የጸረ – ቤተሰቡ የአንዳርጋቸው ጽጌ የፖለቲካ ውርዴ ውርስ፣ ባንዳነትና ክህደት

Date:

[በውሸት፣ በጥላቻና በባንዳነት የተገነባ የአንዳርጋቸው ጽጌ የፖለቲካ ማንነት] ለማያውቁት ሁሉ ሊነገር ይገባል። አንዳርጋቸው በሚመስሉት ሚዲያዎች በየጊዜው እየወጣ የሚናገረው ሁሉ ሃሰት መሆኑን መናገር ደግሞ ትውልድን መጠበቅ ነው። ቤተስቡን የበተነው ሞራል አልባው አንዳርጋቸው ብዙ የሚነገሩ የቅጥፈትና ትዳሩን አራክሶ የተልከሰከሰበት ታሪኩ፣ ስለ አጠቃላይ ስብዕናውና በዚሁ የረከሰ ስብዕናው አማካይነት ራሱን ለምን ለግርድና አሳልፎ እንደሰጠ ደጋግሞ ለትውልድ ማስታወቅ የህሊና ዕዳ ሆኖ ተሰምቶኛል።

በአለባቸው ጉብሳ – ነጻ አስተያየት

አንዳርጋቸው  ተረስቷል። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ቦታ የለውም። ስለዚህ ሰውዬ አሁናዊ የፖለቲካ ዓቋም የመጻፍ ፍላጎት አልነበረኝም፣ ስለተረሳ ሰው መጻፍ የአዕምሮን የትዝታ ማኅደር የመቀስቀስ ዓቅም ስላለው። ለዚህም ነው፣ ዝምታ ትልቁ ጸረ ፕሮፓጋንዳ እንደሆነ የሚገለፀው። 

ሆኖም ግን አዲሱ ትውልድ ማወቅና መማር ስላለበት የስድሳዎቹ ትውልድ አባላት (በተለምዶ “ያትውልድ” ተብሎ የሚጠራው) የባዕዳንን ማርክሲስት ሌሊንስት ርዕዮተ ዓለም ተቀብለው ሃገርን ያቆሙና ያጸኑ ከቤተሰብ፣ ከሃይማኖትና ከሃገር ፍቅር አርበኝነት የሚመነጩ እሴቶችን በመሸርሸር አሁን ላለንበት ውጥንቅጥና ልሽቀት እንዴት እንዳደረሱን የአንዳርጋቸውን የነተበ የፖለቲካ ተክለስብዕና መሠረት በግልጽ ማቅረቡ ትክክል ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ጊዜውም ነው።

ጸረ – ቤተሰቡ አንዳርጋቸው

ማርክሲስቶች ለማጥፋት ከሞክሩት የሃገር ምሶሶዎች አንዱ ኢትዮጵያዊ የቤተሰብን ተቋማዊ እሴትን (ዋጋ) ነው። አንዳርጋቸው በማርክሲስት ሌኒንስት “የሕዝብ ልጅነት” ትርክት ሰክሮ ከመሠረታዊው የቤተሰብ ተቋም የኢትዮጵያ እሴት (values) የተፋታ ነው። ቤተሰብ አጽንቶ አስተዳድሮ አያውቅም፣ቤተሰብ አፍቃሪም አይደለም። ራሱ በትወልድ አይደናገር መጽሐፉ ራሱ ተደናግሮ ካቀረበልን በተጨማሪ የኢሳት ስቱዲዮ ውስጥ የፈጸመው ውስልትና “ ጋሼ ለገሰ”ና መላው የኢሳት ባልደረቦች ያውቁታል። ለነገሩ “ጋሽ ለጌ” እሳቸውም ከአሜሪካ አዲስ አበባ “ስራ” ብለው ሲከርሙ ባያስወልዱም እዛው አካባቢ ያጫውቱ ስለነበር ነገሩ “ከዝንጀሮ ቆኖጆ” ነውና ልለፈው። 

