ከኤርትራ ወታደሮች በትዕዛዝ በትግራይ እናቶች፣ እህቶችና ሕጻናት ማህጸን ውስጥ የተላኩ ደብዳቤዎች፤

Date:

በቀናት ልዩነት የኤርትራ ወታደሮች በተቀነባበረ፣ ዝግጅት በተደረገበትና ማሳካት የሚፈልገውን ዓላማ ባማስቀመጥ በትግራይ የፈጸሙትን የጅምላ ጾታ ጥቃት፣ ዝርፊያና ግፍያ ‘ዘ ሴንትሪ’ የተባለ ተቋማና ዘጋርዲያን በጁላይ 2025 ይፋ አድርገዋል። 

ለመስማት የሚዘገንነው ሪፖርት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ሴቶች ማሕጸን ውስጥ “የዛጉ ብሎኖች፣ ስፒሎች እና የፕላስቲክ ቆሻሻዎች ይጨምራሉ” ያላል፡፡ ዘጋርዲያን የኤርትራ ወታደሮች ዕድሜ ሳይመርጡ በትግራይ ሴቶች ላይ የፈጸሙትን ዘግናኝ የጅምላ ወሲባዊ ጥቃት ያቀረበው በማስረጃ አስደግፎ ነው። 

“እኛ የኤርትራ ልጆች ጀኞች ነን፤ ለዚህም እራሳችንን ጥተናል፤ በዚህ ተግባራችን ወደፊት እንቀጥላለን፤ የትግራይ ሴቶችን መካን እናደርጋለን ወይም ማሕጸናቸውን እናደርቃለ” የሚለው ማስታወሻ የተገኘው በትግራይ ሴቶች ማህጸን ውስጥ ነው። ደብዳቤውን በእጃቸው ጽፈው በላስቲክ በመጠቅለል በትግራይ እናቶችና ህጻናት ማህጸን ውስጥ ያስቀመጡት የሻዕቢያ ወታደሮች ናቸው። ይህ የሚሆነው ደግሞ በደቦ የአስገድዶ መድፈር ከተፈጸመ በሁዋላ ነው።

“Sons of Eritrea, we are brave,” the note reads. “We have committed ourselves to this, and we will continue doing it. We will make Tigrayan females infertile.”

‘ዘ ሴንትሪ’  The Eritrean Defense Forces Intervention in Tigray የኤርትራ ወታደሮች ጣልቃ ገብነት በትግራይ ሲል ባዘጋጀው ባለ አርባ አምስት ገጽ ሪፖርት፣ በገጽ 14፣ “Sexual violence” በሚለው ርዕስ ስር ዘጋርዲያን ከጻፈው ጋር የሚመጋገብ ሪፖርት አስፍሯል። 

በስም የተጠቅሱ የኤርትራ ጄነራሎች ወታደሮቻቸው በትግራይ ሴቶች ላይ እንዲያደርጉ ከታዘዙትና ከተነገራቸው ባነሰ ደረጃ ግፍ መፈጸማቸውን ገልጸው ይወቅሷቸው እንደነበር ምስክሮቹ ተናግረዋል። እንዲያደርጉ ከታዘዙት ባነሰ መልኩ “they were doing less than what they had been ordered to do by their commanders” 

የኤርትራ የጦር ጄነራሎች ወታደሮቻቸውን በአፈጻጸም ማነስ የሚከሷቸው አንድ የሰባ ሁለት ዓመት አሮጊትን ለሰባት መድፈራቸውን ጭምር ነው። መሠረት ሃዱሽ ይህ ሪፖርት ከመጣቱ በፊት በትግራይ ባቋቋመችው ግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥ የገጠማትን ስታስታውስ በምንባ ነበር። 

“ሰዎች አይደሉም፣ አውሬዎች ናቸው” በማለት የምትጀመረው መሠረት፣ አንድን ሴት ኝድ ላይ አስረው ይደፍሩ እንደነበር፣ በአንድ ቤት ውስጥ እናት፣ ልጅ፣ የልጅ ልጆች ተቀምጠው ሳለ የኤርትራ ወታደሮች ይገባሉ። ሁሉንም ሳይመርጡ በቡድን እየተያዩ መድፈር ይጀመራሉ፣ ትንሿ የ3 ዓመት ልጅ ስታለቅስ ወደ ውጭ ይወረውሯታል። ልጅቷ አሁን ድረስ አጸማም፣ አትናገረም። በዚህ ደረጃ የሚፈጸም ግፍን ነው ጄነራሎቹ “ ከተባለው በታች” ሲሉ ወታደሮቹን የሚገመግሙት።

ሪፖርቱ የኤርትራ ወታደሮች ሲቶቹን በቡድን ከደፈሩዋቸው በሁዋላ ባዕድ ነገር በማህጸናቸው እንደሚከቱ ያስረዳል። በኤክስሬና በምስል የተደገፈው ይህ መረጃ ድርጊቱ ምን ያህል የከፋና ከሰውነት ውጪ ያፈለገጠ ነው። ለኤርትራ መኮንኖች ግን ይህ አያረካቸውም። 

