን የማባበልና የማሳመን ስራ ለመስራት ሙከራ ተደርጓል።
“ሀገር ለማዳን የቀረበ አስቸኳይ የትብብር ጥሪን ይመለከታል” በሚል ርዕስ ከሻዕቢያ ወኪል አቶ ነዓምን የተሰራጨው ደብዳቤ አገሪቱን እየመራ ያለው መንግስት በኃይማኖት ሳቢያ፣ በብሄርና በጥቅሉ በማንነት ህዝብ እያጠቃ መሆኑን፣ ኑሮ መወደዱን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መወገድ እንዳለባቸው በስፋት ዘርዝሮ “ምን ማድረግ እንዳለበን በዙም እንመካከር” የሚል ነው።
በዙም በተደጋጋሚ፣ በተለያዩ ድርጅቶችና ስብሰቦች ሲደረጉ ከነበሩት ስብሰባዎች የዚህኛው ስብሰባ ምን ልዩነት እንዳለው በይፋ የማይገልጸው የጥሪ ደብዳቤ፣ በተናጠል የሚደረግ ትግል ውጤት እንደማያመጣ ያስታውቃል። በአሜሪካ ያሉትን ይሀተለያዩ ሕብረቶች አስመልክቶ የቪኦኤ የምስራቅ አፍሪቃ አስተባባሪ የነበሩት አቶ ነጉሱእ አክሊሉ ከጋዜጠኝነታቸው ጎንለጎን ካደራጁት ኢትዮጵያን አድን ጋር ከሃያ አምስት በላይ እድር መሰል ስብሰቦች እንዳሉ መረጃዎች ያመልክታሉ።
“በተበታተነ የትግል አካሄድ ከመቀጠል ይልቅ በጋራ ታግለን ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ምን ዓይነት የትግል ትብብር ልንፈጥር እንችላለን?በሚለው አንገብጋቢና ወቅታዊ አጀንዳ ላይ ተወያይተን መፍትሄ ላይ ለመድረስ እንድንችል በማሰብ በመጭው ሳምንት እሁድ March 8 ቀን በዙም በሚደረግ ስብሰባ እንዲካፈሉ ጠርተነዎታል” የሚለው የአቶ ነዓምን ደብዳቤ፣ ከኢንጂነር ዘርዓይ በተጨማሪ ደብዳቤውን ለአቶ መሐመድ ሁሴን፣ ባንተ ይሁን፣ መስፍን ተፈራ ፣ክፍሉ ታደሰ፣ መሳይ ከበደ ፣ስፋዬ ወልደዮሐንስ ፣ዶ/ር ታከለ አርጋው፣ ንጉሴ መንገሻ፣ ሰብለ መንግስቱ ፣ዶ/ር ሰለሞን ወልደአብ፣ ዶ/ር መላኩ ተገኝ ፣ ተስፋሚካኤል መኮንን ፣ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ፣ሰለሞን ጥላሁን ፣ዩሱፍ ያሲን ፣ግርማ ጥሩነህ ፣አንተነህ ግርማ፣ ወሰን ደበላ ፣እስማኤል ግሮሰ ፣ሰለሞን ገብረሥላሴ ፣አቻምየለህ ደበላ እና ኦባንግ በግልባጭ በትነዋል።
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የእይራሳቸው እድር መሳይ ስብስብ ያላቸውና በርካቶቹ እድሚያቸው የገፋ የቀድሞ ፖለቲከኞች በዙም ለሚደረገው ስብሰባ ሁለት ሁለት ተዎካዮች እንዲልኩ ታዘዋል።
በደብዳቢያቸው ማሳረጊያ “ተባብረን ሀገራችን ኢትዮጵያን ከመጥፋት እናድን! ሕዝባችንን ከዘረኛዉ፣ አረመኔውና አምባገነናዊው አገዛዝ ነጻ አዉጥተን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርአት እናሸጋግር” ሲሉ የሻዕቢያው ወኪል አቶ ነዓምን ተመኝተዋል። የስብሰባውንም ባለቤት “የህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል እንቅስቃሴ አመቻች ጊዜአዊ ኮሜቴ” እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በቅርቡ ምርጫን አስመልክቶ ስብሰባ የተቀመጠው ብልጽግና፣ የወሰነናቸው ይፋ ያልሆኑ ውሳኔዎች በውጭ አገር ያሉ ተቃዋሚዎችንና ርዥም ዓመት በተቃርኖ ዕድሜያቸውን ላሳለፉ አስደንጋጭ እንደሆነ ተሰምቷል። የአቶ ነዓምንና የጃዋር ጥምረት “ምርጫውን ቅደሙ” በሚል በስፋት እንዲንቀሳቀስ አመራር የተሰጠው በምርጫው ሰፊ ቁጥር ያለው የተቀናቃኝና የግል ተወዳዳሪ አባላት ወደ ፓርላማ እንደሚገቡ በመሰማቱ ነው።
በኢትዮጵያ ታሪክ ተመዝግቦ የማያውቅ የተቀናቃኝና የግል ተወዳዳሪዎች ፓርላማ ከገቡ በውጭ ያለው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ይከስማል። በዚህ ሳቢያ በህዝባዊ እምቢተኛነት ስም ረብሻ ማስነሳት፣ ምርጫ እንዳይካሄድ አገሪቱ ውስጥ ትርምስ ማስነሳትና ወደ ሽግግር መንግስት ለመሄድ እነ ጃዋር ከመቼውም በላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ላይ ያነጣጠረ፣ ብሶትና ንዴት የሚቀሰቅስ ቅስቀሳ እንዲካሄድ የሚያደርግ ዕቅድም አውጥተዋል።