ወደ ቤተሰብ ጉዳይ ከመሄዴ በፊት ለሴቶችና ለወላጆቹ ያለውን ቦታ በተመለከተ ራሱ ያለውን ልጥቀስ። “ትውልድ አይደናገር” በሚለው መጽሐፉ ገጽ 174 ላይ ስለ እናቱ እግር ውበት ሲናገር የብዙ አበሻ ሴቶች እግር እንደ ጭራሮ የቀጠነ ነው በማለት በጅምላ ያንቋሽሻል። ለዚህ አባባሉ ማስረጃም ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ ሮም ላይ “ምን ያደርጋል ታዲያ እግርሽ የዶሮ ሆነ” በማለት ፋሽስቶች በሀገራችን ሴቶች የተሳለቁበትን የሙዚቃ ሬኮርድ በመጥቀስ አብሮ ይሳለቃል። እዚህ መጽሐፉ ላይ ስሟን ጠቅሶ ጡቷን ስለነካት ሴት እና ስለ ሌሎች ሴቶች የጻፈውን ለአንባቢው ግምገማ ልተወው። 

“በህጻንነቴ ጨለማ ውስጥ አኩርፌ የመቀመጥ ልምድ አለኝ” የሚለው አንዳርጋቸው፤ በልጅነቱ መልኩ ከእህትና ከወንድሙ ጠቆር ማለቱ ያሳደረበት ተጽዕኖ ወላጆቹን እንደ ሰይጣን እስከ መቁጠር እንዳደረሰው ይናገራል (ገጽ 223-224)። እንዲያውም ልብሱን አወላልቆ፤ እርቃኑን ከግቢው በመውጣት ወደ መንገድ ይሄድ እንደነበር ይገልጻል። በዚህ መልኩ ራሱን የሚገልጸው አንዳርጋቸው እናቱ ለእርሱ በጎ ስሜት በማሳየት ሲንከባከቡት እንኳ “የሷ ልጅ ስላልሆንኩ ሆድ እንዳይብሰኝ ነው የምንትከባከበኝ” በማለት መልካሙን በክፉ በመመንዘር ያደገ ልጅ እንደነበረና ይህም በእርሱ ባሕርይ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳሳደረበት በግልጽ ይናገራል (ገጽ 225)።

አንዳርጋቸው የሰማንያ ትዳሩንና ልጆቹን ሜዳ ላይ በትኖ በነፃነት ትግል ስም ጫካ ለጫካ ሲሽሎኮለክ የነበረ ከመሆኑም በላይ ሲታሰር የልጆቹ እናት ለትዳሯ ታማኝ ሆና ብቻዋን የቤተሰብ ኃላፊነት እየተወጣችና እሱ ከእስር እንዲፈታ በየኤምባሲው እየተማጸነች በየአደባባዩ እየጮኸች የነበረች ብርቱ ሴት ነበረች። ይህ በዓለም አደባባይ የተመሰከረ ሃቅ ነው። ልጆቹ “አባታችንን ፍቱልን” እያሉ ፍቅር ሰጥተውታል። እሱ ግን በዛ ደረጃ የታመነውን ቤተሰቡን አዲስ አበባ በሚሰራበት ስቱዲዮ ውስጥ ተንደባሎ አርክሶታል። ስቱዲዮ ውስጥ የልጅ አባት የሆነ የስራ መሪ ሆኖ ባለ ልዩ “ታሪክ” ሆኗል። ጋሽ ለገሰ ምስክር ናቸው። ሌሎችም …. እዚህ አዲስ አበባ በኪራይ ኖራ ወደ ኡጋንዳ አሻግሮ ስቃይ ላይ የጣላትን ፍለጎ የሚያናገር ሚዲያ ካለ …

