አምባሳደር ቲቦር ናጂ ኢሳያስ አፈወርቂ ኤርትራን ለቀው ይኮበልላሉ አሉ፤ ካልኮበለሉ የጋዳፊ ዕጣ ይጠብቃቸዋል 

Date:

የቀድሞው የአሜሪካ ዲፕሎማትና የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት አምባሳደር ቲቦር ናጂ፣ በአስመራው አምባገነን መንግሥት መሪ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ መጨረሻቸውን አስመልክቶ አነጋጋሪ ፍንጭ ሰጥተዋል። 

አምባሳደሩ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሲያከትምላቸው እንደ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ከመሳሰሉት የቀድሞ አምባገነኖች ተርታ የሚዘከር ታሪክ እንጂ ሌላ ዕድል እንደሌላቸው ያስታወቁት በግል ኤክስ ገጻቸው ሲያበቃላቸው ፈርጥጠው ከአገር ይኮበልላሉ ብለዋል። አምባሳደሩ ይህን ይህን ያሉት በግል የኤክስ ገጻቸው ሲሆን፣ ዝርዝር ጉዳዮችን ከ”ብርጌድ ንሓመዱ” ጋር መወያየታቸውን ጠቁመዋል። የ”ብርጌድ ንሓመዱ” አባልም በተነጋገሩባቸው ጉዳዮችና ድርጅቱ በአሜሪካ እያካሄደ ያለውን የዲፕሎአማሲ ትግል አካቶ በአቶ ዳዊት አማካይነት መረጃ አካፍሏል። 

በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ውጥረት ከመባባሱ ጋር ተያይዞ የመጨረሻው ውጤት ምን እንደሚሆን ሲናገሩ፣ ጦርነት ከተነሳ ሁለት ዋና ውጤቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። ዳዊት እንዳሉት በሁለት መልኩ የቀረበው ትንተና ኢትዮጵያ የአሰብን ወደብ መቆጣጠሯና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሥልጣን መወገድ  ናቸው።

የአምባሳደር ቲቦርናጄ መልዕክት ዝም ብሎ የሚነገር፣ ወይም ከተራ ዲፕሎማት እንደሚሰማ የግል አስተያየት ዓይነት ተደርጎ እንደማይወሰድ በርካቶች አስተያየት ሰጥተዋል። በተለይም አሁን ላይ አሜሪካ ቀይ ባህር ላይ ለመስፈር ከሶማሊ ላንድ ጋር ከጀመረችው ንግግር አንጻር አንጻር የአምባሳደሩ ንግግር ከብደት እንዳለው የተናገሩም አሉ።

በ አሜሪካ ምን እየሰራች እንደሆነ አመልካች ተደርጎ ተወስዷል። የአምብሳደሩ ንግግር የአሜሪካና ኤርትራ ግንኙነት በመሻሻል ላይ ነው በሚል በግልና በቡድን በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲያስተጋቡ ለነበሩ አፍቃሪ ኢሳያስ እና ለራሱ ለኤርትራ መንግስት ሹማምንት አስደንጋጭ እንደሆነባቸው ከተለያዩ አካላት እየተሰማ ነው።

የአምባገነኖች ዕጣ ፈንታ፡ ታሪካዊ ንጽጽር አምባሳደር ናጂ በኤርትራ መንግሥት መጨረሻ ኩብለላ ወይም እንደ ጋዳፊ መሆኑን ከመጠቆማቸው ጎን ለጎን የሻዕቢያን አገዛዝ በመቃወም ትግል ከጀመሩ የተቃዋሚ ቡድኖች አመራሮች ጋር ያላቸው ግንኙነት ማደጉን መግለሳቸው የሰጡትን ጥቆማ አጠንክሮታል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በአሜሪካ የኤርትራ ሰማያዊ አብዮት ግንባር (EBRF) አመራር ጋር መወያየታቸውን በይፋ አምባሳደሩ አስታውቀዋል። ይህ ግንባር ብርጌድ ንሓመዱ በመባል የሚታወቀውን ተፅዕኖ ፈጣሪ የወጣቶች እንቅስቃሴን ያካተተ ሲሆን፣ ግንባሩ በኢትዮጵያም