አዲስ ሪፖርተር ከወር በፊት ሰነዱን ጠቅሳ እንደዘገባችው የኢትዮጵያን ቁልፍ የመሰረተ ለማት ተቋማት፣ ታላላቅ ኢንቨስተሮችን፣ ከፈተኛ ገቢ የሚያስገቡ ማምረቻዎችና ፕሮጀክቶችን በመለየት የስም ማጥፋት ዘመቻ ይካሄዳል። ታጣቂዎች ተቀናጅተው በመናበብ ህዝብን የሚያበሳጩና የሚያስቆጡ ተግባራትን እንዲፈጽሙ ይደረጋል። በተለይም በኃይማኖት በኩል ልዩነትን የሚያገዝፉ ግድያዎች፣ የቤተክርስቲያን መቃተል፣ የአገልጋዮች መታፈንና የመሳሳሉት ተግባራት እንዲፈጸሙ ይደረጋል።
ከዚሁ ጋር ጎን ለጎን በዚሁ ጎራ ያሉ ሚዲያዎች በትጋት ይህንኑ ድርጎት ህዝብ እንዲከፋው፣ እንዲቆጣ በተለያዩ አገባቦች ያሰራጫሉ። ጃዋር የሚዲያ ባለሙያ በመሆኑ የመሪነቱን አክሊል ደፍቶ የሚመራው የትርምስ አጀንዳ ሰሞኑን በተጀመረበት አግባብ እንደሚቀጥል እየተሰማ ነው።
በቀረበው አዲስ ሰነድ “ይህ 7ኛዉ ምርጫ ለትግል አመች የሆነ የአንድ የዕድል በር እንደከፈተ ይሰማናል፤ ሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ለማካሄድ የሚያስችል ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነም እናምናለን፤ ሕዝቡ ያለፉት ስድስት ምርጫዎች በኑሮው ምንም ለዉጥ እንዳላስገኙለትና፤ በተለይም ይህ ሰባተኛዉ ምርጫ ሀገራችን በጦርነትና የእርስበርስ ግጭት፤ በኢኮኖሚ ዉድቀት፤ የኑሮ ዉድነትና ሙስና በተንሰራፋበት፤ ዜጎች ከምንጊዘዉም በባሰ ግፍና ሰቆቃ በሚሰቃዩበት ወቅት፤ ሊደረግ የታሰበ በመሆኑ፤ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለማስረዳት መልካም አጋጣሚ ነው እንላለን፤ ሕዝቡም በኑሮዉ ምንም ለዉጥ በማያመጣ የይስሙላ ምርጫ ከመሳተፍ ይልቅ፤ በሰላማዊ ሕዝባዊ እምቢተኝነት ትግል በአንድነት በመነሳት መሠረታዊ ለዉጥ ለማምጣት እንዲታግል ጥሪ ለማድረግ አመች ሁኔታን እንደፈጠረ እናምናለን” ይላል።
“በኃይማኖት፣ በብሄርና በተለያዩ አግባቦች በአገሪቱ ብጥብጥ እንዲነሳና እስካሁን የተነሱትንም ብጥብጦች ስፖንሰር የሚያደርጋቸው ማን እንደሆነ ለሚያውቁ ይህ ትልቅ በራስ ላይ የተሰጠ ምስክርነት ነው” በማለት ሰነዱን የላኩት ወገኖች፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን ለመበተን ስምምነት ላይ የደርሰውን የሽግግር መንግስት አባላት ዝርዝር አስደግፈው ተጨማሪ መረጃ እንደሚያቀርቡ አመልክተዋል።
ሻዕቢያ በሚመራውና ትህነግ በሚያጅበው አዲስ የሽግግር መንግስት ዕቅድ የአገር መከላከያ ሙሉ በሙሉ እንዲፈርስ፣ የቀድሞው ህገመንግስትና የክልሎች ካርታ ባለው እንዲቀጥል ስምምነት ላይ ተደርሷል። ነዓምን ዘለቀ፣ ጃዋር መሐመድና ገዱ አንዳርጋቸው ቁልፍ ቦታ በያዙበት በዚህ የስልጣን ድልድል ሰነድ ኢትዮጵያ መከላከያዋ ፈርሶ የሰላም ገነት እንድትሆን “የወደብና የባህር በር ጥያቄ አይነሳም” የሚል ቃል ኪዳንም አለበት።
ይህን እውን ለማድረግ ነው ለኢትዮጵያዊያን አዲስ የትርምስ ጥሪና የአመጽ ዕቅድ የተዘጋጀላቸው። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከትህነግ ሰዎች ጋር በአዲስ አበባ የተጀመረው ንግግር ነገሮችን በሙሉ ሊያከሽፍ እንደሚችል እየተጠቆመ ነው። በትርምስ አጀንዳ ቀረጻው ውስጥ ከሚሳትፉት ውስጥ በሰላም ወደ አገር ቤት ገብተው ፓርላማ ለመግባት እንዲመቻችላቸው ጥያቄም ያቀረቡ አሉ። ዝርዝሩን እንመለስበታለን።
ዜናውን በዩቲዩብ ይከታተሉ https://www.youtube.com/watch?v=hP0FWOl08g4
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393