አንዳርጋቸው ይህችን ብርቱ ሴት ከድቶ ሌላ ሴት ከማማገጥ ወደ ኋላ አለመመለሱ ምን ያህል ሞራሉ የገሸበና ርካሽ መሆኑን የሚያመላክት ትልቅ ማሳያ ስለሆነ ላልፈው አልቻልኩም። አንዳርጋቸው ለቤተሰቡ ታማኝ ካለመሆኑም በላይ ይህንኑ ሃፍረቱንና ብልግናውን ተሸክሞ በግብር በሚመስሉት ሚዲያዎች አማካይነት ሕዝብ ፊት ይቆማል። ይህ አንዳርጋቸው ነው በዚህ ሁሉ የሃፍረቱ ቡሉኮ ተጀቡኖ ስለ ኢትዮጵያ ሊሰብከን የሚወደው። ስለ ሌሎች ስብዕና ልተርክ አይኑን በጨው አጥቦ የሚጣደው። 

ለቤተሰብ ተቋም እሴት ቅንጣት ያህል አይጨነቅም። ምንም ፀፀት አይታይበትም። “ሕይወቱን በሙሉ ለሕዝብ ነፃነት እየታገለ” ብላችሁ ምክንያት በመፍጠር ሌላ ስህተት እንዳትሠሩ። በትንሹ ለቤተሰቡ ታማኝ ሆኖ (family loyalty ኖሮት) ተቋሙን አፅንቶ ነፃ ሳያወጣ ሕዝብን ነፃ የሚያወጣበት ዓቅም የለውም። ውሸት ነው። በማለት ሃቁን ለመግለጽ የተነሳሁት አስንዳርጋቸው ማለት እንዲህ ያለ ሞራሉ የወደቀ በመሆኑ ነው።

በሰለጠኑ ሃገራት የአንድ ሰው የፖለቲካ ቅቡልነት ዋና መለኪያው ቤተሰቡን መምራት መቻሉ ነው። የቤተሰብ ተቋም በሃገር አስተዳደር ይመሰላል። ቤተሰብ የሃገርና የኅብረተሰብ መሠረት ነው። የቤተሰቡን ደኅንነት ያልጠበቀ፣ የሚያስፈልገውን መሠረታዊ ፍጆታ ያላሟላ እና ለትዳር አጋሩ ታማኝነቱን በተግባር ያላሳየ ፖለቲከኛ ወይም የአደባባይ ሰው እንኳን የሃገር አስተዳደር ውስጥ በመሪነት ሊመራ አይቻለውም። መሪ ሊሆን አይገባውም። ቅቡልነት የለውም። ያደግንበት ማኅበረሰብ ትዳር ያልመሠረተን ለእድር ዳኝነት እንኳ በእጩነት አያቀርብም። ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያውያን ለቤተሰብ ተቋም ትልቅ ቦታ እንደሚሰጡ ነው። በትንሹ ለእድር ዳኝነት ያልበቃ ለሃገር መሪነት ብቁ አይሆንም። ለአደራ አይበቃም። እንኳን በትልቁ የሃገር አስተዳደር ቀርቶ በእድር ውስጥ እንኳ ኃላፊነት አይሰጠውም። 

ይህን ከጥንት ጀምሮ ተቀባይነት ያለውን የአመራር ቅቡልነት መለኪያ እንደገና ማንበር ካለብን አሁንኑ መጀመር አለብን። አንዳርጋቸውና መሰሎቹ በዚች ሃገር የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ ቅቡልነት እንዳይኖራቸው በይፋ ማውገዝ አለብን። 

ውሸት ጌጡ አንዳርጋቸው

የአንዳርጋቸው ውሸታምነት ከሁለት ምንጮች ይቀዳል። ከማርክሲስት ሌኒንስት የትግል ስልት እና ከጥላቻ። ውሸት የልቦና ውቅሩ አንድ አካል የሆነበት ምክንያት ኢሕአፓ ከሌኒን What is to be done መጽሐፍ በቀዳው የአባላት መታገያ ስልት ማስተማሪያ መጽሐፉ ውስጥ ውሸት የፖለቲካ ግብን የሚያሳካ ከሆነ የሚፈቀድ ሞራላዊ ተግባር እንደሆነ በግልፅ አስፍሯል። አንዲ ደግሞ ይህን ማስተማሪያ ድርሳን በቁም መዝለቅ እንደ ልህቀት መገለጫ አድርጎ እያነበነበ ያደገ ሰው ነው።

