አልቡርሃን በሽብርተኛነት እና በዲፕሎማሲ ገደል ጫፍ፤ በዙሪያቸው ያሉትን ይዘው ይገነደሳሉ ወይስ ይተርፋሉ?

Date:

አዲስሪፓርተር – በገልፍ ሃገራት በአሜሪካና እስራኤል ጥምር ጦር በኢራን ላይ የከፈቱት ወታደራዊ ዘመቻ በሱዳን ፖለቲካዊና ወታደራዊ አሰላለፍ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል። ይህንኑ ተከትሎ በአብደል ፋታህ አል-ቡርሀን የሚመራው የሱዳን ጦር ቀውስ ገጥሞታል። አልቡርሃን የገቡበት ቀውስ እንደ ኤርትራ ያለች ለጎርቤታቸውንና ወዳጆቻቸውን ይዘው ይገነደሳሉ ወይስ ይህን የገደል ጫፍ ዲፖሎማሲ ያልፉታል? በሚል እያነጋገረ ነው።

በሀገር ውስጥ በፈጥኖ ደራሹ ጦር በተደጋጋሚ እየደረሰበት ያለውን ወታደራዊ ሽንፈት ለመቀልበስ በኢራን ድሮኖች ላይ ከፍተኛ ጥገኝነት ያለው የአልቡርሃን ጦር፣ በዓለም አቀፍ መድረክ ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ላለመጋጨት ጥንቃቄ የተሞላበት የዲፕሎማሲ እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመልክታሉ። ይህ አካሄድ ጦሩ በጦር ሜዳ ካለው ፍላጎት እና በዲፕሎማሲው ረገድ ሊደርስበት በሚችለው መገለል መካከል ባለው ክፍተት ምክንያት ውጥረት ውስጥ እንደከተተውም እየተገለጸ ነው።

የአልቡርሃን ወታደራዊና ፓለቲካዊ አስተዳደር  በተለይ በአሜሪካ በአሸባሪነት ከተፈረጁ የሙስሊም ወንድማማቾች ታጣቂ ቡድኖች ጋር ያለው ግንኙነት፣ ጦር ሰራዊቱን የእስራኤልና የአሜሪካ ጥቃት ኢላማ ውስጥ እንዳያስገባው ከፍተኛ ስጋት ደቅኖበታል። ይህንኑ ስጋት ለማርገብ አል-ቡርሀን በቅርቡ የእስላማዊ  ቡድን “አል-በራዕ ቢን ማሊክ” ብርጌድ አዛዥ የሆነውን ጀነራል አል-ናጂ አብዱላህን በቁጥጥር ስር አውሎታል። ይህ እርምጃ የተወሰደው ጀነራሉ ኢራንን ከአሜሪካና እስራኤል ወረራ ለመከላከል ተዋጊዎችን እልካለሁ ብሎ መዛታቸውን ተከትሎ ነበር። ይህም የአልቡርሃን አስተዳደር  ከአሸባሪነት ፍረጃና ከማዕቀብ ለማዳን የወሰደው ስልታዊ እርምጃ ተደርጎ እንደሚወሰድ የጂኦፓለቲካ ተንታኞች እየገለፁ ይገኛል። ተንታኞቹ እርምጃውን እንደ ስልታዊ ቢሉትም አልቡርሃን ለየመን ቱትሲዎች መሳሪያ ማቀባበያ እንደሆኑ ከተመዘገበባቸው ጉዳይ እንደሚያድናቸው እርግጠኞች አይደሉም።

በተጨባጭ  የሱዳን ጦር በካርቱም አካባቢ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ግስጋሴ ለመግታት የኢራኑን “ሞሃጀር-6” እና “አባቢል-3” ድሮኖችን እንደ ዋነኛ መሣሪያ እየተጠቀመ ይገኛል። እነዚህ ወታደራዊ ዱሮኖች በኤርትራ በኩል ገብተው ምጽዋ ካረፉ በኋላ በድብቅ ወደ ፖርት ሱዳን እንደሚገቡ የሳተላይት መረጃዎች ያሳያሉ። ይህ ሁኔታ ሱዳን በይፋ የምትከተለው የዲፕሎማሲ መስመርና በድብቅ የምታደርገው ወታደራዊ ትብብር ምን ያህል ታቅዶበት የሚሰራ ለመሆኑ ጉዳዩን የሚከታተሉ በተደጋጋሚ ሪፖርት አድርገዋል።

