ጻድቃን ታደሰ ወረደን ከሰሱ፤ “ሻዕቢያ ትግራይን የጦር አውድማ ለማድረግ ተስማምቷል”

Date:

ትግራይን እንዲመሩ በፌደራሉ መንግስት የተሰየሙት የቀደሞው ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ አቋም አነጋጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል። ትህነግ ባዘጋጀው ኮንፍረስን ላይ መንግስትን ለመጣል በቂ ትጥቅና ኃይል እንዲሁም አጋዦች እንዳሉ ባስታወቁ ማግስት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጎን የታዩት ታደሰ ወረደን የከሰሷቸው ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ናቸው። ክሱም በተጨባጭ ዝርዝር የተደገፈና በትግራይ ለውጥ ለማምጣት የተቀናጁት ክፍሎች እሳቸው ከሃላፊነት እንዲነሱ ቅድመ ሁኔታ ማስቅመጣቸው የሚጠይቁት ጥያቄ መሆኑንም አመልክተዋል።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትግራይን እንዲመራ የተቋቋመውንና በአቶ ጌታቸው ረዳ ይመራ የነበረውን ጊዜያዊ አስተዳደር ከማገዝ ይልቅ፣ ሌተናል ጄኔራል ታደሰ የክልሉ የጸጥታ ኃላፊነታቸውን ተገን በማድረግ ክህደት መፈጸማቸውን ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ አስታውቀዋል።

ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሰፊ ቃለ መጠየቅ የሰጡ ሌ/ጄነራል ፃድቃን፣ ዝርዝር ባይሆንም ኢትዮጵያ ድጋሚ አሰብን የመውሰድና የኢትዮጵያን ታሪካዊ ጠላት ሻዕቢያን ለማስወገድ መልካም አጋጣሚ የነበርበት ወቅት ላይ ኢትዮጵያን ይመሩ የነበሩት አቶ መለስን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት አጋጣሚውን ለመጠቀም የቀረበውን አሳብ ውድቅ ማድረጋቸውን አስታወቅዋል። ከአቶ ተፈራ ዋልዋ በስተቀር ሁሉም በሚባል ደረጃ የኢሳያስ ደጋፊ እንደነበሩ በቁጭት ሲያብራሩ ነው ታደሰ ወረደ እያሉ በትግራይ ለወጥ ለማምጣት እንደሚያስቸግር አቋም መያዙን የተናገሩት።

ጊዜያዊ አስተዳደሩን በሴራና በትጥቅ ያፈረሱት የዛሬው የትግራይ መሪ መነሳት እንዳለባቸው የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ሶስት ታዋቂ ግለሰቦች ያካተተው ጥምረት ወይም ካውንስል እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡን ያስታወቁት ሌ/ጄነራል ፃድቃን፣ የፌደራል መንግስት እንዴት ከታደሰው ወረደ ጋር እንደሚሰራ ግራ እንደሚገባቸውም አመልክተዋል። መንግስት ከሳቸው ጋር አብሮ ለመስራት ምን ምክንያት እንዳለው የሚያውቀውም ራሱ የፌደራል መንግስቱ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ጄነራሉ በሰጡት ሰፊ ቃለ ምልልስ፣ “ የትግራይ ህዝብ ከሻዕቢያ መንግስት ጋር የሚደረግ ትብብር/ፅምዶ አልፈልግም ነው ያለው “ በሚል አሁን ላይ ስላለው አዲስ የፖለቲካ ሽርጉድ አስታውቀዋል።

ትግራይ የሚገኙት የትህነግ አመራሮች ከሻዕቢያ (ከኢሳያስ መንግሥት ጋር) ሽርክና በመፍጠር ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰሩ እንደሆነ ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ሲያስታውቁ ከፋኖ ጋር ጭምር ጥምረት ተፈጥሮ አገር የማተራመስ ስራ እየተሰራ ነው በማለት ነው።

