ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ እንቅፋት ገጠመው፤ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያ አማራጭ ሆነ፤

Date:

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፤ ኢህአፓን ማገዝና ብረት ያንሱ ድርጅቶችን ስለመርዳት ምክክር ይደረጋል

አዲስ ሪፖርተር – ራሱን አክስሞ ሻዕቢያ ባደራጀውና አቶ ነዓምን በሚመሩት የአመጽ አመቻች ቴክኒክ ኮሚቴ ውስጥ ተካቶ የነበረው አብሮነት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ነበር። በስብሰባው ላይ ከአጀንዳ ውጭ የተነሳው ጉዳይ የስለሞን ቦጋለ ወደ ትውልድ አገሩ ኢትዮጵያ መመለሱና ይህንኑ ተከትሎ ፋኖ በሽብር ቡድን ደረጃ ሶስት መመደቡ ስላስከተለው ስጋት ነበር።

“የሰለሞን በሽብር ተጠርጥሮ ከአሜሪካ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ በዲያስፖራው ዘነድ ፍርሃቻ ነግሷል። ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጣ ሰው የለም፤ ባለን መረጃ ስጋቱ ከባድ ነው፤ ምን ታስቧል” በሚል ለቀረበው ጥያቄ አቶ ልደቱ ምላሽ ሳይሰጡ ዘለውታል።

ከአቶ ልደቱ አብሮነት ለቀው ወደ አቶ ነዓምን የአመጽ አመቻች ቴክኒክ ኮሚቴ ዝውውር ያደረጉት አቶ ያሬድ ለዚህ ተግባር ከተቋቋመው አንከር ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “አሁን ላይ በውጭ አገር ሰልፍ ቢደረግ ሰሚ የለም” በማለት ከሽብር ስጋት ይልቅ ጉዳዩን ዓለም ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር በማሳየት የተባለው ሰላማዊ ሰልፍ ፋይዳው እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ አመልክተዋል።

የህግ ባልሙያዎች “በአሜሪካ ህግ አላወኩም ነበር የሚል ነገር አይሰራም። ዜጎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል። ከሽብር ጋር በተያያዘ መሳተፍ፣ በሽብር ከተፈረጀ አካል ጋር አብሮ መስራት፣ ዓላማውን ማስተዋወቅ፣ በገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ወዘተ ያስቀጣል” በሚል በዚሁ ሚዲያ ተደጋጋሚ ምክር መለገሳቸው አይዘነጋም። እነዚሁ ነዋሪነታቸው አሜሪካ የሆነ የህግ ባለሙያዎቹ ምክራቸውን የለገሱት ለማስፈራራት ሳይሆን፣ ዜጎች ማናቸውንም ጉዳይ በእውቀት ላይ ተመስርተው እንዲያደርጉት ለማሳሰብ እንደሆነ በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል።

“አንተ ያለህበት አገር ሳይቀር ዓለም በዲክታተሮች እጅ ወድቃለች” በማለት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን አካተው የፈረጁት አቶ ያሬድ፣ በዚሁ ሳቢያ አገር ቤት ያለው ሕዝብ አመጽ እንዲያነሳ መስራቱ እንደሚሻል አመልክተዋል። ቀደም ሲል አለቃቸው አቶ ነዓምን ዘለቀም ተመሳሳይ ጥያቄና አስተያየት ተነስቶ “እኔም እርግጠኛ አይደለሁም። በብዙ ገፊ ምክንያቶች ሕዝብ አይወጣም” ማለታቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ይህንኑ አስመልክቶ የመጨርሻ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ሰኞ የአቶ ነዓምን ቡድን ስብሰባ መጥራቱ ታውቋል። በዚሁ ስብሰባ ላይ በሚወሰነው መሰረት ሶስት ሰዎች የፊታችን ሃሙስ መገለጫ እንዲሰጡ ይመረጣሉ።

በስብሰባው ላይ በአገር ቤት ከነዳጅ መጥፋት ጋር በተያያዝዘ የተከሰተውን እጥረትና የዋጋ ጭማሪ በመጠቀም ሕዝብ ለአመጽ እንዲነሳ ለማድረግ፣ ኢህአፓ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ስለመደገፍ፣ ከታጣቂ ኃይሎች ጋር አብሮ ስለመስራት ምክክር ይደረጋል።

በጋዜጣዊ መግለጫ ስለ ሽግግር መንግስት ትግበራ ማብራሪያ እንደሚሰጥ የጠቆሙት የአዲስ ሪፖርተር የመረጃ ምንጮች፣ ከጃልመሮ ወኪል አቶ ጅሬኛ በስተቀር ሌሎች የሚታወቁ የኦሮሞ ተወላጆች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ኮሚቴውን ጥለው መውጣታቸው ሁሉንም ግራ አጋብቷል። በተለምዶ “አጋር” የሚባሉ ክልል ተወላጆችም ከአቶ ነዓምን ዘለቀ ኮሚቴ ውስጥ መባረራቸው ቅሬታ ያስነሳ ጉዳይ ነው።

የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ በመባል የሚታወቀው ቡድን ያሰናበታቸው የአጋር ክልል ተወካዮች ያሰሙትን ቅሬታ ተከትሎ የተበተነው አብሮነት አስቸኳይስ ስብሰባ ማድረጉ ታውቋል።

