ምርጫ ቦርድ 30 በመቶ የሚሆነውን የመንግስት የመጀመሪያ ድጋፍ ልቀቀ፣ የአካል ጉዳተኞች የምርጫ ተሳትፎ ልዩ ድጋፍ

Date:

አዲስ ሪፖርተር – ቦርዱ ለተመዘገቡ እጩዎች እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ የእጣ አወጣጥ ሥነ ሥርዓቱን በዛሬው ዕለት እያካሄደ ይገኛል። የቦርዱ የህግ አማካሪ አይተነው ደበበ የእጩዎችና የፓርቲዎችን ስም፣ ምልክት እና ምስል በድምፅ የሚወሰንበት ሥርዓት መደንገግ የምርጫ ሂደቱ ግልፅ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሆነ ተናግረዋል።

የድምፅ መስጫ ወረቀት የእጩዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስም መለያ ምልክትና የእጩዎችን ምስል በመያዝ ታትሞ የተዘጋጀና መራጮች ለሚፈልጉት እጩ ድምፅ የሚሰጡበት ወረቀት መሆኑንም ገልጸዋል። በመድረኩ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉን ጨምሮ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን÷ ምርጫ ቦርድ እስካሁን የሰራቸውን ስራዎች አቅርቧል፡፡

የአካል ጉዳተኞች የምርጫ ተሳትፎ…

አካል ጉዳተኞች ከሌሎች የሕብረተሰብ ክፍሎች እኩል ተገቢው የዴሞክራሲ ተሳትፎና ውክልና እንዲኖራቸው በተለየ ሁኔታ ትኩረት ያሻቸዋል፡፡

ስለሆነም የእነዚህ የሕብረተሰብ ክፍሎች ሁኔታ በተገቢው ተጠንቶ የመራጮች ትምህርት እንዲያገኙ፣ በመራጭነት/ተመራጭነት እንዲመዘገቡ እና እንዲመርጡ የሚያስችል እቅድ ወጥቶ ይተገበራል፡፡

አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ኢትዮጵያ ያፀደቀችው ዓለም ዓቀፍ የአካል ጉዳተኞች ኮንቬንሽን፤ የአካል ጉዳተኞች በፖለቲካው መስክ በነፃነት በሚመርጧቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት በመምረጥና በመመረጥ ከሌሎች ጋር ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚኖርባት ይደነግጋል፡፡

በዚህ ረገድ:-
👉የምርጫ አሰራሮች፤
👉ቁሶችና ስፍራዎች ለአካል ጉዳተኞች ተስማሚ እንዲሆኑ፤
👉ድምጻቸውን በነፃነትና በምስጢር የሚሰጡበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
👉እርዳታ የሚሹ በሚመርጡት ሰው የመታገዝ መብት እንዲኖራቸው ፤
👉ተመርጠው በማናቸውም ደረጃ የማገልገል ዕድል እንዲኖራቸው ፤
👉አስፈላጊ የሆኑ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በአጠቃላይ የአካል ጉዳተኞች ያለአድልዎ ከሌሎች ጋር በእኩልነት በፖለቲካና እና በህዝብ አስተዳደር ጉዳዮች እንዲሳተፉ ማድረግና ማበረታታት ያለበት መሆኑ በኮንቬንሽኑ አንቀፅ 29 ሥር ተደንግጓል፡፡

የምርጫ አዋጅ ቁ. 1162/2011 መሠረትም በምርጫ ወቅት የኮንቬንሽኑ አንኳር ድንጋጌዎች ተፈፃሚ የሚሆኑበትን ሥርዓት ዘርግቷል፡፡

አዋጁ የአካል ጉዳተኞች የጉዳት ዓይነት በመራጮች መዝገብ ላይ እንዲገለፅ ከማድረግ አንስቶ ለዕጩነት ለመቅረብ የሚያስፈልገው የድጋፍ ፊርማ ብዛት ከሌሎች ዕጩዎች ያነሰ እንዲሆን ያዝዛል፡፡

እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ የሚያደርጉት ተሳትፎ ከፍ እንዲል እነርሱን በአባልነት፣ በዕጩነት እና በአመራርነት ለሚያሳትፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግበት የማበረታቻ ሥርዓት ዘርግቷል፡፡

ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter2
X፡ https://x.com/amejuju?s=21
https://web.facebook.com/addisreporternews
ስልክ ቁጥር፡ +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን ሲካሄድ የነበረው ድርድር ያለ ስምምነት ተበተነ

አዲስ ሪፓርተር— በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በፓኪስታን አስተናጋጅነት...

ሻዕቢያ ያደራጀው የአመጽ ቀስቃሽ ኮሚቴ እንቅፋት ገጠመው፤ ዲያስፖራው ስለፈራ አገር ቤት አመጽ ማስነሳት ቅድሚያ አማራጭ ሆነ፤

ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠራ፤ ኢህአፓን ማገዝና ብረት ያንሱ ድርጅቶችን...

ኢህአፓ ሌላው የ “ሞዐ ተዋሕዶ” ክንፍ? “ከፈጣሪ የለም” ወደ የብሉይ ምሁር አመራር ሽግግር ሚስጢር

ሰራተኛ ሰፈር ዛሬ ፈርሷል እንጂ ምክር ነው። በየአንዳንዱ ቤት...

ፕሮፌሰር መሐመድ “ቀጣፊ ነው፤ የሚልኩብን እነሱ [ሻዕቢያዎቹ] ናቸው” ነዓምን

አዲስ ሪፖርተር - በኢትዮጵያ ፖለቲካና የታሪክ ጥናት ውስጥ እጅግ...