በአፋር የመሬት መንቀጥቀጥ በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

Date:

በአፋር ክልል ሰሜናዊ ዞን በባራሕሌ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ።የመሬት መንቀጥቀጡ በሰዎች ላይ ሞትና የአካል ጉዳት ሲያከትል፣ በንብረት ላይ ከባድ የተባለ ውድመት ማድረሱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አሊ ሁሴን ናቸው ያስታወቁት።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አሊ ሁሴን በመሬት መንቀጥቀጡ የ12 ዓመት ዕድሜ ታዳጊ ህይወቱ ሲያልፍ፣ 6 ሰዎች ላይ ጉዳት ደውርሶባቸዋል። በቡሬ እና ዓስጉቢ ቀበሌዎች በርካታ ቤቶች መፍረሳቸውን ሲያታውቁ እንዳሉት በመሬት መንቀጥቀጡ 43 ሺህ 456 የሚሆኑ ሰዎች ቤቶቻቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን እና ያለመጠለያ መቅረታቸውን ጠቁመዋል። ለተጎጂዎች ድጋፍ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ዋና አስተዳዳሪው ጉዳቱ እንደደረሰ አስታውቀዋል።

በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ ዞን በራሕሌ ወረዳ የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ያስከተለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት እንዲሁም የክልሉ መንግሥት አፋጣኝ እርዳታ እያካሄደ መሆኑን የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ባሰራጨው መግለጫ አስታውቋል።

​ኮሚሽኑ ጥቅምት 02 ቀን 2018 ዓ.ም “በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ ዞን በራሕሌ ወረዳ የተከሰተው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ያስከተለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት እንዲሁም የክልሉ መንግሥት እሰጠ ያለው አፋጣኝ ምላሽ” በሚል መነሻ ይፋ ባደረገው መግለጫው የሚከተለውን ብሏል።

​የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ፣ በኪልበቲ ረሱ ዞን በራሕሌ፣ ኮናባ እና ዳሎል ወረዳዎች በትላንትናው ምሽት ጥቅምት 01 ቀን 2018 የተከሰተውን ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከትሎ የክልሉን ጥልቅ ሐዘን ይገልጻል። ይህ አደጋ፣ በተፈጥሯዊ የጂኦሎጂ አቀማመጥ ምክንያት በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ለሚያጋጥመው የክልሉ ክፍል አዲስ እና ከባድ ፈተና ሆኗል።

​በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በተለይም በበራሕሌ ወረዳ በሚገኙት ቡሬ እና አስ ጉቢ አላ ቀበሌዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። አንድ (1) የ12 ዓመት ህጻን ሕይወት ሲያልፍ፣ ስድስት (6) ዜጎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል። ሁሉም ተጎጂዎች በአፋጣኝ ወደ ጤና ጣቢያ ተወስደው አስፈላጊውን የሕክምና አገልግሎት እያገኙ ይገኛሉ።

የመጠለያ እጦትና መፈናቀል አመልክቶ በቡሬ እና አስ ጉቢ አላ ቀበሌዎች ብቻ 43,456 (አርባ ሦስት ሺህ አራት መቶ ሃምሳ ስድስት) ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተፈናቅለው ለድንገተኛ መጠለያ እና ሌሎች ድጋፎች አስቸኳይ ፍላጎት አጋጥሟቸዋል።

የንብረት ውድመትን በተመለከተ ​በርካታ የመኖሪያ ቤቶች እና የመንግሥት መዋቅሮች ሙሉ በሙሉ በመፍረሳቸው ከፍተኛ የሆነ የንብረት ውድመት ደርሷል።

​የአደጋው የጂኦሎጂያዊ ዳራ አስመልክቶ የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተበት የኪልበቲ ረሱ ዞን አካባቢ በተፈጥሮ የምስራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ (East African Rift Valley) ወሳኝ አካል በመሆኑ፣ ለጂኦሎጂያዊ እንቅስቃሴዎች እና ለርዕደ መሬት ተደጋጋሚነት ተጋላጭ መሆኑ ይታወቃል።

​የክልሉ መንግሥት እሰጠ ያለው አፋጣኝ ምላሽ

​የአፋር ክልላዊ መንግሥት የተከሰተውን ከባድ አደጋ ተከትሎ በአፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እና ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለመደገፍ ሙሉ አቅሙን አሰባስቧል።

• ​አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታ፡ ለተፈናቀሉ ዜጎች አስቸኳይ ምግብ፣ ጊዜያዊ መጠለያ እና አስፈላጊ የጤና አገልግሎቶች እንዲደርሱ የማድረግ ሥራ በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ ነው። ለቆሰሉ ዜጎችም የተሟላ የሕክምና አገልግሎት በፍጥነት እንዲያገኙ ተደርጓል።

• ​የጉዳት ግምገማ እና የመልሶ ግንባታ ዕቅድ፡ የአደጋውን አጠቃላይ ስፋት እና የጉዳት መጠን በሳይንሳዊ መንገድ ለመገምገም የሚያስችል ባለሙያዎች ቡድን በቦታው ይገኛል። ግምገማው ሲጠናቀቅ ለተጎጂዎች ዘላቂ የመቋቋሚያና የመልሶ ግንባታ ዕቅድ ይፋ ይደረጋል።

​የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በድጋሚ እየገለጸ፣ የክልሉን ነዋሪዎች፣ ሀገር አቀፍ ተቋማትን፣ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶችን እና ዓለም አቀፍ አጋሮችን ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ በአክብሮት ጥሪ ያቀርባል።

​የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሰመራ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ለጸረ ሌብነት ዘመቻው ኢትዮጵያ ያቃታት ሶስተኛው መንገድ – “ድመቷ ጥቁር ትሁን ነጭ ዋናው ጉዳይ አይጥ መያዟ ነው”

በዓለማችን የሙስና መመዘኛ መሠረት በጣም ዝቅተኛ ሙስና ይካሄድባቸዋል ተብለው...

እውነት እኛ “ጋዜጠኞች” ነን? የገፈፍነው የሕዝብ ዳኝነት … !!

የ “ጋዜጠኝነት” ስም የሚሰጠው ለሚታወቅ ስራና “ሙያተኛ ” ብቻ...

የትህነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብርሃም ተከስተ ቤተሰቦቻቸው በአሜሪካ ጥገኝነት እንዲያገኙ አመልከቱ

በምህረት ከእስር የተፈቱት የትህነግ ከፍተኛ አመራር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካን...

ጻድቃን ታደሰ ወረደን ከሰሱ፤ “ሻዕቢያ ትግራይን የጦር አውድማ ለማድረግ ተስማምቷል”

ትግራይን እንዲመሩ በፌደራሉ መንግስት የተሰየሙት የቀደሞው ሌተናል ጄነራል ታደሰ...
Shares