የፌደራሉ መንግስት ለክልሎች የሚመደበው የበጀት መጠን ክልሎች በሚሰበስቡት ግብር ልክ እንዲኾን ግዴታ ሊጣልባቸው ነው

Date:

ክልሎች የፌደራል መንግስት በተመነው ልክ ግብር ካልሰበሰቡ ባለስልጣናቱ እስከማባረር የሚያደርስ ውሳኔ ይጠብቃቸዋል

አዲስ ሪፖርተር – የፌደራል መንግስት ለክልሎች የሚመድበው በጀት ክልሎች በሚሰበስቡት ሊወሰን መኾኑን የተገለፀ ሲኾን ከአቅማቸው በታች ግብር የሚሰበስቡ ክልሎች በዝያው ልክ ዝቅተኛ በጀት የሚመደብላቸው መሆኑን የፌደሬሽን ምክርቤት አስታውቋል።

ከፌደሬሽን ምክርቤት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው የፌደራል መንግስት ለክልሎች ሲያደርገው የነበረውን የበጀት አመዳደብ ተመን ለመቀየር መታሰቡንና ክልሎች የሚሰበስቡት የግብር መጠን ዝቅተኛ እየሆነ በመምጣቱ መሆኑን ይገልፃል።

በተለይም አንዳንድ ክልሎች ከፍተኛ ገቢ የመሰብሰብ እድል ቢኖራቸውም እየሰበሰቡት ያለው የግብር መጠን ከሌሎች ክልሎች አንፃር ዝቅተኛ ሆኖ መመዝገቡ የበጀት አያያዝ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እየፈጠረ ነው የሚል አመክንዮ እንደቀረበበት መረጃው ያመለክታል።

የፌደሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እንደተናገሩት ከሆነም ካሁን በኃላ ገቢ የመሰብሰብ አቅማቸው ምን ያህል ነው የሚለውን ደግሞ በጀት መዳቢ መስርያ ቤት በሁሉም ክልሎች ላይ ጥናት የሚያደርግ ግብረኃይል መቋቋም እንደታሰበና የክልሎች አቅም ለመለካት ውጥን መያዙን ገልፀዋል።

አፈጉባኤ አገኘሁ የተገመተለትን በጀት የመሰብሰብ አቅም ልክ የማይሰበሰብ ክልል ያለ እንደሆነ ክልሎቹና የስራ ሐላፊዎቹ የሚጠየቁበት እንዲሁም ከሓላፊነት እስከ መነሳት የሚደርስ ውሳኔ ሊተላለፍባቸው እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋል።

በተያያዘ መረጃ በቅርቡ የአለማቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ይፋ ባደረገው አንድ ጥናት እንደገለፀው ከሆነም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ካሉ አገራት ዝቅተኛ ገቢ የመሰብሰብ አፈፃፀም ያላት አገር መኾንዋን ጠቅሶ ለዚህም እንደምክንያት ያነሳው መንግስታዊ መዋቅሩ ልል በመሆኑ ነው ብሏል።

ድርጅቱ አክሎም፣ የጸጥታ ጉዳይ ካስከተለው ጫና ባሻገር፣ በአገሪቱ የሚስተዋለው ሕገወጥ ንግድን ጨምሮ የመንግስት ባለስልጣናት የሚሳተፉበት ኮንትሮባንድ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲሁም የተበታተነ የኢኮኖሚ መዋቅር ዝቅተኛ ገቢ እንዲሰበሰብ ያቻሉ ምክንያቶች ናቸው።

በዚህ የተነሳም ኢትዮጵያ ከአለማቀፍ የገንዘብ ድርጅት የተበደረችው ብድር አከፋፈል ላይ አሉታዊ ጫና ሊያስከትል እንደሚችል በሪፖርት ማመልከቱ አይዘነጋም።

ድርጅቱ ይኽንን ይበል እንጂ፣ በመንግስት የውፓለቲካ መዋቅሩ እንደሚባለው ሳይሆን ካለፉት ዓመታት አንፃር ሲታይ የተስተካከለና የተሻሻለ የለውጥ ሂደት ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ የተቋሙን ግምገማ ሙሉ በሙሉ እንደማይቀበለው አስታውቆ ነበር።

የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ፕሬዝዳንት ታየ አፅቀ ስላሴ በቀጣይነት ብሔራዊ ምርጫ ለማድረግ በቂ ዝግጅት እየተደረገ እንዳለና ከተለያዩ ወገኖች በኩል የሚነሳው ወቀሳ በቂ ትንተና የጎደለው መኾኑን በህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት አዲሱን የስራ ዘመን የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ አስታውቀዋል።

