የድሮን ቴክኖሎጂ ማምረቱን አጠናክሮ የቀጠለው ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ…

Date:

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጄነራል አቶ ሲሳይ ቶላ እንደገለጹት፤ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስከበር እንዲሁም ካለው የላቀ ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አንጻር የድሮን ቴክኖሎጂን በራስ አቅም ማልማት ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው። የኢትዮጵያን በኢኮኖሚው ዘርፍ የጀመረችውን ጉዞ ዘላቂ ለማድረግ ወታደራዊ አቅሟን መገንባትና በብቃት ማደራጀት እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው፡፡

ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የድሮን ቴክኖሎጂዎችን ማምረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተሩ እንዳስታወቁት                  ኢንዱስትሪው ማምረት የጀመራቸውን ድሮኖች ምርት በማስፋት የድሮን ቴክኖሎጂን በምርምርና ሥርጸት ለማሳደግና ተግባራዊ ተሞክሮን ለማዳበር ከተለያዩ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
 
ስምምነቱን የተፈራረመው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ከኢፌዴሪ አየር ኃይል፣ ከመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር መሆኑ ተመላክቷል በስነስርዓቱ ላይ ተመልክቷል። 
 
ምክትል ዳይሬክተር ጄነራሉ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስከበር እንዲሁም ካለው የላቀ ኢኮኖሚያዊና ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አንጻር የድሮን ቴክኖሎጂን በራስ አቅም ማልማት ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ነው፡፡ 
 
ይህን ከግምት በማስገባት ባለፈው ዓመት የካቲት ወር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ስራ የጀመረው ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንደስትሪ ለደኅንነት፣ ለመረጃ ስምሪት፣ ለሲቪልና ለወታደራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ድሮኖች ምርትን አጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
 
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ዩኒቨርሲቲው በዘርፉ በሚያደርጋቸው ምርምር እና ልማት እንዲሁም የሰው ኃይልን በማሰልጠን ከስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንደስትሪ ጋር በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንደስትሪ የሚመረቱ ድሮኖችን መጠቀም የሚችልበት ዕድሎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡
 
የሀገራችንን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዘርፉን በራስ አቅም በተገቢው መንገድ ለመጠቀም በትብብር ለመስራት አጋጣሚው ተፈጥሯል ያሉት ደግሞ የመከላከያ ኢንጂነሪግ ኢንደስትሪ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታቸው ሃይለማርያም ናቸው፡፡
 
የካቲት 29 ቀን 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተመርቆ ስራ የጀመረው ስካይዊን ኤሮኖቲክስ ኢንደስትሪ ለደኅንነት፣ ለመረጃ ስምሪት፣ ለሲቪልና ለወታደራዊ አገልግሎቶች የሚውሉ ድሮኖች ምርት ማምረቱን አጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተገለጸው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ለጸረ ሌብነት ዘመቻው ኢትዮጵያ ያቃታት ሶስተኛው መንገድ – “ድመቷ ጥቁር ትሁን ነጭ ዋናው ጉዳይ አይጥ መያዟ ነው”

በዓለማችን የሙስና መመዘኛ መሠረት በጣም ዝቅተኛ ሙስና ይካሄድባቸዋል ተብለው...

እውነት እኛ “ጋዜጠኞች” ነን? የገፈፍነው የሕዝብ ዳኝነት … !!

የ “ጋዜጠኝነት” ስም የሚሰጠው ለሚታወቅ ስራና “ሙያተኛ ” ብቻ...

የትህነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብርሃም ተከስተ ቤተሰቦቻቸው በአሜሪካ ጥገኝነት እንዲያገኙ አመልከቱ

በምህረት ከእስር የተፈቱት የትህነግ ከፍተኛ አመራር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካን...

ጻድቃን ታደሰ ወረደን ከሰሱ፤ “ሻዕቢያ ትግራይን የጦር አውድማ ለማድረግ ተስማምቷል”

ትግራይን እንዲመሩ በፌደራሉ መንግስት የተሰየሙት የቀደሞው ሌተናል ጄነራል ታደሰ...
Shares