አደረጃጀቱብ አስፍቶ በኢሳያስ አፉወርቂ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ ለማካሄድ ከቀይ ባህር አፋር ጋር በጋራ ሰመራ ከተማ ስብሰባ ማድረጉ አይዘነጋም። አምባሳደሩ ከተጠቀሱት አካላት ጋር ከተወያዩ በኋላ በኤክስ ገጻቸው እነዚህኑ የሻዕቢያ አገዛዝ የሚቃወሙ አካላትን በማግኘታቸው የተሰማቸውንም ኩራት በይፋ አስታውቀዋል። የኤርትራው የተቃውሞ እንቅስቃሴ “ብርጌድ ንሓመዱ” በአዲስ አበባ ቢሮ መክፈቱንንና ቢሮው “በቀጣይ ወታደራዊ ማዕከሎች ሲቋቋሙ፤ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት” ሆኖ እንደሚያገለግል ማስታወቁ አይዘነጋም። 

የተቃውሞ እንቅስቃሴው በኢትዮጵያ “ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ማዕከሎች” ሊኖሩት እንደሚችልም በሚያዚያ ወር 2025 ለቢቢሲ አስታውቆም እንደነበር ይታወሳል።  ብርጌድ ንሓመዱን የሚቀላቀሉ ኤርትራውያን “ዋስትና ስለሚያገኙበት መንገድ” ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር “መነጋገሩን” የእንቅስቃሴው አመራር ጨምሮ መናገሩ በወቅቱ ተዘገቦ ነበር። 

አምባሳደሩ ሉዊስ ፲፮ (Louis XVI)፣ ዛር ኒኮላስ (Czar Nicholas)፣ ኒኮላይ ቻውሼስኩ (Nicolae Ceaușescu)፣ መንግሥቱ ኃይለማርያም እና ሙዓመር ጋዳፊን የመሳሰሉ ከሥልጣናቸው የተወገዱ አምባገነን መሪዎችን በመጥቀስ፣ የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ዕጣ ፈንታቸው ከዚህ የሚለይ እንደማይሆን አስታውቀዋል።

ውጥረቱና የሥርዓቱ ፍጻሜ

የአምባሳደሩ ማስጠንቀቂያና ግምገማ በተለይም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ያለው ውጥረት እጅግ በጣም ከፍ ባለበት ወቅት የተሰማ መሆኑ ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጠው ሆኗል። የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አዛዥ የነበሩት ጀኔራል አበበ ተክለኃይማኖትም ከወራት በፊት በሰጡት አስተያየት፣ ጦርነቱ ቢነሳ የሻዕብያ ሥርዓት “ግብዓተ መሬት” የሚፈጸምበት ሊሆን እንደሚችል ግምት ማስቀመጣቸውን በማስታወስ የግምገማውን መገጣጠም ያነሱ አሉ። 

መኮብለል ወይም እንደ ጋዳፊ መሆን መናገራቸው ሳይሆን፣ ደጋፊዎችን አንስተው የተናገሩት ነው። የሥልጣን ዘመናቸው እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያመለክታል። የኤርትራ ሰማያዊ አብዮት ግንባር ደግሞ ከአምባሳደሩ ጋር መወያየቱ፣ የፕሬዝዳንት ኢሳያስን ሥርዓት ለመቀየር ያለውን ቆራጥነት ያሳያል፤ ይህም የትግሉ ማዕበል ወደ አዲስ ምዕራፍ እየተሸጋገረ መሆኑን

የሚያመላክት ነው።

እጅግ ከፍተኛ ስሜት የሰጠው ምልከታቸውና ማሳሰቢያቸው አምባገነን መሪዎችን የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ በማስታወስ፣ የፕሬዝዳንት ኢሳያስን መጨረሻ የመቃረቡን ጉዳይ መጠቆማቸው ብቻ ሳይሆን፣ 

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...