ሌ/ጄነራል ፃድቃን ፤ የትህነግ ሰዎች ከኢሳያስ መንግስት ጋር በማበር ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰሩ ያሉት የወንጀል ስራዎቻቸውን ለመሸፈን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል። አክለውም “ የወንጀል ስራዎች እና ወደ ጦርነት የተገባበት ውሳኔ እራሱ (የቀድሞው ጦርነት) የaccountable ጥያቄ አለበት “ ብለዋል።

ሌ/ጄነራሉ ፥ እጅግ በጣም ብዙ የጠፉ ፣ የተሰረቁ ፣ የተዘረፉ ንብረቶች፣ ወርቅ፣ መሬት ፣ ገንዘብ እንዳለ ጠቁመዋል። በዚህ የወንጀል ተግባር ውስጥ በግልጽ የሚታወቁ ትላልቅ አመራሮች እንዳሉበት በስፋት ዘርዝረዋል። ክልሉ ሰላም እንዳያገኝ የሚፈለገውም ለርዚሁ ተግባር መሆኑን አመልክተዋል።

እነዚህ አካላት የወንጀል ስራዎቻቸውና የፖለቲካ ስልጣን ፍላጎታቸው አንድ ላይ እንደተቀላቀሉ ፤ ይህን ለመከላከል ወይም ከሰሯቸው የወንጀል ስራዎች ነጻ ለመሆን የሚያስችላቸው አንዱ መንገድ ጦርነት መፍጠር እንደሆነ እንደሚያምኑ አመልክተዋል። ለዚህም “ ከኢሳያስ መንግሥት ጋር መተባበር ነው – ፅምዶ “ ብለው እየሰሩበት እንደሆነ ገልጸዋል።

“ የትግራይ ህዝብ እያንዳንዱ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አውቆባቸዋል “ ያሉት ሌ/ጄነራሉ ፤ የትግራይ ጄኖሳይድ ኮሚሽን ባጠናው ጥናት በትግራይ ጦርነት ወቅት 75% የሚሆነውን የግፍና የወንጀል ስራዎችን የሰራው የኤርትራ ሰራዊት እንደሆነ መመላከቱን ተናግረዋል። ይህ ተዘነግቶ ዳግም ከሻዕቢያ ጋር ጥምረት መፈጠሩ በትግራይ ሕዝብ ታሪክ ትልቁ ክህደት እንደሆነም አመልክተዋል።

  • “ሰው የገደለው፣ ሴቶች የደፈረው፣ ሴቶች ማዕፀን ላይ ያልሆነ ነገር ያስገባው የኤርትራ ሰራዊት ነው፤ ይህ በማስረጃ የተደገፈ ነው” ያሉት ጻድቃን፣ “ የአክሱም ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ የማህበረ ደጎ ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ የማርያም ደንገላት ነፍሰ ገዳይ የሻዕቢያ ወታደር ነው ፤ ደቡብ ትግራይ ራያ ላይ መጥቶ በመቶዎች የሚሆኑ ሰዎችን ረሽኖ የሄደው የሻዕቢያ ወታደር ነው “ ሲሉ ከብዙ በጥቂቱ የፕሬዚዳንት ኢሳያስ መንግስት የፈጸመውን ወንጀልና ግፍ ዘርዝረዋል።

“ህዝቡ ይሄንና የወታደራዊ እና የፖለቲካ መሪዎቹን ፍላጎት እንዲሁም የሚያደርጉትን ግንኙነት ስለሚያውቅ ከሻዕቢያ ጋር የሚደረግ ትብብር /ፅምዶ አልፈልግም ነው ያለው” ሲሉ በተለያዩ መድረኮች ላይ በግልጽ የተሰጡ አስተያየቶችን ባምስታወስ ጻድቃን ተናግረዋል። አክለውም “ከእነሱ ጋር በወንጀል የተሳሰረው ካልሆነ በስተቀር ህዝቡ ከኢሳያስ መንግሥት ጋር መተባበር ጥፋት እንደሚያመጣ አምኖ አልተቀበለውም” በማለት ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እነዚህ ጦርነት እንዲነሳ የሚፈልጉ እና እየሰሩ ያሉ አካላት በኤርትራና በሱዳን በኩል ጥይት፣ ጠመንጃ እንደሚያስገቡ ገልጸዋል። ትህነግ የጦር መሳሪያም እየሸመተ እንደሆነና ይህንንም ጠንቀቀው እንደሚያውቅ ሌ/ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ ተናግረዋል።