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኔይ መገደልና የቀጠናው ጦርነት መባባስ፣ አል-ቡርሀን እንደ ኢራን አጋር ተደርገው እንዳይፈረጁ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። ይህንን ፖለቲካዊ ኪሳራ ለመታደግ ሱዳን ፊቷን ወደ አረብ ሀገራት፣ በተለይም ወደ ሳዑዲ አረቢያ በማዞር አዲስ አማራጭ ለመፈለግ ሞክራለች።

በዚህም መሠረት በሳዑዲ አደራዳሪነት ከፓኪስታን ጋር የ1.5 ቢሊዮን ዶላር የጦር መሣሪያ፣ የJF-17 የጦር አውሮፕላኖች እና ድሮኖች ግዥ ስምምነት ብታደርግም፣ ሳዑዲ አረብያ አቋም መቀየር ሳቢያ ውሉ ከሽፏል። ሳዑዲ ቅርሚያ ለደህንነቷ እንደምትሰጥ በመግለፅ መሳሪያዎቹ ለአል ቡርሃን እንዳይሰውት ሆኗል። ተንታኞች እንደሚገልፁት ምንም እንኳ ሳኡዲ መሳሪያዎቹን የከለከለችው ለውስጥ ደህንነቷ ቅድሚያ በመስጠት በሚል ምክንያት ቢሆንም ዋነኛው ምክንያት በአሁኑ ሰአት የሳኡዲ የቅርብ ወታደራዊ አጋር የሆነቸው አሜሪካ የሱዳን ሙስሊም ወንድማማቾችን በይፋ በአሸባሪነት በመፈረጇ እንደሆነ ይታመናል።

የአልቡርሃን አስተዳደር የውስጥ ጠላቱን (ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን) ለማሸነፍ የኢራንን የጦር መሣሪያ በድብቅ እየተጠቀመ፣ በሌላ በኩል በሽብርተኝነት በመፈረጅ በአሜሪካ እና በአጋሮቿ የገልፍ ሃገራት በዲፕሎማሲ እንዳይገለል እና ሌሎች ወታደራዊ ድጋፎችን ላለማጣት ሲል እስላማዊ ጀነራሎቹን እስከ ማሰር ደርሷል። ይህ በጦር ሜዳ ፍላጎት እና በዲፕሎማሲያዊ ህልውና መካከል የሚደረግ የመንታ መንገድ ውጥረት የአልቡርሃንን አስተዳደር እጅግ ጠባብና አደገኛ በሆነ የገደል አፋፍ እንዲራመድ አድርጓታል። የዚህ ስልት ቀጣይነትም ሱዳን በቀጠናው ካላት የወደፊት እጣ ፈንታ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለውም ተመልክቷል።

ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰማው መረጃ ግን አልቡርሃንን እየዞረ ያለው የሽብርተኛነት ክስ ከከረረ ጎረቢታቸው ኤርትራ እና እዛው ገባ ወጣ የሚሉ፣ ወታደር ያዋጡና አብረው ቅንጅት ፈጥረው እየሰሩ ያሉት አካላትም ከጸበሉ ሊደርሳቸው እንደሚችል የሚጠቁሙ አሉ። የተጀመረ እንቅስቃሴ እንዳለ የሚናገሩ እንደሚሉት የቀጠናው የጂኦፖለቲካ ለውጥ ያስነሳው ማዕበል በቀላሉ የሚያልፍ አይመስልም።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

[ኦክቶፐሱ] ኢሳያስ አፈወርቂ እና ስውር እጆቻቸው፤ ኦክቶፐስ ስምንት፣ ኢሳያስ አምስት እግር ወይም እጅ አላቸው

ኢትዮጵያ በትልቅ እንግድነት ገብቶ ነበር። ትልልቅ የክብር መቀመጫዎች ተቀምጠዋል።...

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ – ዲጂታል “ኢህአፓ”

በሲንጋፑር ቆይታው ወቅትም የባዕድነትና የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማው በሚል ሰበብ...