“We will make the Tigrian’s uterus unfertile፣የትግራይ ሴቶችን ማሕጸን እንዳርቃለን” በሚል በጃቸው ጽፈው በላስቲክ በመጠቅለል ማሕጸናቸው ውስጥ የሚያስቀምጡት የኤርትራ ወታደሮች “ በ90ዎቹ ያደረጋችሁትን አንረሳም” ሲሉ ቂም እምንዳለባቸውም በጽሁፋቸው ይገልጻሉ። 

“በአንድ ሴት ላይ ባሉ የተፈጥሮ ቀዳዳዎች ሁሉ እንደ ዝንብ ወረው ወሲብ ይፈጽማሉ” ስትል ከሰላባዎቹ ከሰማችው ጥቂቱን የምትናገረው መሠረት፣ የኤች አይቪ ቫይረስ ተሸካሚዎች ሆን ተቦ የትግራይን ሴቶች እንዲበክሉ እንደሚደረግ ተናግራለች።

እሷ ይህን ካለች ዓመታት በሁዋላ፣ በሪፖርቱ እንደተካተተው ኤች አይ ቪ ያለባቸው የኤርትራ ወታደሮች ሆን ብለው ንጹሃንን እንዲደፍሩ ይደረግ እንደነበር ተረጋግጧል። 

ሪፖርቶቹ ከወጡ በሁዋላ አስገራሚ የሆነው ለትግራይ ሕዝብ መብት እንታገላለን የሚሉ ወገኖች ሻዕቢያና ትህነግ አዲስ ህብረት በመጀመራቸው ዝምታን መምረጣቸው ነው።

ሪፖርቱን ያዘጋጀው ክፍል በዝርፊያ፣ በግድያና በአስገድዶ መድፈር ታቅዶ የተሰራውን ከዘረዘረ በሁውላ ለአሜሪካ፣ ላውሮፓ ሕብረት፣ ለእንግሊዝና አግባብ ላላቸው አካላት ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።

ኤርትራ ተጥሎባት የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ መነሳቱን ተከትሎ ሠራዊቷን መልሳ በማጠናከር በአካባቢው በተለይም በኢትዮጵያ መረጋጋት እንዳይኖር እያደረገች ነው ሲል አንድ የአሜሪካ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሪፖርት አመለከተ። ኤርትራ ግን የቀረበባት ክስ የፈጠራ እና ማሳበቢያ ነው በማለት በአካባቢው ለተፈጠረው ውጥረት ተጠያቂያዋ ኢትዮጵያ ናት ስትል ከስሳለች።

‘ዘ ሴንትሪ’ የተባለው የአሜሪካ የመብቶች ተከታታይ መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ሰኞ ዕለት ባወጣው ሪፖርት ኤርትራ ተጥሎባት የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ከሰባት ዓመት በፊት ከተነሳ በኋላ ሠራዊቷን መልሳ በመገንባት እና በማጠናከር “በጎረቤቶቿ በተለይም በኢትዮጵያ ውስጥ አለመረጋጋት እየፈጠረች ነው” ብሏል።

ከደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት በኋላ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በፍጥጫ ውስጥ የቆዩት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በ2010 ዓ.ም. የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ በተባባሩት መንግሥታት ተጥሎባት የነበረው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ እንደተነሳላት ይታወሳል።

“የተጣለባት ማዕቀብ በተነሳበት በአሁኑ ወቅት ኤርትራ ጦር ሠራዊቷን መልሳ እየገነባች፣ የመከላከያ ኃይሏን እያጠናከረች እና ጎረቤቶቿ እንዳይረጋጉ ማድረጓን ቀጥላለች” ሲል የአሜሪካው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ‘ዘ ሴንትሪ’ ያወጣው ሪፖርት ላይ አመልክቷል።

ሪፖርቱ አክሎም “ያለው ሁኔታ ሳይቀየር ባለበት የሚቀጥል ከሆነ [ኤርትራም] እያደረገች ባለው ትቀጥላለች ተብሎ ይጠበቃል” ሲል አስጠንቅቋል።

‘ዘ ሴንትሪ’ ባወጣው ሪፖርት በኤርትራ ላይ የቀረበውን ክስ በተመለከተ በፈረንሳይ ዜና ወኪል፣ ኤኤፍፒ የተጠየቁት የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል “የፈጠራ ትርክት” በማለት ሪፖርቱ የሌሎችን ድርጊት በኤርትራ ላይ “የሚያላክክ” ነው በማለት አጣጥለውታል።