ውሸት የማንነቱ አንድ አካል ሆኖ አድጓል። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የፖለቲካ ግቡን የሚያሳካለት ከሆነ “በሃሰት አትመስክር” የሚለውን ቅዱስ ቃል ከመተላለፍ ወደኋላ አይልም። ከዚህም ባለፈ፣ ማርክሲስት ሌኒንስቶች ፀረ-ሃይማኖት ናቸው። ሃይማኖትን እንደ ገዥ መደብ መጨቆኛ መሳሪያ ፈርጀው ከሃይማኖት የሚመነጩ የበጎ ምግባር አስተምህሮዎችን የሚቃረኑ ናቸው። ሃይማኖታቸውን ፖለቲካ ትክክለኝነታቸው(political correctness) እና ሳይንሳዊ ሶሻሊዝም ነው። ለዚህም ነው፣ ለፖለቲካ ትክክለኝነታቸው እንኳን መዋሸት፣ ነጩን ጥቁር ማለት ቀርቶ የፖለቲካ ተቃራኒያቸውን አቅድው፣ ጓዶቻቸውን ከኋላ አድበተው የሚገድሉት።

ሌላኛው የውሸት ምንጭ ጥላቻ ነው። አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር ከተፈታ በኋላ ያለውን ልምድና ተሰሚነት ተጠቅሞ ለለውጡ መንግሥት ምክርና ድጋፍ ሲሰጥ እንደነበር ማንም የማይክደው ሃቅ ነው። ከሻዕቢ ጋር የመሠረተውን ወዳጅነት በመጠቀም ለረዥም ዓመት ዝግ የነበረው የኤርትራንና የኢትዮጵያ ግንኙነት እንዲከፈት ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጓል። በፌደራል መንግሥትና በሕወሃት ጦርነት ወቅት፣ ሻዕቢያ ህወሃትን ለማጥፋት ያለውን ዓላማ ለማሳካት፤ ከፍተኛ የወታደራዊ ፕራፓጋንዳ ዘመቻ ውስጥ በመሳተፍ የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት ደግፏል። ሌላም ሌላም።

ሆኖም ግን አንዳርጋቸው ለራሱ የተጋነነ ግምት አለው። ይህም ፋወሎችን እንዲፈጽም በር ከፈተ። ከሱ አቅም በላይ የሆኑ ብዙ ገንዘብና የሰው ሃብት የሚያስፈልጋቸውን የመረጃ ጉዳዮች (Counter intelligence) እንደ ወረደ ታምነው ውሳኔ እንዲወሰንባቸው ይፈለጋል። እነዚህ ሁሉ የሃገርን ብሔራዊ ጥቅም ስሌት ውስጥ ሳያስገባ ለህወሃት ካለው ከግል ጥላቻ የሚመነጩ ነበሩ።

ከዚህ በተጨማሪ ህወሃት ጋር የሚደረግን ዕርቀ ሰላም እና የፕሪቶሪያ ስምምነት እንደ ክህደት ቆጠረ። በዚህ ጉዳይ በዐቢይ አስተዳደር ውስጥ ተሰሚነቱ እየቀነሰ መጣ። ይህ ተሰሚነት መቀነስ ታህታይ ምስቅልና ውስጥ እንዲገባ አድርጎ ጥላቻው ጨመረ። ታላቁ ፈላስፋ ፍሬድሪክ ኒቼ “የጥላቻ ዘረ-መል” በተሰኘው የስነ ልቦና ድርሳኑ በደንብ እንደገለፀው፤ አንዳርጋቸው በጥላቻ ታውሮ የገሃዱ ዓለምን እውነታ መካድ ጀመረ። ኒቼ እንደሚለው አንዳርጋቸው የእሴት ቅልበሳ (Inversion of Values) ውስጥ ገባ። የራሱን የውሸት አለም ፈጠረ። 