አቶ ነዓምን የሚመሩት ቡድን እንዲጠቀልለው በተወሰነው መሰረት ሟሙቶ የነበረው አብሮነት አርብ ዕለት ድንገተኛ ስብሰባ ያደረገው አኩራፊዎችን ለማስታገስ እንደሆነ ስብሰባውን የተካፈሉ ለአዲስ ሪፖርተር ተናግረዋል። ስብሰባው ይህንን ቅሬታ ለማስተንፈስ በሚል እንደተዘጋጀ የገባቸው የአጋር ክልል ተወካዮች፣ አብሮነት በይፋም ባይሆን በተዘዋዋሪ ሚናውን ያጣ ማህበር እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ ነዓምን በሚመሩት ቡድን ውስጥ አብሮነት ምንም የመወሰን ሚና እንደሌለው በማንሳት ቅሬታ ያነሱት አባላቱ፣ ቀደም ሲል ትህነግ ያደርገው እንደነበር “አጋር” ተብለው መጠቀሚያ እንዲሆኑ እንጂ በትክክል ታምኖበት በእኩልነት እንዲሳተፉ አለመደረጉን ለአዲስ ሪፖርተር ተናግረዋል። ስብሰባው የተጠራውም እነሱን ሚናውን በተቀማ ድርጅት ስም ስብሰባ በመጥራት የመገፋት ስሜት እንዳይሰማቸው ለማድረግ በማሰብ እንደሆነ አስታውቀዋል። አክለውም “የሽግግር ሰነድ ሰልማዘጋጀትና፣ ይህንኑ የሚሰሩ አባላትን ምረጡ ይሉናል። አብሮነት የሽግግር መንግስት ሲያዘጋጅ እነሱም ነበሩ ለማለት ነው። ይግፉበት” በማለት በቅርቡ ይፋ በመውጣት ተቃውሟቸውን እንደሚያሰሙ አመልክተዋል።

ኢህአፓ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ጥሪው በእምነት ተቋማት መዋቅር ውስጥ እንዲሰራጭ ቀደም ሲል በተዘረጉ የግንኙነት አግባቦች እንዲከናወኑ እየተሰራ መሆኑን መስማታቸውን በአቶ ነዓምን የሚመራው ኮሚቴ ውስጥ ያሉ አመልክተዋል። እነዚሁ ወገኖች እንዳሉት ዝርዝር ባያብራሩትም የፋይናንስ ድጋፉም በዚሁ መዋቅር ስር እንዲያልፍ እንደሚደረግ አመልክተዋል።

እንዲህ ያለ መረጃ ቢኖርም፣ ኢህአፓ ይህንኑ የአመጽ ጥሪ በሚያስራጭበት ማህበራዊ ሚዲያ አውዶች ስር የሚሰነዘርበት ተቃውሞ እና ጠንካራ ምላሽ ከፍተኛ ነው። “ታላላቆቻችንን አስጨረሳችሁ፤ አሁን ደግሞ እኛን?” በሚል ድጋሚ የሚታለል እንደሌለ የሚገልጹት ይበዛሉ።

ኢህአፓ “ሁለገብ ትግል” በማለት የከተማ ውስጥ የትጥቅ ትግል መጀመሩን ተከትሎ ደርግ በጀመረው የቀይ ሽብር ዘመቻ በርካታ እናቶች ጧሪ አልባ መሆናቸውና፣ የኢትዮጵያን ሙሉ አንድ ትውልድ ያከሰረ እልቂት መደረሱ አይዘነጋም።

መስከረም 16 ቀን 1969 ዓ. የወቅቱ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበር (ኢሠማ) ምክትል ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ተመስገን ማዴቦን “ነጭ ሽብርን” አሃዱ ብሎ የጀመረው ኢህአፓ እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል። ግድያው የተፈጸመው አመራሩን የከፋፈለውን ኢህአፓ በከተማ የሽምቅ ውጊያ (Urban Guerrilla Warfare) ስልት “ነጭ ሽብር” በመባል የሚታወቀውን እርምጃ መጀመሩን ባወጀ ቅጽበት ነበር።

ይህ ግድያ ደርግ በኢህአፓ ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ እንዲያፋጥን እና በኋላም “ቀይ ሽብር” ተብሎ ለተጠራው ደም አፋሳሽ ዘመቻ እንደ አንዱ መነሻ ሆኖ አገልግሏል።

አቶ ተመስገን ላይ ግድያው በተፈጸመ በሳምንቱ መስከረም 23 ቀን 1969 ዓ.ም በጊዜያዊ ወታደራዊ ደርግ ሊቀመንበር በነበሩት በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ። ይህ ተደራራቢ ክስተት በሁለቱ ወገኖች መካከል የነበረውን ልዩነት ወደ መጨራረስ እንዳሸጋገረው በርካታ ጸሐፊዎች ምስክርነታቸውን ሰጠዋል።

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addm

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢህአፓ ሌላው የ “ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍ? “ከፈጣሪ የለም” ወደ የብሉይ ምሁር አመራር ሽግግር ሚስጢር

ሰራተኛ ሰፈር ዛሬ ፈርሷል እንጂ ምክር ነው። በየአንዳንዱ ቤት...

ፕሮፌሰር መሐመድ “ቀጣፊ ነው፤ የሚልኩብን እነሱ [ሻዕቢያዎቹ] ናቸው” ነዓምን

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ...

የአመጽ አደራጅ ቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱን አባረር፤ በግምገማ “የተጋበዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና ሚዲያዎች ሸሽተውናል” ተባለ

በዋሽንግቶን ዲሲ እና በሎንዶን ይካሄዳል የተባለው 'ምድር አንቀጥቅጥ' ሰላማዊ...

የሱኒ ሃገራት ዓለም ፤ በስሜትና በተጨባጭ እውነታ መካከል ያለው ልዩነት፤ የአህመዲን ጀበል የግሉ ጂኦ-ፖለቲካ

በዘመናዊው ጂኦ-ፖለቲካ ውስጥ ትክክለኛው ሃይል የሚለካው በቴክኖሎጂ ልዕልና፣ በኢኮኖሚ...