ሚኒስትሩ አክለውም “በቀጣናው ለተፈጠረው አዲስ ውጥረት ምክንያቱ ኢትዮጵያ ከሕግ ውጪ በይፋ ወደብ እና የባሕር ጠረፍ የማግኘት ፍላጎት እንዳላት ማሳወቋ” መሆኑን በመጥቀስ ኢትዮጵያን ተጠያቂ አድርገዋል።

ባለፈው በዚህ ዓመት አጋማሽ ላይ የኤርትራ መንግሥት የቀድሞ የሠራዊት አባላት ወደ የክፍሎቻቸው ለዳግም ሥልጠና እንዲመለሱ እና ሌሎች ዜጎቹ ከአገር ለመውጣት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች ማጥበቁን ቢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል።

በዚህም ከ60 ዓመት በታች የሆኑ በኤርትራ ሠራዊት ውስጥ ያገለገሉ ዜጎች ተመዝግብው ወደ ማሠልጠኛ እንዲገቡ፤ እንዲሁም ከ50 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች ደግሞ ተገቢውን ፈቃድ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ሳያገኙ ከአገር እንዳይወጡ ዕገዳ መጣሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በትግራይ ጦርነት አንድ ላይ ቆመው የትግራይ ኃይሎችን የወጉት የኤርትራ እና የኢትዮጵያ መንግሥታት ወዳጅነታቸው መቀዛቀዝ የጀመረው ጦርነቱን ያበቃው የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ነው።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ የኅልውና ጉዳይ መሆኑን በይፋ ካሳወቁ በኋላ የሁለቱ አገራት ግንኙነት ወደ ውዝግብ እና መካሰስ ተሸጋግሯል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ኤርትራ በውስጥ ጉዳያቸው ጣልቃ እየገባች ታጣቂዎችን እየደገፈች ነው የሚል ተደጋጋሚ ክስ ሲያቀርቡ የቆዩ ሲሆን፣ በቅርቡም የኤርትራ ኃይሎች ከያዟቸው የኢትዮጵያ ግዛቶች እንዲወጡ ተጠይቋል።

ከሁለቱም አገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና መገናኛ ብዙኃን በተደጋጋሚ የሚሰማው ንግግር ዳግም ጦርነት ሊፈነዳ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

ኤርትራ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን ያመለከተውን ሪፖርት ያወጣው ‘ዘ ሴንትሪ’ የተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ዋነኛ ትኩረት የሚያደርገው ጦርነቶችን የሚደግፉ ስውር የገንዘብ ዝውውሮችን መከታተል ላይ ሲሆን፣ በአውሮፓውያኑ 2009 በኤርትራ ላይ የጦር መሳሪያ ማዕቀብ የተጣለባት ለሶማሊያ ጂሃዲስት ቡድኖች ድጋፍ ትደርጋለች በሚል ክስ መሆኑን ጠቅሷል።

ቁልፍ ምክሮች 

በአስቸኳይ ግጭትን ለመከላከል አሜሪካ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ እንግሊዝ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የኢትዮጵያ መንግስት፣ የኤርትራ መንግስት፣ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ተመልሰው ወደ ግጭት ከገቡ የከፋ ዓለም አቀፍ ምላሽና ማዕቀብ እንደሚጠብቃቸው ግልጽ መልእክት ማስተላለፍ አለባቸው።

አሜሪካ፣ እንግሊዝና አውሮፓ ሕብረት የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ብርጋዴር ጄነራል እዮብ ፍሰሃዬ፣ ብርጋዴር ጄኔራል ሲሞን ኦቅቡ ሜጀር ጄኔራል ሮማዳን ኦስማን አውሊያ በትግራይ ለተፈጸመው የሰብአዊ መብት ረገጣ ተጠያቂ ማድረግ 

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የድንበር ጉዳዮችን፣ እ.ኤ.አ. ህዳር 2 ቀን 2022 የተፈረመውን የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ያልተተገበሩ ጉዳዮችን፣ ጨምሮ በማጤን ለዓለም ዓቀፍ ሰላም እና ደህንነት ጠንቅ እንደሆነ ከውሳኔ ላይ መድረስ። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ ሁኔታውን የመከታተል እና ሪፖርት ለማድረግ በተቀመጠ ይህግ አግባብ ሥልጣን ያለው አጣሪ ቡድን ማቋቋም አለበት።

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ሃገራዊ የወርቅ ገበያ ዋጋ መናሩ የተለያየ ትንተና እየቀርበበት ነው

አዲስ ሪፓርተር ጥቅምት 12 ቀን 2018 አዲስ አበባ -...

ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ የተለያየ የፓለቲካ ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ችግሮቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበች

አዲስ ሪፖርተር ጥቅምት 2 ቀን 2018 በኢትዮጵያ እየተወሳሰበ የመጣውን...

“ኤርትራ እንደ አገር ትክሰማለች”

የአየር ንብረት ለውጥ አደጋና ስጋትን መቋቋም ከማይችሉት አገራት መካከል...