በዐቢይ አስተዳደር የሚፈፀሙ በዓይን የሚታዩ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊና ቴክኖሎጂያዊ ስኬቶችና ለውጦች ከራሱ የቅዥት ዓለም ጋር ስለሚለያይ እንደ እውነት ሊቀበላቸው አልቻለም። በመሆኑም በአዕምሮው ውስጥ በቅዠት ከፈጠራት በዐቢይ አህመድ መሪነት ፍትህ፣ እኩልነት፣ ነፃነት የሌለባት በድህነት አረንቋ ውስጥ የተዘፈቀችው ኢትዮጵያ ጋር መስማማት ስላለበት ይዋሻል። ይዋሻል አይገልፀውም፣ ይበጠረቃል እንጂ።

ስለዚህ አንዳርጋቸው ጽጌ ትላንት በአደባባይ የተናገረውን እና በመጽሐፍ ያሳተመውን ሃሳቡን ዓይኑን በጨው አጥቦ የሚክደው፣ የሚዋሸው። ትላንት ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣቷ የሻዕቢያና የህወሃት ሤራና በደል እንደሆነ ሲነግረን የነበረ ሰውዬ ዛሬ ተገልብጦ “ትክክል አልነበርኩም፣ በጉርምስና እድሜ የፃፍኩት ነው፣ የተናገርኩት ነው” ቢለን ልንገረም አይገባም።

ባንዳው አንዳርጋቸው

አንዳርጋቸው ባንድነትን የወረሰው ከኢሕአፓ ነው። ኢሕአፓ በዚያድ ባሬ ከምትመራው ተስፋፊዋ ሶማሌ ጋር አብሮ ኢትዮጵያን በባንዳነት ወግቷል። ከሃገራቸው ብሔራዊ ጥቅም በተቃራኒ በመቆም የሃገራቸውን መከላከያ ሠራዊት ከውስጥ ሆነው ከጀርባው ወግተዋል። አጥቅተዋል። ለዚህም እስካሁን ድረስ ፀፀት አይታይባቸውም። የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ አልጠየቁም። ይህ ሥር የሰደደ ባንዳነት የሚመነጨው የማርክሲስት ሌኒንስት ውላጅ ከሆነው ከፖለቲካ ትክክለኝነታቸው ነው።

አንዳርጋቸው የኢሕአፓ አባል ስለሆነ በድርጊቱ ተሳታፊ ባይሆንም ውጤቱን በሃሳብ ደረጃ ሙሉ በሙሉ ይቀበለዋል። አሁንም ከዚህ ከቀደመ የልቦና ውቅሩና ከቁሳዊ ሰቀቀኑ በመነጨ በባንዳነት ከታሪካዊ ጥላቶቻችን ጋር በማበር ሃገራችንን ከውስጥ ለማዳከም ቢሰራ አይገርምም። ይህን ሰው ውጉዝ ከመአርዮስ ማለት የነበረብን “ኢሳትን ያቋቋምኩት ከሻዕቢያ የመቶ ሺ ብር” የፋይናንስ ድጋፍ ተደርጎልኝ ነው ብሎ በአደባባይ የተናገረ ዕለት ነበር። ይህ ትልቁ ስህተት ነው። ክፉ ዓመል እንደማይለቅ ማወቅ ነበረብን። የፖለቲካ ሉዓላዊነቱን በሠላሳ ዲናር የሸጠን ግለሰብ የፖለቲካ አርኣያ ሰብ አድርገን ማየታችን ዋጋ እንዳስከፈለን መረዳት ይገባል።