“በማንኛውም ጊዜ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል” ሲሉ አፍሪካ ሪፖርት በተሰኘ መጽሔት ባሰፈሩት ጽሁፍ ትንታኔ ምስጠታቸው አይዘነጋም። ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ ከሁለቱ አገሮች አልፎ ሱዳንንና የቀይ ባህር አከባቢዎችን ሊያጠቃልል ይችላል ያሉት ጄኔራሉ “ትግራይ ከእንዲህ አይነት ግጭት እርቃ ሰላምን ማስፈን ትመርጣለች” ብለውም ነበር።

በዚሁ በማርች 2025 ጽሁፋቸው በርካታ ስጋትና መላምታቸውን ካስቀመጡ በኋላ ኤርትራ “ጠብ አጫሪ ሀገር ነች” ብለዋል። አክለውም በዙሪያዋ ያሉትን አገሮች በተለይም በኢትዮጵያን እና በሱዳን ያለውን አሁናዊ ሁኔታ ለመጠቀም እየሞከረች ነው ሲሉ ክስ አሰምተዋል።

አክለውም ኤርትራ ትግራይን ለምኞቶቿ አለመሳካት “ዋነኛ እንቅፋት” አድርጋ እንደምትመለከታት የጠቆሙት ጄነራሉ፣ ኢሳያስ በትግራይ ላይ ማሳካት የፈለጉተን ሳያሳኩ በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ጦርነቱ መቆሙን ተከትሎ “ተኮሊፍና” በማለት ቁጣቸውንና ቁጭታቸውን ማስተጋባታቸውን አስታውሰዋል። እናም በስምምነቱ መነሻነት ያልተሳካላቸውን ምኞታቸውን ለማሳካት ሌላ ጦርነት ለመጀመርና ዕቅዳቸውን ለማሳካት ዝግጅታቸውን እንዳጠናቀቁ አስጠንቅቀዋል።

አስተያየት ሰጪዎች ትግራይ በዳግም ጦርነት ከወደመች ኢሳያስ በቅጽበት ለሰላም እጃቸውን እንደሚሰጡ ደጋግመው ገልጸዋል። መረጃ አለን የሚሉ አሁን ላይ በትግራይ ያለው የሕዝብ የሰላም ፍላጎት ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከፍተኛ ስጋት እንደሆነባቸውም እየገለጹ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ለጸረ ሌብነት ዘመቻው ኢትዮጵያ ያቃታት ሶስተኛው መንገድ – “ድመቷ ጥቁር ትሁን ነጭ ዋናው ጉዳይ አይጥ መያዟ ነው”

በዓለማችን የሙስና መመዘኛ መሠረት በጣም ዝቅተኛ ሙስና ይካሄድባቸዋል ተብለው...

እውነት እኛ “ጋዜጠኞች” ነን? የገፈፍነው የሕዝብ ዳኝነት … !!

የ “ጋዜጠኝነት” ስም የሚሰጠው ለሚታወቅ ስራና “ሙያተኛ ” ብቻ...

የትህነግ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶክተር አብርሃም ተከስተ ቤተሰቦቻቸው በአሜሪካ ጥገኝነት እንዲያገኙ አመልከቱ

በምህረት ከእስር የተፈቱት የትህነግ ከፍተኛ አመራር አብርሃም ተከስተ በአሜሪካን...

የትግራይ ሰላማዊ ሰልፎችና የታደሰ ወረደ ዕጣ ፈንታ እያነጋገረ ነው፤ “ሰላም እንሻለን” ታጣቂዎች

በትግራይ ለፓለቲካ ጥቅም ሲባል ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም...
Shares