የዓለም ባንክ እአአ ጥቅምት 8 ቀን 2025 ባወጣው አዲስ ሪፖርት ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ኮትዲቯር የላቀ የኢኮኖሚ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ ግምቱን አስቀምጧል። ኢትዮጵያም ከወድሞ የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ክምችት እንዳላት ገልጿል።

ባንኩ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ በሚታተመው አፍሪካስ ፐልስ (Africa’s Pulse) ላይ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ላይ ይፋ እንዳደረሰው የተጠቀሱት ሦስቱ አገራት ፈጣን ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ ይገልጻል። ኢትዮጵያን ጨምሮ አገራቱ በያዝነው ዓመትና በሚቀጥለው ዓመት ፈጣን የኢኮኖሚ በሚያስመዘገብ ጎዳና ላይ እንዳሉ የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ ለመላው ከሰሃራ በታች አፍሪካ (SSA) ክልል ያለው ዕድገት በ2025 3.8 በመቶ እንደሚደርስ ይተነብያል።

ይኸው ተገማች ዕድገት የዋጋ ግሽበትን ለማቃለል እንደሚረዳ ሪፖርቱ ጠቅሷል። ለምሳሌ በኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪን ለማረጋጋት፣ ዋጋን ለመቆጣጠር እና የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ የተወሰዱት እርምጃዎች የወለድ ምጣኔን ለመቀነስ የሚያስችሉ መሆናቸውን አመልክቷል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ መርዶና ብስራት የሚያቀርበው የዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋምም ሆኑ አገር ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች መንግስት ግብር መሰብሰብ ላይ ደካማ መሆኑን፣ በተለይም የክልል መንግስታት የበጀት ድጎማ ሰፊ ነቀፌታ ሲሰነዘርበት የነበረና አሰራሩ የፌደራል መንግስትን ወጪ የሚያንር እንደሆነ ሲገለጽ ረዥም ጊዜ አስቆጥሯል።

ክልል የመሆን ጥያቄዎች በአብዛኛው መነሻው ፖለቲካዊ ሳይሆን ሰፊ በጀት በማስመደብ ከሌብነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ሲናገሩ የነበሩ ቢዘገይም ውሳኔው አግባብ እንደሆነ አመልክተዋል። አዲስ ሪፖርተር ያናገራቸው የፓርላማ አባል፣ ውሳኔው ወደፊት ክልል ለመሆንና በጀት ለመዝረፍ ለሚቧደኑ መርዶ እንደሚሆንባቸው አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የክልልነት ጥያቄ ፖለቲካዊ ሳይሆን ንግድ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚናገሩ ይህን መሰሉ አሰራር ቀደም ብሎ ቢተገበር ኖሮ የተበጣተሰው የደቡብ ክልል እዚህ ደረጃ ባልደረሰ ነበር ብለዋል።

የፌደሬሽን ምክርቤት የበጀት አመዳደብ እና የግብር አሰባሰብ ዙርያ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነም ክልሎች የግብር አሰባሰብ ስርዓታቸውን እንዲያዘምኑና በተገመተላቸውና የሚጠበቅባቸውን ያህል ግብር እንዲሰበስቡ የተጣለባቸው ሐላፊነት እንዳለ ይገልፃል። በአንፃሩመንግስት በክልሎች ላይ የሚጥለው አስገዳጅ ውሳኔ አላስፈላጊ ዋጋ እንዳያስከፍል እና የግብር ጫናዎች መደራረብ ሕብረተሰቡ ላይ አሉታዊ ጫና እንዳያሳድር ከፍተኛ ስጋት መኖሩን እየተገለፀ ይገኛል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ለጸረ ሌብነት ዘመቻው ኢትዮጵያ ያቃታት ሶስተኛው መንገድ – “ድመቷ ጥቁር ትሁን ነጭ ዋናው ጉዳይ አይጥ መያዟ ነው”

በዓለማችን የሙስና መመዘኛ መሠረት በጣም ዝቅተኛ ሙስና ይካሄድባቸዋል ተብለው...

እውነት እኛ “ጋዜጠኞች” ነን? የገፈፍነው የሕዝብ ዳኝነት … !!

የ “ጋዜጠኝነት” ስም የሚሰጠው ለሚታወቅ ስራና “ሙያተኛ ” ብቻ...

የትህነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብርሃም ተከስተ ቤተሰቦቻቸው በአሜሪካ ጥገኝነት እንዲያገኙ አመልከቱ

በምህረት ከእስር የተፈቱት የትህነግ ከፍተኛ አመራር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካን...

ጻድቃን ታደሰ ወረደን ከሰሱ፤ “ሻዕቢያ ትግራይን የጦር አውድማ ለማድረግ ተስማምቷል”

ትግራይን እንዲመሩ በፌደራሉ መንግስት የተሰየሙት የቀደሞው ሌተናል ጄነራል ታደሰ...
Shares