አሁን አሁን ይህ የሻዕቢያ ውለታ አንዳርጋቸውን በባንዳነት ከጎናቸው እንዲሰለፍ አያደርገውም የሚሉ ወገኖችን መከራከሪያ ውሃ ባያነሳም ሃሳባቸውን አከብራለሁ። እነሱ የሚሉት የሻዕቢያ የስለላ ተቋም በአንዳርጋቸው ላይ ሌላ ምሥጢር ቢኖረው እንጂ አንዳርጋቸው ትላንት ጊዜው፣ ጉልበቱንና ዕውቀቱን ሰውቶ የታገለላትን በባንዳነት አያጠቃትም የሚል ነው። እኔ ደግሞ እላለሁ፣ አንዳርጋቸው ከልጅነት እስከ እውቀት ባንዳነትን ጌጡ አድርጎ ስለተቀበለ እንዲሁም በጥላቻ ስካር የቅዠት ዓለም ውስጥ ስላለ በማናቸውም ሁኔታ፣ ጊዜና ቦታ በፍርፋሪ ዳረጎት የሃገሩን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ለመስጠት ወደኋላ አይመለስም።

በአጠቃላይ የአንዳርጋቸው ፀረ-ቤተሰብ፣ ፀረ-ሃይማኖት፣ ፀረ-ሃገር እና እውነታ የሚመነጨው ከማርክሲስት ሌኒንስት እና ጥላቻ ከወለደው የስነ ልቦና ስብራት መሆኑን መረዳት ይገባል። ይህን ሃሳብ የበለጠ በማዳበር የፖለቲካ ትምህርት ቤቶች ምርምርና ጥናት ሊያደርጉበት ይገባል። እንዲሁም ትውልዱ ከእንደዚህ ዓይነት ባሕርና ድርጊት እንዲጠበቅ በማስተማሪያነት ሊውል ይገባል። በጊዜያዊ ሆይ ሆይታ እንደዋዛ መታለፍ የለበትም።

በመጽሐፉ ላይ “በህጻንነቴ ጨለማ ውስጥ አኩርፌ የመቀመጥ ልምድ አለኝ” እንዳለው አሁንም የተደረገለትን መልካም ነገር ከማየት ይልቅ በሽምግልና ዘመኑ እንደ ልጅነቱ አኩርፎ የፖለቲካ ጨለማ ውስጥ መቀመጥን መርጧል።

ዝግጅት ክፍሉ ይህ ጽሁፍ የጸሐፊው አስተያየት ብቻ ነው። የሚወክለውም የጸሐፊውን አቋም ብቻ ነው። መስልስ ለመጻፍ ወይም ተጨማሪ አስተያየት ለሚሰጡ መድረኩ ክፍት ነው። ከስር ባሉት አድራሻዎች ይጠቀሙ።


ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/profile.php?id=61577410241403
ዌብሳይት፡ https://addisreporter.com/
ኢሜል፡ info@addisreporter.com
ቴሌግራም፡ https://t.me/addisreporter11
X፡ https://x.com/addisreporter
ስልክ ቁጥር፡ +251981866434 / +251116393393

Share and Enjoy !

Shares

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

Share post:

Subscribe

spot_imgspot_img

Popular

More like this
Related

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዳር እስከዳር አመጽ ለማቀጣጠል በተጠራው ስብሰባ “አስቻይ ሁኔታ የለም ተባለ” ጃዋር በድጋሚ አፈገፈገ

"በዋሽንግቶን ዲሲና ሎንዶን አገር አንቀጥቅጥ ሰልፍ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ...

“አሳጋቾቹን ካህናት ስም ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን”

አዲስ ሪፖርተር - የወረታ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ...

ዩኒቨርሲቲዎች እንደ ነፃ የሃሳብ ሪፐብሊክ፣ የሁምቦልድት ፍልስፍና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሪፎርም እይታ

ቢልዱንግ እና የሃሳብ ትውልድ እሳቤዎች ሲቀናጁ ምሁራን የቆዩ የትርክት...